Get Mystery Box with random crypto!

ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚደራደር ቡድን መሰየሙን በዚህ ሳምንት ያሳወቀው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚደራደር ቡድን መሰየሙን በዚህ ሳምንት ያሳወቀው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)«ማናቸውም ንግግር በሰላም ጥረቶች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የነበራቸውን የኬንያውን ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታን ማካተት አለበት» ብሏል። የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ «የድርድሩን ሂደት በሙሉ ለአፍሪቃ ኅብረት መስጠት ለኛ በጣም ሃላፊነት የጎደለው ነው የሚሆነው» ሲሉ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ሁለቱን ወገኖች በተናጠል ሲያነጋግሩ የነበሩት የአፍሪቃ ኅብረት ልዩ ልዑክ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ለኢትዮጵያ መንግሥት ቅርበት አላቸው የሚለው ህወሓት ድርድሩ በኬንያታ አስተባባሪነት እንዲካሄድ እንደሚፈልግ ከዚህ ቀደምም አስታውቆ ነበር። የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ብልጽግና ግን ማናቸውም ድርድሮች በአፍሪቃ ኅብረት ብቻ ነው ሊመሩ የሚችሉት ብሏል። ከህወሓት ጋር ለሚደረገው ድርድር የመንግሥት ተደራዳሪ ኮሚቴ ሥራ መጀመሩን ባለፈው ሳምንት ተናግሯል።ለትግራዩ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ የሚደረገው ጥረት እንዲሰምር ከሁለቱ ወገኖች ምን ይጠበቃል ?ሃሳባችሁን አካፍሉን ፤ ተወያዩበት