Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዚህችን ግለሰብ ጉዳይ 'ወደ ወሎ ዩኒቨርስቲ ደውዬ እውነታውን አጣርቻለው' በ | ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዚህችን ግለሰብ ጉዳይ "ወደ ወሎ ዩኒቨርስቲ ደውዬ እውነታውን አጣርቻለው" በማለት የሰራው ዘገባ እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ነው

ይህች እህት "ወሎ ዩኒቨርስቲ 12 አመት ልምድ አለኝ" አለች እንጂ ዩኒቨርስቲው አባረረኝ ወይም ከስራ ገበታ አፈናቀለኝ አላለችም፣ በማንኛውም ሁኔታ በተቋሙ ላይ ክስና አሉባልታ አላነሳችም።

በመቀጠል ወደ ዩኒቨርስቲው አንድ ኋላፊ ተደውሎ የዚህችን ሴት ችግር ያስረዳበት ቋንቋና በሚስጥር ሊጠበቅላት የሚገባ የግል ጉዳይ "የዐዕምሮ ታማሚ ነች" በመቀጠልም "የማህፀን ህመም አለብኝ ምናምን ትል ነበር" እያለ ከአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የማይጠበቅ ቋንቋዎችን እየተጠቀመ ተቋሙን ባልከሰሰችበት ሁኔታ የግለሰቧን ሚስጥሮች ሲያዝረከርክ ነበር።

ዩኒቨርስቲው አስተማሪዋን ከስራ ሳትለቅ ህክምናዋን እየተከታተለች ከተቋሙ ጋር እንድትቀጥል ቢለምንም "ህመሜን ለመከታተል አዲስ አበባ በቅርብ ህክምናዬን ለመከታተል ይመቸኛል በማለት በአቋማቸው በመፅናታቸው መልቀቂያ ሰጥቶ እንዳሰናበታቸውም ዩኒቨርስቲው ገለፀ" ብሏል።

አንድን ተቋም 12 አመት ያገለገለችንና ስራ ማጣቷን ብቻ ገልፃ ትብብር የጠየቀችን ሴት በብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ "የአዕምሮ ታማሚ ነች" እና "የማህፀን ህመም አለብኝ ምናምን ትል ነበር" የሚሉ መልዕክቶችን በ Fact Check ስም በአደባባይ ማስተላለፍ የተፈለገው የትኛውን ሃገራዊ መልካችንን ለመከላከል ነው?

አንድን ስራ ማጣቱን ብቻ ገልፆ ትብብር የጠየቀን ሰው ስም በአዕምሮ ህመምተኝነት እየፈረጁ እዝነት በሌላቸው ቃላቶቾ ለአደባባይ ሃሜት ማስጣትስ የግለሰቧን የጤና ሁኔታ አያባብስም ወይ?

ይህ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የወረደ ዘገባ እና የወሎ ዩኒቨርስቲ ሃላፊዎች መረን የቃላት አጠቃቀምና ባልተከሰሱበት ጉዳይ ራስን የመከላከል ጥድፊያ በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም።

ይህች እህታችን የስራ ቦታቸውን ለመልቀቅ ያስገደዳቸውና እንደተባለውም የዐዕምሮ ህመም ገጥሟቸው ከሆነ ለህመማቸው መነሻና መባባስ የሆኑ ምክንያቶች ከዩኒቨርስቲው የስራ ከባቢ የተወለደ ቢሆንስ? የሸሹት ለጤናቸው ቢሆንስ?

ሚድያው የግለሰቧን መልሶች ሰምቶ ሚዛናዊ ዘገባ ከመስራት ይልቅ አስከፊ ሀገራዊ ሁኔታችንን ለመሸፈን በሚመስል መልኩ ሌላ የዘቀጠ ዘገባ መስራቱ እንደ ኢቲቪ ያሉ ተቋማት ያሉበትን ደረጃ የሚያሳዩ ናቸው።

ምንጭ: ሙሉቃል ቃል

እኔም እላለሁ፣ Fact Check ማለት አንድን አካል ብቻ ሳይሆን ለምሳሌ ግለሰቧን፣ የህክምና ማስረጃ ካላት እሱን፣ የትምህርት ማስረጃዎቿን፣ ዩኒቨርስቲውን... በማናገር መረጃዎችን አመሳክሮ የሚሰራ እንጂ ግለሰቦችን ለማጥቃት ወይም የተቋማትን ስም ለመገንባት የሚከናወን ስራ አይደለም።

*ግለሰቧ የምትገኝበትን ስልክ ወይም አድራሻ የሚያውቅ ካለ በኮመንት ወይም ቴሌግራም ላይ @ContactElias ላኩልኝ።

@EliasMeseret