Get Mystery Box with random crypto!

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የሰርጥ አድራሻ: @eliasmeseret
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 100.56K
የሰርጥ መግለጫ

Journalist-at-large

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2024-03-31 01:32:31
በአዲስ አበባ የሚከናወነው 'የልማት ኮሪዶር' የሚነካቸውን ወይም የሚያካትታቸውን ስፍራዎች በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎች ደርሰውኛል

ይህንን በተመለከተ በመንግስት የተዘጋጀ አንድ ባለ 318 ገፅ ዝርዝር የማስተር ፕላን ዶክመንትን ዛሬ የተመለከትኩ ሲሆን ይህ በምስል 1 ላይ የምትመለከቱት ፕሮጀክቱ የሚያካትታቸውን ቦታዎች ነው።

- በዚህም መሰረት ከፒያሳ ጀምሮ ወደ ብሄራዊ፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ ሳርቤት፣ ጎተራ አድርጎ ወሎ ሰፈር ይደርሳል።

- ፕሮጀክቱ አምስት ክፍለ ከተሞችን (አራዳ፣ ልደታ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ቦሌ) የሚያካትት ሲሆን በአጠቃላይ 10.4 ኪ/ሜ ርዝመት ይኖረዋል፣ የፕሮጀክቱ ቦታ ስፋትም 460 ሄክታር ይደርሳል።

- ፕሮጀክቱን ለመፈፀም ተሞክሮዎች ከኩሪቲባ (ብራዚል)፣ ከቦጎታ (ኮሎምቢያ) እና ከካናሪ ዋርፍ (እንግሊዝ) ተወስደዋል።

- በፕሮጀክቱ መስመር ላይ ታሪካዊ ህንፃዎች ተብለው የተቀመጡት የአ/አ ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት ህንፃ፣ የድሮው ፖስታ ቤት፣ ባንኮ ዲሮማ፣ ሴጣን ቤት ቲያትር፣ እንደ ሊሴ ገ/ማርያም ያሉ ትምህርት ቤቶች፣ ፖስታ ቤት፣ ኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ፓርክ እና ክቡ የንግድ ባንክ ህንፃዎች ናቸው። እነዚህ በፕሮጀክቱ ሊነኩ የማይችሉ እንደሆነ ያሳያል።

- በመጨረሻም፣ 'የዲፕሎማቶች ሰፈር' የሚባል ፕሮጀክት የታሰበ ሲሆን ዲፕሎማቶች ብቻ የሚኖሩባቸው ኤምባሲዎች፣ ቆንስላዎች እና ተያያዥ አገልግሎት መስጫዎች ይገነባሉ (ምስል 2 ይመልከቱ)

@EliasMeseret
32.4K viewsElias M, 22:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 16:02:05 የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዚህችን ግለሰብ ጉዳይ "ወደ ወሎ ዩኒቨርስቲ ደውዬ እውነታውን አጣርቻለው" በማለት የሰራው ዘገባ እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ነው

ይህች እህት "ወሎ ዩኒቨርስቲ 12 አመት ልምድ አለኝ" አለች እንጂ ዩኒቨርስቲው አባረረኝ ወይም ከስራ ገበታ አፈናቀለኝ አላለችም፣ በማንኛውም ሁኔታ በተቋሙ ላይ ክስና አሉባልታ አላነሳችም።

በመቀጠል ወደ ዩኒቨርስቲው አንድ ኋላፊ ተደውሎ የዚህችን ሴት ችግር ያስረዳበት ቋንቋና በሚስጥር ሊጠበቅላት የሚገባ የግል ጉዳይ "የዐዕምሮ ታማሚ ነች" በመቀጠልም "የማህፀን ህመም አለብኝ ምናምን ትል ነበር" እያለ ከአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የማይጠበቅ ቋንቋዎችን እየተጠቀመ ተቋሙን ባልከሰሰችበት ሁኔታ የግለሰቧን ሚስጥሮች ሲያዝረከርክ ነበር።

ዩኒቨርስቲው አስተማሪዋን ከስራ ሳትለቅ ህክምናዋን እየተከታተለች ከተቋሙ ጋር እንድትቀጥል ቢለምንም "ህመሜን ለመከታተል አዲስ አበባ በቅርብ ህክምናዬን ለመከታተል ይመቸኛል በማለት በአቋማቸው በመፅናታቸው መልቀቂያ ሰጥቶ እንዳሰናበታቸውም ዩኒቨርስቲው ገለፀ" ብሏል።

አንድን ተቋም 12 አመት ያገለገለችንና ስራ ማጣቷን ብቻ ገልፃ ትብብር የጠየቀችን ሴት በብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ "የአዕምሮ ታማሚ ነች" እና "የማህፀን ህመም አለብኝ ምናምን ትል ነበር" የሚሉ መልዕክቶችን በ Fact Check ስም በአደባባይ ማስተላለፍ የተፈለገው የትኛውን ሃገራዊ መልካችንን ለመከላከል ነው?

አንድን ስራ ማጣቱን ብቻ ገልፆ ትብብር የጠየቀን ሰው ስም በአዕምሮ ህመምተኝነት እየፈረጁ እዝነት በሌላቸው ቃላቶቾ ለአደባባይ ሃሜት ማስጣትስ የግለሰቧን የጤና ሁኔታ አያባብስም ወይ?

ይህ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የወረደ ዘገባ እና የወሎ ዩኒቨርስቲ ሃላፊዎች መረን የቃላት አጠቃቀምና ባልተከሰሱበት ጉዳይ ራስን የመከላከል ጥድፊያ በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም።

ይህች እህታችን የስራ ቦታቸውን ለመልቀቅ ያስገደዳቸውና እንደተባለውም የዐዕምሮ ህመም ገጥሟቸው ከሆነ ለህመማቸው መነሻና መባባስ የሆኑ ምክንያቶች ከዩኒቨርስቲው የስራ ከባቢ የተወለደ ቢሆንስ? የሸሹት ለጤናቸው ቢሆንስ?

ሚድያው የግለሰቧን መልሶች ሰምቶ ሚዛናዊ ዘገባ ከመስራት ይልቅ አስከፊ ሀገራዊ ሁኔታችንን ለመሸፈን በሚመስል መልኩ ሌላ የዘቀጠ ዘገባ መስራቱ እንደ ኢቲቪ ያሉ ተቋማት ያሉበትን ደረጃ የሚያሳዩ ናቸው።

ምንጭ: ሙሉቃል ቃል

እኔም እላለሁ፣ Fact Check ማለት አንድን አካል ብቻ ሳይሆን ለምሳሌ ግለሰቧን፣ የህክምና ማስረጃ ካላት እሱን፣ የትምህርት ማስረጃዎቿን፣ ዩኒቨርስቲውን... በማናገር መረጃዎችን አመሳክሮ የሚሰራ እንጂ ግለሰቦችን ለማጥቃት ወይም የተቋማትን ስም ለመገንባት የሚከናወን ስራ አይደለም።

*ግለሰቧ የምትገኝበትን ስልክ ወይም አድራሻ የሚያውቅ ካለ በኮመንት ወይም ቴሌግራም ላይ @ContactElias ላኩልኝ።

@EliasMeseret
44.1K viewsElias M, edited  13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 16:01:54
40.7K viewsElias M, 13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-29 14:24:29 #NewsAlert በአዲስ አበባ ከተማ እየተስፋፋ የመጣው የእገታ ወንጀል

ከሰሞኑ በስፋት እየደረሱኝ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በፊት በፊት በክፍለ ሀገራት፣ ከዛም በአንዳንድ የአዲስ አበባ አቅራቢያ ስፍራዎች ሲከናወኑ የነበሩ የእገታ ወንጀሎች አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ መታየት ጀምረዋል።

ከ10,000 ብር ጀምሮ እስከ 1 ሚልዮን ዶላር የተጠየቀባቸው ሰዎች እንዳሉ፣ እገታዎቹ በቀንም ይሁን በጭለማ እንደሚከናወኑ፣ አብዛኞቹ የፀጥታ አካላትን በመምሰል (ወይም ሆነው... ይህ ሲጣራ ይታወቃል) ድርጊቱን እንደሚፈፅሙ እና ከመኖርያ ቤታቸው ጭምር የተወሰዱ ሰዎች እንዳሉ አረጋግጫለሁ።

እንደ ነጋዴዎች፣ ዲያስፖራዎች እና የውጭ ዜግነት ያላቸው ሰዎች እና ብር አላቸው ተብለው የሚገመቱ ማንኛውም ሰዎች በተለይ ኢላማ እንደሆኑ ታውቋል።

አጋቾቹ ድርጊቶቹን ከፈፀሙ በኋላ ታጋቾች ድርጊቱን ለፖሊስ እንዳያሳውቁ ስለሚያስፈራሩ ትክክለኛ የድርጊቱን መጠን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው።

ማስተባበል መቼም መፍትሄ ስለማይሆን አሁንም ሳይረፍድ የሚመለከተው አካል በይፋ ወደፊት በመምጣት ድርጊቱን ቢያንስ በይፋ ለህዝብ ማሳወቅ አለበት።

ከእንዲህ አይነት እገታ 'ተጠንቀቁ' ቢባል እንዴት መጠንቀቅ እንደሚቻል ባላውቅም... ብቻ ጥንቃቄ አይለየን።

@EliasMeseret
26.2K viewsElias M, 11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 18:30:48
"መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶችንና ምእመናንን አሰቃቂ ግድያ በማስቆም ከደሙ ነጻ መሆኑን በአስቸኳይ ሊያረጋግጥ ይገባል።"

እናት ፓርቲ

@EliasMeseret
36.0K viewsElias M, 15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 18:23:03
#እጃችሁንአንሱ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እና አባቶች ላይ የሚፈፀመውን ንቀት፣ ግፍ እና ግድያ እቃወማለሁ።

ሼር አድርጉት፣ ምስሉን ፕሮፋይል ፒክቸር በማድረግም ድምፅ እናሰማ። በጣም በዛ!

@EliasMeseret
36.7K viewsElias M, 15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 07:04:55
የሶማልያ አየር ተቆጣጣሪዎች ያደረጉት እንደሆነ በተጠረጠረ ድርጊት አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን እና ሌላ የኤምሬትስ አየር መንገድ አውሮፕላን ባለፈው እሁድ ወደግጭት አምርተው (collision course ላይ ሆነው) በመጨረሻ በፓይለቶች ጥረት እንደተረፉ ታውቋል።

ይህንን ክስተት የሶማሊላንድ ሲቪል አቪዬሽን አረጋግጦ መግለጫ ያወጣ ሲሆን በአየር መንገዶቹ በኩል ግን እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

በዚህ ዙርያ መረጃ የጠየቅኩት አንድ የአቪዬሽን ባለሙያ ክስተቱ ትክክል መሆኑን አረጋግጦ "ነገር ግን ሁለቱም አውሮፕላኖች የግጭት መከላከያ ሲስተም TCAS ስላላቸው ለፓይለቶቹ ያሳውቃቸዋል" በማለት ክስተቱ ግን አሳሳቢ መሆኑን አስረድቷል።

በተመሳሳይ በአንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በሌላ የኳታር አየር መንገድ አውሮፕላኖች ዙርያ ተመሳሳይ ድርጊት የዛሬ ወር ገደማ አጋጥሞ ነበር።

ታድያ ይህ በአጋጣሚ ሊሆን ይችላል?

ለማንኛውም፣ የዛሬ ወር የፃፍኩትን አሁንም ላስቀምጠው

"ብዬ ነበር ማለቱ ዋጋ ስለሌለው በአየር መንገዱ ላይ አደጋ ከመከሰቱ በፊት በረራ ወደ ሶማልያ ከማቋረጥ እስከ የበረራ አቅጣጫ መቀየር የሚደርሱ እርምጃዎችን መውሰድን ሊያጤን ይገባል ብዬ አስባለሁ፣ ቢያንስ የአለም አቀፍ የበረራ እና ሲቪል አቪዬሽን መስሪያ ቤቶች ምን እየሆነ እንደሆነ ምርመራ አድርገው እስከሚያሳውቁ። በዚህ አካሄዳቸው ሌላው ቀርቶ ሞቃዲሾ በረራ አድርጎ የቆመ የሀገራችን አውሮፕላን ላይ ምን ሊያጠምዱ እንደሚችሉ ማን ያውቃል?"

@EliasMeseret
39.7K viewsElias M, 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 19:18:49
በአንድ እና ሁለት የሶሻል ሚድያ ልጥፎች (ፖስቶች) ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል የዚህ የአየር ማረፊያ ጉዳይ አንድ ማሳያ ነው

ተጎጂዋ 'በእኔ ላይ የደረሰውን ልንገርህ፣ በሌላው ተጓዥ ላይም እንዳይደገም መፍትሄ ጠቋሚ ሊሆን ይችላል' በማለቷ ያቀረብኩት መረጃ ግቡን መቷል። በሌሎች ጉዳዮች ላይም እንዲህ በይፋ ባይነገርም ለውጦች እንደሚደረጉ እንሰማለን።

ይሁንና በሌሎች በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የህዝብ እሮሮዎች ይሰማሉ፣ ስለዚህ አንዳንድ ሚድያዎች በየቀኑ ይህንን የአየር ማረፊያ ጉዳይ እየደጋገሙ ከሚዘግቡ ወደነዚህ ሌሎች ህዝብን እያስጨነቁ ያሉ ጉዳዮች ቢያዞሩ መልካም ነው ብዬ አስባለሁ።

@EliasMeseret
40.9K viewsElias M, edited  16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-26 21:47:34
ከሚደርሱኝ ጥቆማዎች በመነሳት ማረጋገጥ የቻልኳቸው የቤት ፈረሳ መረጃዎች

- አያት ዞን አንድ ውስጥ ያሉ በርካታ 'ዘመናዊ' ሊባሉ የሚችሉ መኖርያ ቤቶች ስፍራው ለሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ግንባታ ስለሚፈለግ ተነሱ እንደተባሉ፣ ባለፈው እሁድ እለት በመንግስት አካላት ስብሰባ ተጠርተው ይህ በይፋ እንደተነገራቸው አረጋግጫለሁ። ይህ በአካባቢው ቤቶችን የማንሳት ጉዳይ ቀጣይ እንደሆነም ታውቋል።

- በቦሌ ክ/ከተማ በተለምዶ ጉርድ ሾላ ንግድ ባንክ አካባቢ አስፓልት ዳር ያሉ የግል ቤቶች ተለክተው አንዳንዱ ቤት እስከ ሳሎኑ፣ አንዳንዱ ደግሞ እስከ መኝታ ቤት ድረስ እንዲፈርስ መደረጉ ታውቋል። እስከ ሳሎን ድረስ ብቻ በልኬት የፈረሰባቸው ቀሪውን መኝታ ቤታቸውንና ኪችናቸውን ዛሬ ለመሸፈን መግቢያና መውጪያ በራቸውን ሲሰሩ በድጋሜ አፍርሰውባቸው እንደገና ፍቃድ አውጡ እንደተባሉ ተረጋግጧል።

#AddisAbaba

Photo: File

@EliasMeseret
46.6K viewsElias M, edited  18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-26 16:27:28 ይህን መጋቢት 4/2016 ያጋራሁትን መረጃ መልሼ ላጋራው!

ቤተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ታጣቂዎችን አስጠልለዋል፣ የመሳርያ ማከማቻ ሆነዋል፣ ማሰልጠኛ ናቸው እየተባለ በከፍተኛ የወታደራዊ አመራሮች [እና ፖለቲከኞች] ጭምር እየተሰነዘሩ ያሉ የጅምላ ፍረጃዎች ውጤታቸውን እናያለን።

መረጃው ትክክለኛ ከሆነ እነዚህን ቤተ ክርስቲያናት እና ገዳማት በትክክል ለይቶ አውጥቶ ህግ ማስያዝ ያስፈልጋል፣ ነገር ግን በደፈናው "ቤተ ክትስቲያናት እና ገዳማት" እየተባለ በሀገሪቱ ዙርያ ያሉ የእምነት ስፍራዎችን እና የሀይማኖት አባቶችን ለጥቃት እያጋለጠ ይገኛል።

Mark my word... በመንግስት ሀላፊዎች እና በአክቲቪስቶቻቸው ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈፀመው የስም ማጥፋት እና የደፈና የጥላቻ ንግግር ካልቆመ ጥቃቶች፣ ግድያዎች ይቀጥላሉ።

ድርጊቱን ፈፃሚዎችም "መንግስት ራሱ መስክሮ የለ" በሚል የልብ ልብ ተሰምቷቸው ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ።

@EliasMeseret
46.6K viewsElias M, 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ