Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከንቲባ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ለሕግ እንዲቀርቡ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

የአዲስ አበባ ከንቲባ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ለሕግ እንዲቀርቡ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ ጠየቀ። "የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዥው ፓርቲ የሚፈጸሙበት የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውሶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፉ በመሄድ ላይ ይገኛሉ" ሲል በመግለጫው የተናገረው ፓርቲው "የከንቲባ አዳነች አበቤ አስተዳደር ከተማዋንም ሆነ አገሪቷን ወደ ቀውስ በፍጥነት እና በጥልቀት እየገፋት ይገኛል" ብሏል።

ፓርቲው ሰሞኑን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለባለ እድለኞች ለመስጠት በወጣው የተጭበረበረ ዕጣ የከተማዋ ከንቲባ "በድርጊቱ መሪ ተዋናይ እንደነበሩ በርካታ መረጃዎች ተገኝቶባቸዋል" ብሏል በመግለጫው፡፡ "በዚህ አውድ፣ ከንቲባዋን ትቶ ሌሎች የአዲስ አበባ አስተዳዳር ባለሥልጣናት እና ሙያተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ የፍትሕ ሥርዓቱን ባዶነት እና አድሎኝነት አጋልጧል" የሚለው ባልደራስ « የከንቲባዋ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ለተነሱባቸው ጥያቄዎች የከንቲባዋ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ለሕግ እንዲቀርቡ፣ የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ እንዳይሆን እና የኦሮሚያ ክልል ባንዲራና መዝሙር በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች እንዳይሰቀል እና እንዳይዘመር" ሲል ጠይቋል።
የከተማው ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር ሲሳይ መንግሥቴ ሰሞኑን በተከናወነው የምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ "ትምህርት ቤቶች ላይ የኦሮሚያ ባንዲራ ይውለብለብ አይውለብለብ በሚል ችግር ፈጥሯል፣ መዝሙሩ ይዘመር አይዘመር በሥርዓት ነው መወሰን ያለበት" በሚል ላቀረቡት ጥያቄ ከንቲባ አዳነች አቤቤ "የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለአዲስ አበባ በሚሆን መንገድ የአዲስ አበባ ተማሪዎች ኦሮሚኛን መማር የሚገባቸው በምን መልኩ ነው ለሚለው ካሪኩለም ቀርጿል። ኦሮምኛ መዘመራቸው ይቀጥላል ብለዋል።