Get Mystery Box with random crypto!

የመላው ኢትዮጵያ አድንነት ድርጅት መኢአድ፣ እናት ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ኢ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

የመላው ኢትዮጵያ አድንነት ድርጅት መኢአድ፣ እናት ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ኢህአፓ በዛሬው ዕለት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተገደሉ ወገኖችን በማሰብ የሕሊና ጸሎት እንዲደደረግ ጥሪ አቀረቡ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የመኢአድ የፋይናንስ እና አስተዳደር ክፍል ኃላፊ ዶክተር ታዲዮስ ቦጋለ ፓርቲያቸው «ከቀኑ ስድስት ሰዓት ተኩል ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የሚገኙ ጥሪውን የሰሙ ወገኖች በያሉበት በግፍ የተጨፈጨፉትን ዜጎች በጸሎት እንዲያስቡ መልእክት አስተላልፏል» ብለዋል። በዋናነት ዘርን መሠረት በማድረግ የጥቃት ሰለባ የሆኑ የአማራ ተወላጆች መሆናቸውን አጽንኦት የሰጡት ዶክተር ታዲዮስ ሆኖም ሌሎች ወገኖችም ዘራቸው ሳይጠቀስ እንዲህ ያለው የግፍ ጥቃት ሰለባዎች በመሆናቸው የሕሊና ጸሎቱ ሁሉንም የሚመለከት መሆኑንም አስረድተዋል።
ከዚህም ሌላ ከዛሬ ጀምሮ እነዚህ በገዛ ሀገራቸው በፈለጉበት ስፍራ በነጻነት እና በሰላም ሠርቶ የመኖር ዕድል የተነፈጉ ወገኖችን ጥቁር በመልበስ ለማሰብ መኢአድን ጨምሮ ሦስቱ ፓርቲዎች መልእክት ማስተላለፋቸውንም ገልጸዋል። በግፍ የተገደሉትን ዜጎች በአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት የማሰቡ ስርዓት ዛሬ ማለዳ ተካሒዷል። ዛሬ እኩለ ቀን ላይ የመኢአድ ፓርቲ መርሃ ግብር እንደሚቀጥል የገለጹት ዶክተር ታዲዮስ ማምሻውን በ12:30 ላይም እንዲሁ እንደሚደረግም ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። ...