Get Mystery Box with random crypto!

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የሰርጥ አድራሻ: @eliasmeseret
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 100.56K
የሰርጥ መግለጫ

Journalist-at-large

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-04-05 07:12:38 የካ ላይ እየተገነባ ያለው ቤተ መንግስትን ያካተተው የጫካ ፕሮጀክት ወጪ 10 ቢልዮን ዶላር

ለጋሽ ሀገራት በኢትዮጵያ ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ስዊዘርላንድ ላይ ሚያዝያ 8 ለማሰባሰብ ያቀዱት የገንዘብ መጠን 1 ቢልዮን ዶላር

በዚህ አመት ድርቁን ለመቀልበስ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን 3.2 ቢልዮን ዶላር

#ቁጥሮችአይዋሹም

@EliasMeseret
35.7K viewsElias M, edited  04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 19:13:59
ይህ መረጃ እንደወጣ...!

- አንደኛ፣ የተፈረመው የመግባብያ ሰነድ ከሶማልያ እና ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋር ያላትመናል፣ ሉአላዊ የሆነ ሀገርን አካል እንደ ሀገር እውቅና መስጠት አለም አቀፍ መርሆችን እና የመልካም ጉርብትና ስርዐቶችን ይጥሳል፣

- ሁለተኛ፣ ስምምነቱ የኪራይ ውል ለማድረግ የተፈፀ ስምምነት እንጂ የባለቤትነት ጉዳይ አይደለም፣

- ሶስተኛ፣ የታሰበው ወደብ ለወታደራዊ አገልግሎት እንጂ ለንግድ አገልግሎት አይውልም፣

- አራተኛ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ሼር ለመስጠት ውሉ ላይ መጠቀሱ አግባብ አይደለም፣ አየር መንገዱን ለአደጋም ሊያጋልጠው ይችላል፣

- አምስተኛ፣ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ተብሎ ጉዳዩን በአክቲቪስቶች ማስጮህ ውጤቱ ጥሩ አይደለም

... ብለን ነበር። በወቅቱ 'ባንዳ፣ ፀረ-ኢትዮጵያ' ተብለን ነበር። ይኸው ዛሬ በአለም failed states ሊባሉ ከሚችሉ ሀገራት አንዷ የሆነችው ሱማልያ እንኳን አምባሳደራችንን አባረረች፣ የአለም ሀገራት እና አለም አቀፍ ተቋማት ከሶማልያ ጋር ቆሙ። መንግስት አሁን ላይ የታሰበው ውል እንደተተወ ውስጥ ለውስጥ ቢያስነግርም ሶማልያዎች ግን በይፋ አሳውቁ ብለው እየተዘባበቱብን ነው።

ሀገራችን ላይ ይህ እንዳይሆን ነበር እንግዲህ ያንን ሁሉ ያልነው። አሁንም ግን ከስህተት አንማርም፣ ለህዝብ ግን ጉዳዩ ቀስ እያለ እየተገለጠ ያለ ይመስላል።

@EliasMeseret
40.8K viewsElias M, 16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 18:10:11 የአዲስ አበባ 'ልማት ኮሪዶር' ፕሮጀክትን በተመለከተ ዘ ጋርዲያን የተነሺዎችን ቅሬታ የያዘ መረጃ አጋርቷል

ተነሺዎች ለዘመናት ከኖሩበት ቤት እንዲወጡ አምስት ቀን ብቻ እንደተሰጣቸው፣ ከዛም ከሶስት ቀን በኋላ ውሀ ሆን ተብሎ እንደተቋረጠባቸው እና ንብረታቸውን በማውጣት ትርምስ ውስጥ ዝርፊያ እና ውድመት እንደደረሰባቸው ለሚድያው ተናግረዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ: https://amp.theguardian.com/global-development/2024/apr/04/dismay-in-addis-ababa-as-the-soul-of-the-city-is-razed-for-development-ethiopia
38.1K viewsElias M, 15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 17:56:16
ህጋዊ ምዝገባ ባላቸው የሬድዮ፣ ቴሌቭዥን፣ ጋዜጣ፣ መፅሄት እንዲሁም ሶሻል ሚድያ ገፆች ላይ ማስታወቂያ አሰርቶ ከዛም እሱን ተጠቅሞ ህዝብ የማጭበርበር ድርጊት እየተስፋፋ ነው

ህዝብ እነዚህ ህጋዊ እውቅና ያላቸው ሚድያዎች ላይ አንድ ማስታወቂያ ሲተላለፍ ከሌሎች በተለይ ከፍ ያለ እምነት ይኖረዋል፣ ስለዚህ ንብረትም ሆነ ምርት የመግዛት እድሉ ከፍ ያለ ነው።

በኋላ ግን ማጭበርበር ቢፈፀምባቸው ህዝብ ተበልቶ ይቀራል እንጂ እነዚህ ማስታወቂያ ያስተላለፉ አካላት ተጠያቂ ሲሆኑ አይታይም።

አንድ ሚድያ እያንዳንዱን የአስተዋዋቂ ድርጅት ሀሳብ እና ገመና ሊያውቅ አይችልም፣ ግን ቢያንስ ማስታወቂያው እውነተኛ መሆኑን ለማወቅ በተቻለ መጠን ጥረት ማድረግ አይገባውም?

@EliasMeseret
35.9K viewsElias M, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 16:38:30
በኢትዮጵያ ያለውን እርዳታ ፈላጊ ህዝብ ለመድረስ የሚያግዝ እና 1 ቢልዮን ዶላር ለመሰብሰብ ያለመ አለም አቀፍ ስብሰባ በጄኔቫ ሊካሄድ ነው

ሚያዝያ 8/2016 በስዊዘርላንዷ ከተማ በሚካሄደው በዚህ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ስብሰባ ላይ የሰብአዊ ቀውሱን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ በርካታ ሀገራት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከሁለት ወር በፊት ዘንድሮ በሀገሪቱ የተከሰተውን የምግብ እጥረት ለመፍታት 3.2 ቢልዮን ዶላር (ከ180 ቢልዮን ብር በላይ) ያስፈልገኛል ማለቱ ይታወሳል።

ሙሉ ሪፖርቱን አዲስ ስታንዳርድ ላይ ለማንበብ: https://addisstandard.com/global-leaders-to-gather-in-geneva-aiming-to-raise-1-billion-to-alleviate-ethiopias-humanitarian-crisis/

@EliasMeseret
34.8K viewsElias M, 13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 16:23:54
ሶማልያ በሞቃዲሾ የሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር በ72 ሰአት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ እንዳዘዘች ተሰምቷል

ከዚህም በተጨማሪ በሶማሊላንድ እና ፑንትላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያ ቆንፅላ ቢሮዎች እንዲዘጉ ቀነ ገደብ ማስቀመጧ ታውቋል።

እነዚህ ሁለት ቆንፅላ ቢሮዎች እንዲዘጉ እና ሰራተኞቻቸው ጠቅልለው እንዲወጡ አንድ ሳምንት እንደተሰጣቸው የዘገበው ጋዜጠኛ ሀሩን ማሩፍ ይህ ባይሆን ተጨማሪ እርምጃ እወስዳለሁ እንዳለች ፅፏል። ማሳሰቢያውን ያወጣው የሶማልያ ጠ/ሚር ቢሮ ነው።

ሬውተርስ በበኩሉ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙርያ ተጨማሪ መረጃ ጠይቆ ቃል አቀባዩ መረጃ እንደሌላቸው እንደነገሩት ዘግቧል።

በዚህ ዙርያ ከደቂቃዎች በፊት ያናገርኳቸው አንድ የዲፕሎማቲክ ምንጭ ለዚህ ውሳኔ ምክንያት ሊሆን የሚችለው ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ቀናት የሶማልያ ራስ ገዝ አስተዳደር የሆነችው ፑንትላንድ ባለስልጣናትን ተቀብላ በአዲስ አበባ ማነጋገሯ እንደሆነ ጠቅሰው ይህም ከሶማሊላንድ ስምምነት ጋር ተዳምሮ የፈጠረው ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰዋል።

"ባለኝ መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ የሶማሊላንድ የወደብ ስምምነትን እንደማትተገብረው ደጋግማ ለሶማልያ መንግስት በቀጥታም፣ እንደ ኬንያ ባሉ ሌሎች ሀገራት በኩልም ደጋግማ አሳውቃለች" ያሉት እኚህ ምንጭ ሶማልያ ግን ውስጥ ለውስጥ ሳይሆን ኢትዮጵያ በይፋ ስምምነቱን እንደማትፈፅም ታሳውቅ በማለት እንዳልተቀበለችው ገልፀዋል።

ምናልባትም ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ በሶማልያ የሚገኘው ጦሯን ልታስወጣ እንደምትችል እኚህ ምንጭ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

@EliasMeseret
36.1K viewsElias M, edited  13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 07:02:59 የዛሬ ሳምንት የህዳሴ ግድብ የሲቪል ስራ 99%፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ ደግሞ 80% ተጠናቋል፣ ፕሮጀክቱ በሚቀጥለው አመት ያልቃል

አሁን ግንባታው እስካሁን 191 ቢልዮን ብር ፈጅቷል፣ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 50 ቢልዮን ብር ያስፈልጋል



@EliasMeseret
38.0K viewsElias M, edited  04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 05:56:09 ሽግግር ወደ ኤሌክትሪክ ትራንስፖርት!

በርካታ የአለማችን ሀገራት ከነዳጅ ወደ ኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ሽግግር ለማድረግ አስበው እቅድ አውጥተዋል፣ በዚህ ደግሞ የስካንዲኔቭያን ሀገራት ቅድሚያውን ይይዛሉ።

እኛ ሀገር ደግሞ ከሰሞኑ የኤሌክትሪክ መኪና፣ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል... ወዘተ በአስገዳጅነት እየተተገበረ ነው ወይም ሊተገበር ታስቧል።

የእኛ ሀገር 'ዋና አላማ' የተመናመነውን የውጭ ምንዛሬ ማዳን እንደሆነ ሲታመን ሌሎች በተለይ ያደጉ እና እንደ ህንድ ያሉ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ደግሞ የአካባቢ ብክለት ለመቀነስ ነው።

እንደ ቻይና ያሉ ሀገራት ይህን ቀስ በቀስ ለመተግበር እቅድ ይዘዋል፣ እኛ ሀገር ደግሞ በአስቸኳይ አሁኑኑ ይተግበር ተብሏል። ሌላው ቀርቶ የኤሌክትሪክ መኪና ብቻ ይግባ የሚለው ህግ እጅግ በአስቸኳይ አሁኑኑ ይሁን ከመባሉ የተነሳ እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር ያሉ አካላት መረጃው እንኳን አልነበራቸውም።

በዚህ ፅሁፍ ላነሳ ያሰብኩት ወደ ኤሌክትሪክ የሚደረገው አስቸኳይ ሽግግር ሊያጋጥሙት የሚችሉትን ተግዳሮቶችን እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ነው።

1. የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ የማድረጊያ ጣብያዎች በስፋት ያስፈልጋሉ፣ ይህ ከሚጠይቀው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት አንፃር ችግር ሊሆን ቢችልም አንዱ ዋና ጉዳይ ነው፣

2. የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በስፋት ባለበት ሀገር ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ የሚደረግ ሽግግር በርካታ ተሽከርካሪዎችን መብራት በጠፋ ቁጥር ከጥቅም ውጪ ሊያደርግ ይችላል፣

3. ይህ ሽግግር በነዳጅ ማጓጓዝ እና ማከፋፈል እንዲሁም ትንሽም ቢሆኑ የነዳጅ መኪና አምራች ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ በርካታ ግለሰቦችን ከስራ ውጪ ያረጋል፣ ስለዚህ ካሁኑ እነዚህን ዜጎች በሽግግሩ ሂደት ውስጥ ታሳቢ ማድረግ ያስፈልጋል፣

4. ሌላው አለም ካሁኑ እየተቸገረ ያለበት ጉዳይ ደግሞ አገልግሎት የጨረሱ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪዎች ጉዳይ ነው።  እንደ ቻይና ያሉ ሀገራት ይህ ከፍተኛ እና መርዛማ ብክለት እያስከተለባቸው ስለሆነ የህግ ማእቀፎችን አዘጋጅተዋል፣ ይህ በኢትዮጵያም ሊታሰብበት ይገባል፣

5. የኤሌክትሪክ መኪናዎች የመጓዝ አቅም ከግዜ ወደ ግዜ እየተሻሻለ ቢሆንም በነዳጅ ከሚሰሩት አንፃር ሲታይ በአንድ ቻርጅ መጓዝ የሚችሉት ርቀት በተለይ ወደ ክፍላተ ሀገራት የሚደረጉ ረጃጅም ጉዞዎች ላይ አስቸጋሪ መሆኑ አይቀርም።

6. በነዳጅ የሚሰሩ ሞተር ሳይክሎች በአስቸኳይ ወደ ኤሌክትሪክ ሞተር ይቀይሩ ተብሏል፣ ይህን ከፍተኛ ወጪ መንግስት የሚጋራው ስላላሆነ በሞተር ስራ ላይ ለሚገኙ በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል፣

ሲሆን ሲሆን በአመታት ወይም በወራት ሂደት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ማስወጣት (phase out ማድረግ) የተሻለው እንደሆነ በአለም ዙርያ ያሉ ተሞክሮዎች ያሳያሉ።

ካለ ምንም ሽግግር "ከዛሬ ጀምሮ" ተብለው የተተገበሩ እነዚህ ውሳኔዎች እነዚህንና ሌሎች ጉዳዮች በማሰብ ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ፣ ኢንቨስትመንት እና ትብብር ከሌለ ውጤቱ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

@EliasMeseret
40.8K viewsElias M, 02:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 05:56:00
36.2K viewsElias M, 02:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 05:18:01
አንዴ ወይም ሁለቴ ማሳሰቢያውን ይፋ ካደረገ በኋላ ስራውን በውስጥ አግባብ እና በህግ መሰረት መስራት ሲገባው በተደጋጋሚ በማህበራዊ ገፁ እና በየቅርንጫፍ ደጃፉ እንዲህ እያደረገ መሳለቂያ መሆን ምን ያስፈልጋል?

የዛን ሁሉ ሰው ፎቶ በፖስተር ለማሰራት ወጪውስ ስንት ይሆን? አንዳንዶች 'ባንኩ መራገም ቢጀምር ያዋጣዋል' እያሉ ይገኛሉ

ይህ በራሱ የባንኩ brand image ላይ ተፅእኖ ስላለው ቢያስቡበት።

Photo: Social Media

@EliasMeseret
41.7K viewsElias M, edited  02:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ