Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አበባ ላይ ባለው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት በቦሌ አውሮፕላን | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አበባ ላይ ባለው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራዎች መዘግየት እንዳጋጠመው አመለከተ። አየር መንገዱ በፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው መልእክት በአየር ጠባይ ምክንያት ከአዲስ አበባ የሚነሱም ሆነ የሚያርፉ አውሮፕላኖች ለመዘግየት መገደዳቸውን ጠቅሶ መንገደኞችን ይቅርታ ጠይቋል። ዛሬ ጠዋት ከለንደን ወደ አዲስ አበባ የተጓዘ የኤርባስ A350-900 የመንገዶች አውሮፕላን በአስቸጋሪው የአየር ሁኔታ ምክንያት ሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ መገደዱን ተጓዦች በማኅበራዊ መገናኛ በቪዲዮ አስደግፈው እየገለጹ ነው። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከአምስት ዓመት በፊት ብዙም ያልተስተካከለ የነበረው የሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ዘንድሮ በተሻለ አቅም ላይ በመሆኑ ትላልቅ አውሮፕላኖች የሚያርፉበት ለመሆን ደርሷል።