Get Mystery Box with random crypto!

በጋምቤላ ከተማ ተደንግጎ የነበረው ሰዓት እላፊ ተነሳ በጋምቤላ ከተማ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሕገወ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

በጋምቤላ ከተማ ተደንግጎ የነበረው ሰዓት እላፊ ተነሳ
በጋምቤላ ከተማ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሕገወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር በሚል የተደነገገው ሰዓት እላፊ ተነሳ። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ እንዳስታወቀው በከተማው ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 እንዲፀና የተደነገገው ሰዓት እላፊ ዛሬ ሙሉ በሙሉ ተነስቷል። በሰዓት እላፊው ገደብ መሠረት ከአምቡላንስና ከፀጥታ ኃይል ተሽከርካሪ በስተቀር ማንኛውም ተሽከርካሪና ሰዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ከንጋቱ 11፡30 እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ነበር። የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ፣ከዚህ ቀደም ኦነግ ሸኔና ጋኽነግ በከፈቱት ጥቃት የከተማይቱ ሰላም መድፍረሱን አስታውሰው በክልሉ አንጻራዊ ያሉት ሰላም ከመጣ በኋላ ተቆርጦ የቀረ የጠላት ኃይል ሲሉ የጠቀሱት ላይ አሰሳ ለማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን ተናግረዋል።ይሁንና «አሁን በከተማይቱ ያለው የፀጥታ ኅይል በቂ በመሆኑ፣ በተለያዩ የልማት ስራዎች የሚሳተፉ ድርጅቶች እንቅስቃሴም በሰዓት እላፊው በመገደቡና የከተማይቱ የአምቡላንስ አገልግሎት በቂ ባለመሆኑ ገደቡ እንዲነሳ ተደርጓል ብለዋል። ክልሉ ሰላም ነው ያሉት ሃላፊው ያም ሆኖ ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።