Get Mystery Box with random crypto!

'...የአገሪቱ ጦር የሕዝቡን ፍላጎት ቀልብሶ ስልጣን መቆጣጠሩ አግባብ አይደለም' - ፕሬዝዳንት ጆ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

"...የአገሪቱ ጦር የሕዝቡን ፍላጎት ቀልብሶ ስልጣን መቆጣጠሩ አግባብ አይደለም" - ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

ትላንት የማይናማር ጦር መፈንቅለ መንግሥት ማድረጉን ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶ ባይደን በማይናማር ላይ ማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

ፕሬዝደንት ባይደን ባወጡት መግለጫ የአገሪቱ ጦር የሕዝቡን ፍላጎት ቀልብሶ ስልጣን መቆጣጠሩ አግባብ አይደለም ብለዋል።

ባይደን፤ “በየትኛውም ስፍራ በዲሞክራሲ ላይ ጥቃት ሲደርስ አሜሪካ ወደጎን አትልም” ሲሉ ገልፀዋል።

በቀድሞዋ በርማ በዛሬዋ ስሟ ማይናማር የነበረውን አምባገነናዊ ወታደራዊ መንግሥት ተከትሎ በአሜሪካ ለረዥም ጊዜ ማዕቀብ ተጥሎ ቆይቶ ነበር።

አሜሪካ ከ10 ዓመታት በላይ በበርማ ላይ ጥላ የነበረውን ማዕቀብ ያነሳችው አገሪቱ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሸጋገሯን ተከትሎ መሆኑን ባይደን አስታውሰዋል። (BBC)

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot