Get Mystery Box with random crypto!

የማይስ ኢትዮጵያ ዘርፍ መለያ ዓርማ ይፋ ይደረጋል። በጉባዔዎቾ፣ ስብሰባዎችና ዐውደ ርዕዮች ሁነቶ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

የማይስ ኢትዮጵያ ዘርፍ መለያ ዓርማ ይፋ ይደረጋል።

በጉባዔዎቾ፣ ስብሰባዎችና ዐውደ ርዕዮች ሁነቶችን ያካተተው የማይስ ኢትዮጵያ ዘርፍ መለያ ዓርማ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛውን የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ይፋ ይደረጋል።

ማይስ ኢትዮጵያ ጉባዔዎች፣ የጉዞ ማበረታቻዎች፣ ኮንፈረንስና የኢግዚቢሽንን ሁነቶችን ያካተተ የቱሪዝም ዘርፍ ሲሆን ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ተቋማት መገኛና ሁነቶችን አስተናጋጅ በመሆኗ ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን አቅዳለች።

በዚህም እንግዶችን ለመቀበልና ሁነቶች እንዲከናወኑ አጋር አካላትን በማስተባበር ዘርፉን የሚመራ በቱሪዝም ኢትዮጵያ ስር የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ የተሸኘ ተቋም ተመስርቷል። ተቋሙም "በምድረ ቀደምት እንገናኝ" የሚል መሪ ቃል እንደሚኖረው ተገልጿል። (ENA)
@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot