Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ከትናንት ጀምሮ በታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ከትናንት ጀምሮ በታጣቂዎች እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭቶች መፈጠራቸውን፤ ሕይወት መጥፋቱን እና ንብረት መውደሙን የአካባቢው ነዋሪ ለዶይቼ ቬሌ ማምሻውን ተናገሩ። ታጣቂዎቹ በወረዳው ሞላሌ ወደምትባል መንደር ገብተው መውጣታቸውንና አሁን ወደ ሌሎች ቀበሌዎች መሸሻቸውንም እኚሁ የዓይን እማኝ አመልክተዋል። ግጭቱ የተከሰተው ከአጣዬ ከተማ በቅርብ ርቀት ባሉ ቀበሌዎች ነው። የአካባበው ነዋሪዎች ጥቃቱን የከፈተው መንግሥት «ኦነግ ሸኔ» የሚለው ታጣቂ ኃይል ነው ይላሉ። የባሕር ዳር ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ወረዳው አስተዳዳሪም ሆነ ወደ ዞኑ ፀጥታ ኃላፊ ስልክ ቢደውልም እንዳልተሳካለት አመልክቷል።