Get Mystery Box with random crypto!

የረቡዕ ሐምሌ 6 ቀን 2014 ዓም ዐርዕስተ ዜና የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ብልጽግና ከህዝባዊ ወያኔ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

የረቡዕ ሐምሌ 6 ቀን 2014 ዓም ዐርዕስተ ዜና
የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ብልጽግና ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)ጋር እንዲደራደር የሰየመው ሰባት አባላት ያሉት «የሰላም አማራጭ ዓቢይ ኮሚቴ» ስራ ጀመረ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪና የኮሚቴው አባል ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ኮሚቴው ትናንት ባካሄደው የመጀመሪያ ስብሰባው በንዑሳን ኮሚቴዎች በመደራጃት ኃላፊነት ተከፋፍሎ ስራውን ጀምሯል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሃላፊ አቶ ምትኩ ካሳ ታሰሩ። የፌደራል ፖሊስ የሙስና ወንጀሎች መርማሪ ቢሮና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እንዳለው ከሰባት ዓመት አንስቶ ኮሚሽኑን ሲመሩ የቆዩት አቶ ምትኩ የታሰሩት በሙስና ተጠርጥረው ነው።

በተቃዋሚዎች ግፊት ዛሬ ከሥልጣን ይለቃሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት የሲሪ ላንካ ፕሬዝዳንት ጎታባያ ራጃፓካሳ ከሸሹበት ከማልዲቪስ ወደ ሲንጋፖር ሊሄዱ ነው ተባለ። ፕሬዝዳንቱ በሌሉበት ጠቅላይ ሚኒስትራቸውን ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አድርገው መሰየማቸውም ዛሬ ህዝባዊውን ተቃውሞ አባብሷል። ተቃዋሚዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቢሮ ጥሰው ገብተዋል። ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4E5Sw?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwcommentbot