Get Mystery Box with random crypto!

ይህን መጋቢት 4/2016 ያጋራሁትን መረጃ መልሼ ላጋራው! ቤተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ታጣቂዎ | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

ይህን መጋቢት 4/2016 ያጋራሁትን መረጃ መልሼ ላጋራው!

ቤተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ታጣቂዎችን አስጠልለዋል፣ የመሳርያ ማከማቻ ሆነዋል፣ ማሰልጠኛ ናቸው እየተባለ በከፍተኛ የወታደራዊ አመራሮች [እና ፖለቲከኞች] ጭምር እየተሰነዘሩ ያሉ የጅምላ ፍረጃዎች ውጤታቸውን እናያለን።

መረጃው ትክክለኛ ከሆነ እነዚህን ቤተ ክርስቲያናት እና ገዳማት በትክክል ለይቶ አውጥቶ ህግ ማስያዝ ያስፈልጋል፣ ነገር ግን በደፈናው "ቤተ ክትስቲያናት እና ገዳማት" እየተባለ በሀገሪቱ ዙርያ ያሉ የእምነት ስፍራዎችን እና የሀይማኖት አባቶችን ለጥቃት እያጋለጠ ይገኛል።

Mark my word... በመንግስት ሀላፊዎች እና በአክቲቪስቶቻቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈፀመው የስም ማጥፋት እና የደፈና የጥላቻ ንግግር ካልቆመ ጥቃቶች፣ ግድያዎች ይቀጥላሉ።

ድርጊቱን ፈፃሚዎችም "መንግስት ራሱ መስክሮ የለ" በሚል የልብ ልብ ተሰምቷቸው ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ።

@EliasMeseret