Get Mystery Box with random crypto!

'አሁን ቀብር ተፈፅሟል፣ የጭካኔ ግድያ የተፈፀመባቸው ለዘመናት በአካባቢው ያገለገሉ ሰዎች ጭምር ና | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

"አሁን ቀብር ተፈፅሟል፣ የጭካኔ ግድያ የተፈፀመባቸው ለዘመናት በአካባቢው ያገለገሉ ሰዎች ጭምር ናቸው"

ሁለት የዶዶላ ደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች ከነቤተሰቦቻቸው በትናንትናው እለት መገደላቸውን በስፍራው ካሉ ሰዎች እና በደብሩ ቀደም ብለው ካገለገሉ አንድ አባት የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

በዚህ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ያገለግሉ የነበሩ መሪጌታ ስምረት የተባሉ አባት ባለቤታቸውን እና ሁለት ልጆቻቸውን፣ እንዲሁም ዲያቆን ዳንኤል የተባለ አገልጋይ ከነባለቤቱ እና ሌላ አንድ ሰው ጋር በድምሩ ሰባት ሰው እንደተገደለ እነዚህ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

"አሁን ቀብር ተፈፅሟል፣ የጭካኔ ግድያ የተፈፀመባቸው ለዘመናት በአካባቢው ያገለገሉ ናቸው። ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ምሽት ሶስት ሰአት ገደማ ነው" ያሉኝ ምንጮች ከዚህ በፊትም በጥቅምት 2012 ዓ.ም ብዙ ሰዎች ተግድለው እንደነበር አስታውሰዋል።

ነፍስ ይማር።

@EliasMeseret