Get Mystery Box with random crypto!

የሶማልያ አየር ተቆጣጣሪዎች ያደረጉት እንደሆነ በተጠረጠረ ድርጊት አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የሶማልያ አየር ተቆጣጣሪዎች ያደረጉት እንደሆነ በተጠረጠረ ድርጊት አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን እና ሌላ የኤምሬትስ አየር መንገድ አውሮፕላን ባለፈው እሁድ ወደግጭት አምርተው (collision course ላይ ሆነው) በመጨረሻ በፓይለቶች ጥረት እንደተረፉ ታውቋል።

ይህንን ክስተት የሶማሊላንድ ሲቪል አቪዬሽን አረጋግጦ መግለጫ ያወጣ ሲሆን በአየር መንገዶቹ በኩል ግን እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

በዚህ ዙርያ መረጃ የጠየቅኩት አንድ የአቪዬሽን ባለሙያ ክስተቱ ትክክል መሆኑን አረጋግጦ "ነገር ግን ሁለቱም አውሮፕላኖች የግጭት መከላከያ ሲስተም TCAS ስላላቸው ለፓይለቶቹ ያሳውቃቸዋል" በማለት ክስተቱ ግን አሳሳቢ መሆኑን አስረድቷል።

በተመሳሳይ በአንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በሌላ የኳታር አየር መንገድ አውሮፕላኖች ዙርያ ተመሳሳይ ድርጊት የዛሬ ወር ገደማ አጋጥሞ ነበር።

ታድያ ይህ በአጋጣሚ ሊሆን ይችላል?

ለማንኛውም፣ የዛሬ ወር የፃፍኩትን አሁንም ላስቀምጠው

"ብዬ ነበር ማለቱ ዋጋ ስለሌለው በአየር መንገዱ ላይ አደጋ ከመከሰቱ በፊት በረራ ወደ ሶማልያ ከማቋረጥ እስከ የበረራ አቅጣጫ መቀየር የሚደርሱ እርምጃዎችን መውሰድን ሊያጤን ይገባል ብዬ አስባለሁ፣ ቢያንስ የአለም አቀፍ የበረራ እና ሲቪል አቪዬሽን መስሪያ ቤቶች ምን እየሆነ እንደሆነ ምርመራ አድርገው እስከሚያሳውቁ። በዚህ አካሄዳቸው ሌላው ቀርቶ ሞቃዲሾ በረራ አድርጎ የቆመ የሀገራችን አውሮፕላን ላይ ምን ሊያጠምዱ እንደሚችሉ ማን ያውቃል?"

@EliasMeseret