Get Mystery Box with random crypto!

ካርቱም-በጎሳዎች ግጭት 105 ተገደሉ በሱዳን ደቡባዊ ግዛት ብሉናይል፣ በመሬት ይገባኛል ውዝግ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

ካርቱም-በጎሳዎች ግጭት 105 ተገደሉ
በሱዳን ደቡባዊ ግዛት ብሉናይል፣ በመሬት ይገባኛል ውዝግብ የዛሬ ዘጠኝ ቀን በተነሳ የጎሳ ግጭት 105 ሰዎች መገደላቸውንና 291 መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሱዳንን ከኢትዮጵያና ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስነው በዚሁ ግዛት ግጭቱ የተካሄደው በርታና ሀውሳ በተባሉ ጎሳዎች መካከል ነው። ከካርቱም 460 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ከግዛቲቱ ዋና ከተማ አል ደማዚን የጤና ሚኒስትሩ በስልክ እንደተናገሩት በአካባቢው ጦር ሠራዊት ከተሰማራበት ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ ግጭቱ ቀንሷል።የተመድ እንደሚለው በግጭቱ ምክንያት ከ17 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ከመካከላቸው 14 ሺዉ አል ደማዚን ውስጥ በሚገኙ ሦስት ትምሕርት ቤቶች ተጠልለዋል።የብሉ ናይሉ ግጭት የተቀሰቀሰው ሃውሳዎች የመሬት አጠቃቀምን በበላይነት የሚቆጣጠር የሲቪል አስተዳደር እንዲሆን ያቀረቡትን ጥያቄ በርታዎች ከተቃወሙ በኋላ ነው።አንድ የበርታ ከፍተኛ መሪ እንዳሉት ግን ግጭቱ የተነሳው ሃውሳዎች የመሬት ይዞታን ደንብ በመጣሳቸው ነው።