Get Mystery Box with random crypto!

ዋሽንግተን የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ዩናይትድ ስቴትስ በመጪው ዓመት ከ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

ዋሽንግተን የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ

ዩናይትድ ስቴትስ በመጪው ዓመት ከአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች ጋር ጉባኤ ለማካሄድ ማቀዷን አስታወቀች።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በታህሳስ ወር ሊካሄድ የታቀደው ይኽው ጉባኤ፣ዩናይትድ ስቴትስ አፍሪቃን ለመደገፍ ያላት ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለዋል። ታህሳስ አጋማሽ ላይ ዋሽግተን ዉስጥ ይካሄዳል የተባለው ጉባኤ ጉባኤ ከምግብ ዋስትና አንስቶ እስከ የአየር ንብረት ለውጥ ድረስ ባሉት ፈታኝ ችግሮች ላይ እንደሚወያይ ባይደን ጠቁመዋል። የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪቃ ግንኙነት አስፈላጊነት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚጋሯቸው፣ ቅድሚያ በሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ ትብብርን ማጠናከርም ጉባኤው አጽንኦት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ መሆኑን ፕሬዝደንቱ አስታውቀዋል።የአሜሪካን ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ማራኬሽ ሞሮኮ ውስጥ በተካሄደው በዩናይትድ ስቴትስ እና አፍሪቃ የንግድ ጉባኤ ላይ ባሰሙት ንግግር ጉባኤው እንደሚካሄድ አንስተው ነበር። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የዋሽንግተን አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣን እንዳሉት በእቅዱ መሠረት 50 የአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች በጉባኤው ላይ ይካፈላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ባይደን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ከሆኑ ወዲህ አፍሪቃ አልጎበኙም።የአሁኑ ባይደን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የምዕራቡን ዴሞክራሲ በማስተዋወቅ በአፍሪቃ ብዙ መዋዕለ ንዋይ ከወረተችው ከቻይና ጋር ለመስተካከል የሚደረግ ጥረት ተደርጎ ተወስዷል። ሆኖም ባለሥልጣኑ እንዳሉት የጉባኤው ትኩረት ይሄ አይደለም። «አፍሪቃውያን አጋሮቻችንን ከእኛና ከቻይና እንዲመርጡ አንጠይቃቸውም ሆኖም ዩናይትድ ስቴትስ የተሻለ ሞዴል ታቀርባለች» ብለዋል።