Get Mystery Box with random crypto!

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የሰርጥ አድራሻ: @eliasmeseret
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 100.56K
የሰርጥ መግለጫ

Journalist-at-large

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2024-04-08 22:01:09
#FactCheck ይህን ቪድዮ በርካታ ሰዎች እያጋሩት ይገኛል

ቪድዮው መሬት ላይ የሌለ እና ሀሰተኛ ሲሆን ከአምስት አመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ተከስቶ የነበረን ግጭትና አለመረጋጋት የሚያሳይ ነው።

ማረጋገጫ:



ጊዜያቸውን ባልጠበቀና ከአውድ ውጭ በሆነ መልኩ የሚጋሩ ቪዲዮዎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ጥንቃቄና ማጣራት እናድርግ።

Courtesy: Ethiopia Check

@EliasMeseret
43.5K viewsElias M, 19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 15:43:37
በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ትላንት መጋቢት 29 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም አንድ ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በተከፈተባቸው የጥይት እሩምታ መገደላቸው ተነግሯል።

ትላንትና ምሽት በግፍ የተገደሉት አቶ ሙሄ ፣ልጃቸው አበባዉ ሙሄ፣ ሽኩር ሙሄ፣ ሙላት ሙሄ እና ጎረቤታቸው አቶ እንድሪስ የተባሉ ሲሆኑ ስርዓት ቀብራቸው በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።

እስካሁን ገዳዮች ስለመያዛቸው የተባለ ነገር የለም።

በከተማዋ ከተገደሉት ሰዎች ባሻገር ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ የሚገኘው መስጂድ ከፍተኛ የመሳሪያ ድብደባ እንደተፈፀመበት ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዛሬ የባህር ዳር ሙስሊሞች በክልሉ በሙስሊሞች ላይ አነጣጥረዋል ያሉትን ግድያ እና እገታ በመቃወም ሰልፍ ማድረጋቸውን "ሀሩን ሚዲያ" ዘግቧል።

እስካሁን በአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትም ሆነ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ አስተያየት የለም።

Via Tikvah Ethiopia

@EliasMeseret
45.7K viewsElias M, 12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 16:58:00
ፈጣን እና አስደሳች ስራ በአዲስ አበባ ፖሊስ!

አሁን እነዚህን ጭካኔያቸውን የሚመጥን ፍትህ በመስጠት ማስተማርያ ማድረግ ነው።

@EliasMeseret
35.8K viewsElias M, 13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 15:08:37 አሁን ደግሞ በቀጣይ የተቃውሞ ሰልፍ ተፈቅዶ ተቃውሞ ያለው ድምፁን እንዲያሰማ ቢፈቀድ የስርዐቱን ታጋሽነት፣ ዴሞክራሲያዊነት እና ሁሉን አካታች ህብረ-ብሄራዊነት ያሳይ ነበር... ያው ነበር ነው!

@EliasMeseret
40.8K viewsElias M, 12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 14:35:11
የሰጣችሁት ድምፅ ውጤት ይህን ይመስላል!

9 ፐርሰንት ወይም 1,585 ሰው >>> በፈቃዴ ድጋፍ ለመስጠት ሰልፍ እወጣለሁ

91 ፐርሰንት ወይም 15,994 ሰው >>> ካልተገደድኩ በቀር ደግፌ ሰልፍ አልወጣም

በአጠቃላይ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ህዝብ፣ ማለትም 17 ሺህ 579 ሰው ድምፅ በመስጠት ተሳትፏል።

@EliasMeseret
39.8K viewsElias M, edited  11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 00:51:36
የህግ ትምህርት ቤት እያለን ጀምሮ ወዳጄ የሆነው ጠበቃ ሙሉጌታ በላይ ንግድ ባንክ ከሰሞኑ እያወጣ ያለውን የተጠርጣሪዎች ፎቶ በተመለከተ ይህን ብሏል። ቪድዮው ሲጠቃለል:

- የግለሰቦችን ምስል ለህዝብ ማውጣት በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸው ፖሊስ እና ፍርድ ቤት ብቻ ናቸው

- ባንኩ ማድረግ የሚችለው በእነዚህ ፍቃድ ባላቸው ተቋማት በኩል ግለሰቦቹን ለመያዝ ካስፈለገ ለጥቆማ እንዲያግዝ ፎቷቸውን ይፋ ያስደርጋል እንጂ ራሱ ማድረግ አይችልም፣

- ባንክ ግለሰቦችን ወንጀለኛ ማለት አይችልም፣ ፖሊስም አይችልም። ብቸኛው ይህ መብት ያለው ፍርድ ቤት እና ፍርድ ቤት ብቻ ነው 

ትናንት ይህን ድርጊት በተመለከተ አንድ መረጃ አጋርቼ "ለሌባ ጠበቃ ቆምክ፣ አንተም ወስደሀል መሰለኝ..." አይነት ዝባዝንኬ አስተያየት የሰጡ ነበሩ።

ዛሬ ይህ ተቋም ከህግ ውጪ ፎቶ ሲለጥፍ "ለምን?" ካላልን ነገ የፈለገው ድርጅት እና ግለሰብ እየመጣ ፎቶህን ለጥፎ ያሻውን ያደርጋል።

ባለኝ መረጃ መሰረት በዚህ አስነዋሪ ድርጊት ላይ ያልተሳተፉ ሰዎች ጭምር ፎቷቸው ወጥቶ ፍርድ ቤት እያመሩ ነው፣ ሌሎቹ ደግሞ የወሰዱትን ብር መልሰው ፎቷቸው ግን ወጥቷል።

ሌብነትን እናውግዝ፣ ለህግ የበላይነት እና መከበርም እንቁም።

መልካም አዳር።

@EliasMeseret
47.0K viewsElias M, edited  21:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 20:08:30 አዳዲስ የዚህ የቴሌግራም ቻናል ሰብስክራይበሮች እንኳን በደህና መጣችሁ!

እስቲ የቻናሉ ነባር ኗሪዎች በ reaction ተቀበሏቸው።

17.4K viewsElias M, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 18:59:49
እንኳን ለሲዳማ ህዝብ የዘመን መለወጫ 'ፍቼ ጫምበላላ' በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

Ayidde Cambalaalla!

@EliasMeseret
22.3K viewsElias M, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 18:50:25
ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ እና እስራት ተፈፀመባቸው

ተማሪዎቹ የተራዘመ የመመረቂያ ግዜን በመቃወም ሰልፍ የወጡ ሲሆን የትግራይ የፀጥታ ሐይሎች ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙባቸው ለዶቼቬለ ተናግረዋል፣ 10 ተማሪዎች ደግሞ መታሰራቸው ተገልጿል።

እንደ ተማሪዎቹ ገለፃ በፖሊስ  የሐይል እርምጃ አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸው ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ግቢ ተነስተው ያሏቸውን ቅሬታዎች ለማሰማት ወደ መቐለ ከተማ ጎዳናዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት ነው።

ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተገደዱት በተለያዩ ችግሮች ለዓመታት ትምህርታቸው ሲስተጓገል ቆይቶ ዘንድሮ ለመመረቅ እየተጠባበቁ የነበረ ቢሆንም፤ ዩኒቨርሲቲው ሌላ ተጨማሪ ዓመት መማር እንደሚጠበቅባቸው ከተገለፀላቸው በኃላ ነው።

ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት ግን ለዩኒቨርሲቲው በተደጋጋሚ ቅሬታ ማቅረባቸውን እና ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልፀዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ በነበሩበት ወቅትም ጥይት በመተኮስ፣ በድብደባ እና በአፈሳ ፖሊስ ሰልፉን በሐይል መበተኑ ተማሪዎቹ አስረድተዋል።

Source: Deutsche Welle Amharic

@EliasMeseret
23.0K viewsElias M, 15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 14:22:27 #Repost አንዳንዶች "ትችቶች ላይ ማተኮርህ ለምንድን ነው?" የሚል አስተያየት ሲሰጡ አያለሁ።

ምክያቱ ይህ ነው፣ ሀገራችን ስዊዘርላንድ ወይም ስዊድን እስክትመስለን ድረስ በጎ በጎውን ብቻ ቀኑን ሙሉ ሲዘግቡ የሚውሉ በብዙ መቶ ሚልዮን ብር የሚቆጠር በጀት ያላቸው የመንግስት ሚድያዎች እና በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከመንግስት ድጋፍ የሚያገኙ አክቲቪስቶች የሚሰሩትን ስራ ከምሻማ ሌሎች ብዙ ትኩረት የማይደረግባቸው ጉዳዮችን እና መረጃዎችን ወደፊት ለማምጣት በማሰብ ነው።

አንደኛ ትችት ማቅረብ በሚድያ ህጉ በቀጥታ ይፈቀዳል፣ ሁለተኛ ትችቶች ማስተካከያዎችን ለማድረግ በር ይከፍታሉ፣ ይህ ደግሞ ተደጋግሞ ታይቷል። ከዛ ውጪ እኔ የዚህም ሆነ የዛ ደጋፊም፣ ተቃዋሚው አይደለሁም።

ይኸው ነው።

@EliasMeseret
30.1K viewsElias M, edited  11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ