Get Mystery Box with random crypto!

ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ dwamharic_news — ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ dwamharic_news — ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @dwamharic_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 2.98K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል
DW AMHARIC NEWS IS A GLOBAL NEWS AND INFORMATION CHANNEL FROM A GERMAN INTERNATIONAL BROADCASTER DEUTSCHE WELLE (DW)
Contact @DWCOMMENTBOT

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-20 13:51:07
በጋምቤላ ከተማ ተደንግጎ የነበረው ሰዓት እላፊ ተነሳ
በጋምቤላ ከተማ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሕገወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር በሚል የተደነገገው ሰዓት እላፊ ተነሳ። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ እንዳስታወቀው በከተማው ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 እንዲፀና የተደነገገው ሰዓት እላፊ ዛሬ ሙሉ በሙሉ ተነስቷል። በሰዓት እላፊው ገደብ መሠረት ከአምቡላንስና ከፀጥታ ኃይል ተሽከርካሪ በስተቀር ማንኛውም ተሽከርካሪና ሰዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ከንጋቱ 11፡30 እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ነበር። የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ፣ከዚህ ቀደም ኦነግ ሸኔና ጋኽነግ በከፈቱት ጥቃት የከተማይቱ ሰላም መድፍረሱን አስታውሰው በክልሉ አንጻራዊ ያሉት ሰላም ከመጣ በኋላ ተቆርጦ የቀረ የጠላት ኃይል ሲሉ የጠቀሱት ላይ አሰሳ ለማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን ተናግረዋል።ይሁንና «አሁን በከተማይቱ ያለው የፀጥታ ኅይል በቂ በመሆኑ፣ በተለያዩ የልማት ስራዎች የሚሳተፉ ድርጅቶች እንቅስቃሴም በሰዓት እላፊው በመገደቡና የከተማይቱ የአምቡላንስ አገልግሎት በቂ ባለመሆኑ ገደቡ እንዲነሳ ተደርጓል ብለዋል። ክልሉ ሰላም ነው ያሉት ሃላፊው ያም ሆኖ ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።
670 views10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 13:51:07
ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚደራደር ቡድን መሰየሙን በዚህ ሳምንት ያሳወቀው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)«ማናቸውም ንግግር በሰላም ጥረቶች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የነበራቸውን የኬንያውን ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታን ማካተት አለበት» ብሏል። የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ «የድርድሩን ሂደት በሙሉ ለአፍሪቃ ኅብረት መስጠት ለኛ በጣም ሃላፊነት የጎደለው ነው የሚሆነው» ሲሉ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ሁለቱን ወገኖች በተናጠል ሲያነጋግሩ የነበሩት የአፍሪቃ ኅብረት ልዩ ልዑክ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ለኢትዮጵያ መንግሥት ቅርበት አላቸው የሚለው ህወሓት ድርድሩ በኬንያታ አስተባባሪነት እንዲካሄድ እንደሚፈልግ ከዚህ ቀደምም አስታውቆ ነበር። የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ብልጽግና ግን ማናቸውም ድርድሮች በአፍሪቃ ኅብረት ብቻ ነው ሊመሩ የሚችሉት ብሏል። ከህወሓት ጋር ለሚደረገው ድርድር የመንግሥት ተደራዳሪ ኮሚቴ ሥራ መጀመሩን ባለፈው ሳምንት ተናግሯል።ለትግራዩ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ የሚደረገው ጥረት እንዲሰምር ከሁለቱ ወገኖች ምን ይጠበቃል ?ሃሳባችሁን አካፍሉን ፤ ተወያዩበት
714 views10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:20:44 የረቡዕ ሐምሌ 6 ቀን 2014 ዓም ዐርዕስተ ዜና
የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ብልጽግና ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)ጋር እንዲደራደር የሰየመው ሰባት አባላት ያሉት «የሰላም አማራጭ ዓቢይ ኮሚቴ» ስራ ጀመረ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪና የኮሚቴው አባል ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ኮሚቴው ትናንት ባካሄደው የመጀመሪያ ስብሰባው በንዑሳን ኮሚቴዎች በመደራጃት ኃላፊነት ተከፋፍሎ ስራውን ጀምሯል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሃላፊ አቶ ምትኩ ካሳ ታሰሩ። የፌደራል ፖሊስ የሙስና ወንጀሎች መርማሪ ቢሮና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዳለው ከሰባት ዓመት አንስቶ ኮሚሽኑን ሲመሩ የቆዩት አቶ ምትኩ የታሰሩት በሙስና ተጠርጥረው ነው።

በተቃዋሚዎች ግፊት ዛሬ ከሥልጣን ይለቃሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት የሲሪ ላንካ ፕሬዝዳንት ጎታባያ ራጃፓካሳ ከሸሹበት ከማልዲቪስ ወደ ሲንጋፖር ሊሄዱ ነው ተባለ። ፕሬዝዳንቱ በሌሉበት ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አድርገው መሰየማቸውም ዛሬ ህዝባዊውን ተቃውሞ አባብሷል። ተቃዋሚዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቢሮ ጥሰው ገብተዋል። ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4E5Sw?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwcommentbot
1.1K views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:09:11
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ከትናንት ጀምሮ በታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭቶች መፈጠራቸውን፤ ሕይወት መጥፋቱን እና ንብረት መውደሙን የአካባቢው ነዋሪ ለዶይቼ ቬሌ ማምሻውን ተናገሩ። ታጣቂዎቹ በወረዳው ሞላሌ ወደምትባል መንደር ገብተው መውጣታቸውንና አሁን ወደ ሌሎች ቀበሌዎች መሸሻቸውንም እኚሁ የዓይን እማኝ አመልክተዋል። ግጭቱ የተከሰተው ከአጣዬ ከተማ በቅርብ ርቀት ባሉ ቀበሌዎች ነው። የአካባበው ነዋሪዎች ጥቃቱን የከፈተው መንግሥት «ኦነግ ሸኔ» የሚለው ታጣቂ ኃይል ነው ይላሉ። የባሕር ዳር ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ወረዳው አስተዳዳሪም ሆነ ወደ ዞኑ ፀጥታ ኃላፊ ስልክ ቢደውልም እንዳልተሳካለት አመልክቷል።
1.1K views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:09:11
የዓለም የጤና ድርጅት ናይሪቢ ኬንያ ላይ ለአስቸኳይ አገልግሎት የሚውል የጤና ማዕከል ከፈተ። እንደ የድርጅቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገለጻ ማዕከሉ በጤናው ዘርፍ ያለውን አቅም በማጠናከር በመላው አፍሪቃ አስተማማኝ የመድኃኒት እና የህክምና መሳሪዎች ክምችት እንዲኖር ያስችላል። ቅዳሜ ዕለት በዓለም የጤና ድርጅት እና በኬንያ መንግሥት ትብብር የተከፈተው የጤና ማዕከል በአህጉሩ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚውል በአፍሪቃ ሃገራት የተዘረጋ የመጀመሪያው የግንኙነት መስመር መሆኑ ተገልጿል። ማዕከሉ በውስጡ ራሱን የቻለ የስልጠና ማዕከል፤ ለደረሰ አስቸኳይ የጤና ችግር በ24 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ መስጠት ለሚችሉ ባለሙያዎች መኖሪያ ቤት እንዲሁም የህክምና መሳሪያዎች ማከማቻ ስፍራ ይኖረዋል ተብሏል። የዓለም የጤና ድርጅት እንዲህ ያለውን ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የባለሙያዎች ቡድን በሁሉም የአፍሪቃ ሃገራት ለመፍጠር የመርዳት ፍላጎት እንዳለው አመልክቷል። የድርጅቱ የአፍሪቃ ዳይሬክተር ማቲዲሶ ሞኢቲ ለሮይተር እንደገለጹት «አህጉሩ ለቀጣዩ ወረርሽኝ የተሻለ ዝግጁ ለመሆን ያለውን ተግባራዊ ቁርጠኝነት እየገለጸ ነው፤ ይኽ ደግሞ የበለጠ ዝግጁ ሆነው ማላሽ መስጠት እንዲችሉ አቅማቸውን ለማጎልበት በእኛ በኩል የሚደረግ ድጋፍ ነው» ብለዋል። በዚህ መሠረትም አሁን ኬንያ ለአፍሪቃ የህክምና መሳሪያ ማዕከል መሆኗ አጎራባች ሃገራት መድኃኒቶችን በፍጥነት ለማግኘት እንዲችሉ እንደሚረዳ ተገልጿል።
885 views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:09:11
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ ከተማ አሶሳ የሰዓት እላፊ ገደብ ባለፈው ሳምንት ዓርብ ከተጣለ አንስቶ በቀን ከ30 እስከ 40 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ጉዳያቸው እየታየ እንደሚገኝ የከተማው አስተዳደር ፖሊስ መመሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ቡሽራ አልቀሪብ በድምበር አካባቢ ከሱዳን እና ከአጎራባች ክልል ቤጊ እና ቆንዳላ የተባሉ ወረዳዎች በርከት ያሉ ሰዎች ወደ ከተማ እና ወደ ዞን ወረዳዎች መፍለሳቸውን ለዶቼ ቬለ (DW) ገልጸዋል። ባለሥልጣኑ የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለበት ምክንያት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በድንበር አካባቢ በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ ጊዜን የተባለ ስፍራና መንጌ የተባለ ወረዳ የጸጥታ ችግር እንደነበርና እና ሌሎችም አካባቢዎች የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች በከተማው እንዳይከሰቱ ቀድሞ ለመከላከል ያለመ መሆኑንም አመልክተዋል። በአካባቢው የተለያዩ ዝርፍያዎች እና ግድያዎችም በመታየታቸው መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ባለሥልጣኑ እንደገለጹትም የሰዓት እላፊው ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ ነው። በተለያዩ ስፍራዎች ሁከት ለመቀስቀስ አልመው የሚንቀሳቀሱ ያሏቸውን ኃይሎችን ለመቆጣጠርም የሰዓት እላፊ ገደቡ ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚቆይም አመልክተዋል።
679 views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:09:11
የአውሮጳ ሃገራት ሕገወጥ ሰው አሸጋጋሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው። ጀርመን ባለፈው ሳምንት በርከት ያሉ ሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር አውላለች። ባለፈው ሳምንት አውሮጳ ውስጥ በተለይ ሕገ ወጥ የሰዎች ሽግግር የሚያከናውኑ በተበራከቱባቸው በአምስት ሃገራት ምርመራ ማካሄዱን ዩሮፖል አስታውቋል። በዚህም 39 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል። ከመካከላቸው ሦስቱ ዋነኛ አቀነባባሪዎች መሆናቸውንም ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ በሙሉ የኢራቅ ዜጎች መሆናቸውን የጀርመን የዜና ወኪል ዲፒኤ ገልጿል። 18ቱ የተያዙት በቤልጅየም መንግሥት ጥያቄ ሲሆን ተላልፈው እንዲሰጧትም ጠይቃለች። ፈረንሳይም በበኩሏ ከሕገወጥ አሸጋጋሪዎቹ ተላልፈው ይሰጡኝ ያለቻቸው አሉ። የጀርመኗ ኦስናብሩክ ከተማ አቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ በዛሬው ዕለት እንደገለጹት ተፈላጊዎቹ ተጠርጣሪዎች ወደ የት ይላኩ የሚለው በውሳኔ ሂደት ላይ ነው። የተደራጁት በሕገወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች ከጎርጎሪዮሳዊው 2021 አንስቶ ባሉት ጊዜያት 10,000 ገደማ ሰዎችን በእንግሊዝ ሰርጥ በኩል ወደ ብሪታንያ በፕላስቲክ ጀልባ አስገብተዋል ተብሏል። ይፋ በሆነው መረጃ መሰረትም ወደ ብሪታንያ በሕገወጥ መንገድ ከገቡት አብዛኞቹ የቪየትናም ዜጎች ናቸው። የጀርመን የዜና ወኪል የጠቀሰው የፖሊስ የውስጥ መረጃ እንደሚለው ጀርመን ውስጥ በተካሄደው አሰሳ በርካታ ገንዘብ እና የጦር መሣሪያ ተገኝቷል። የፕላስቲክ ጀልባዎች እና በርካታ ሞተሮችም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ጀርመን ውስጥ የተካሄደው አሰሳ ኦስናብሩክ እና ኖርድ ራይን ቬስትፋለን የሚካሄደውን ሕገወጥ የሰው ዝውውር መረጃ ያደረገ ነውም ተብሏል። እስካሁን በተገኘው መረጃ መሰረትም ጀርመን ውስጥ የሚንቀሳቀሰው የሕገወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች ቡድን ጀልባዎች እና ሞተሮችን የማቅረብ ኃላፊነት የያዘ መሆኑ ተደርሶበታል።
590 views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:09:11
... በተለያዩ ክልሎች የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን መንግሥት ማስቆም አልቻለም ያሉ 10 ሲቪክ ማሕበራት ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲያስቆሙ ጠየቁ። ማሕበራቱ በደብዳቤው ባለፉት 4 ዓመታት ጥቃቶቹ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በኦሮሚያ ክልሎች መፈጸማቸውን አመልክተዋል።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ሰኔ 11፤2014፤ 338 ሰዎች መገደላቸውን መንግሥት አስታወቋል። የአማራ ማህበር በአሜሪካ በበኩሉ ከ500 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ ማረጋገጡን ገልጿል። ከቀናት በኋላም በቄለም ወለጋ መንገድ ሃያና ሮቢት ገበያ በተባሉ መንደሮች «ኦነግ ሸኔ» በተባለው ቡድን ታጣቂዎች ግድያ መፈጸሙን በርካቶች መፈናቀላቸውን፤ 50 የሚሆኑ ደግሞ ታፍነው መወሳደቸውን ደብዳቤው ዘርዝሯል።
ደብዳቤው «የአማራ ተወላጆች ጅምላ ግድያ» ያለው ተግባር በጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ አስተዳደርም ሆነ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት ተነፍጎታል ሲል ይወቅሳል። የሸዋ ልማትና ሰላም ማሕበር በጎ ፈቃደኛ ሥራ አስኪያጅ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው፤ «የአማራ ክልል መንግሥት ከክልሉ ውጪ ያሉ አማሮችን ደህንነትና ሰላም ለማስጠበቅ ጠንካራ አቋምና ተቆርቋሪነት አያሳይም» ብለዋል።
የተባበሩት አማራ የበጎ አድራጎትና ልማት ማሕበር ፕሬዝደንት ረዳት ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያበይን በበኩላቸው ደብዳቤው የተላከው «ችግሮች ከዛሬ ነገ ይሻሻላሉ የሚል እሳቤ ቢኖርም እየባሰ በመሄዱ» እንደሆነ ገልጸዋል። የተጻፈውም፣ ለተመድ የፀጥታው ም/ቤት፣ ለተመ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ለተመድ ሰብአዊ መብት ጉባኤ፣ ለተመድ ሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፣ ለአፍሪካ እና ለአውሮጳ ሕብረት፣ ለአምነስቲ ኢንተረናሽናል፣ ለሂውማን ራይትስ ዎችና ለዓለም አቀፍ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ መሆኑን ዓለምነው መኮንን ከባሕር ዳር በላከው ዜና ጠቅሷል።
544 views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:09:11
የመላው ኢትዮጵያ አድንነት ድርጅት መኢአድ፣ እናት ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ኢህአፓ በዛሬው ዕለት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተገደሉ ወገኖችን በማሰብ የሕሊና ጸሎት እንዲደደረግ ጥሪ አቀረቡ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የመኢአድ የፋይናንስ እና አስተዳደር ክፍል ኃላፊ ዶክተር ታዲዮስ ቦጋለ ፓርቲያቸው «ከቀኑ ስድስት ሰዓት ተኩል ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የሚገኙ ጥሪውን የሰሙ ወገኖች በያሉበት በግፍ የተጨፈጨፉትን ዜጎች በጸሎት እንዲያስቡ መልእክት አስተላልፏል» ብለዋል። በዋናነት ዘርን መሠረት በማድረግ የጥቃት ሰለባ የሆኑ የአማራ ተወላጆች መሆናቸውን አጽንኦት የሰጡት ዶክተር ታዲዮስ ሆኖም ሌሎች ወገኖችም ዘራቸው ሳይጠቀስ እንዲህ ያለው የግፍ ጥቃት ሰለባዎች በመሆናቸው የሕሊና ጸሎቱ ሁሉንም የሚመለከት መሆኑንም አስረድተዋል።
ከዚህም ሌላ ከዛሬ ጀምሮ እነዚህ በገዛ ሀገራቸው በፈለጉበት ስፍራ በነጻነት እና በሰላም ሠርቶ የመኖር ዕድል የተነፈጉ ወገኖችን ጥቁር በመልበስ ለማሰብ መኢአድን ጨምሮ ሦስቱ ፓርቲዎች መልእክት ማስተላለፋቸውንም ገልጸዋል። በግፍ የተገደሉትን ዜጎች በአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት የማሰቡ ስርዓት ዛሬ ማለዳ ተካሒዷል። ዛሬ እኩለ ቀን ላይ የመኢአድ ፓርቲ መርሃ ግብር እንደሚቀጥል የገለጹት ዶክተር ታዲዮስ ማምሻውን በ12:30 ላይም እንዲሁ እንደሚደረግም ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። ...
548 views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:09:11
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አበባ ላይ ባለው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራዎች መዘግየት እንዳጋጠመው አመለከተ። አየር መንገዱ በፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው መልእክት በአየር ጠባይ ምክንያት ከአዲስ አበባ የሚነሱም ሆነ የሚያርፉ አውሮፕላኖች ለመዘግየት መገደዳቸውን ጠቅሶ መንገደኞችን ይቅርታ ጠይቋል። ዛሬ ጠዋት ከለንደን ወደ አዲስ አበባ የተጓዘ የኤርባስ A350-900 የመንገዶች አውሮፕላን በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ ምክንያት ሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ መገደዱን ተጓዦች በማኅበራዊ መገናኛ በቪዲዮ አስደግፈው እየገለጹ ነው። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከአምስት ዓመት በፊት ብዙም ያልተስተካከለ የነበረው የሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ዘንድሮ በተሻለ አቅም ላይ በመሆኑ ትላልቅ አውሮፕላኖች የሚያርፉበት ለመሆን ደርሷል።
596 views16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ