Get Mystery Box with random crypto!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤት ግንባታ አስጀመሩ። ቀዳማዊት እመቤት | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤት ግንባታ አስጀመሩ።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ ለገጣፎ አካባቢ በሚገኘው ዲቦራ ፋዉንዴሽን ማእከል የአእምሮ ዉስንነት ላለባቸዉ ህጻናት እና ወጣቶች አገልግሎት የሚዉል ትምህርት ቤት ለመገንባት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በአይምሮ ጤና እንክብካቤ እና ደህንነት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ያስታወቀ ሲሆን ለዚህ ግንባታም 19 ሚሊዩን ብር መመደቡን ገልጿል።

የግንባታ ወጪው የተሸፈነውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለትምህርት ቤቶች ግንባታ ከሰጡት የመደመር መጽሀፍ ሽያጭ ላይ መሆኑን ጽ/ቤቱ ጠቅሷል፡፡

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot