Get Mystery Box with random crypto!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ ከተማ አሶሳ የሰዓት እላፊ ገደብ ባለፈው ሳምንት ዓርብ ከተጣለ አን | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ ከተማ አሶሳ የሰዓት እላፊ ገደብ ባለፈው ሳምንት ዓርብ ከተጣለ አንስቶ በቀን ከ30 እስከ 40 የሚደርሱ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ጉዳያቸው እየታየ እንደሚገኝ የከተማው አስተዳደር ፖሊስ መመሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ቡሽራ አልቀሪብ በድምበር አካባቢ ከሱዳን እና ከአጎራባች ክልል ቤጊ እና ቆንዳላ የተባሉ ወረዳዎች በርከት ያሉ ሰዎች ወደ ከተማ እና ወደ ዞን ወረዳዎች መፍለሳቸውን ለዶቼ ቬለ (DW) ገልጸዋል። ባለሥልጣኑ የሰዓት እላፊ ገደብ የተጣለበት ምክንያት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በድንበር አካባቢ በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ ጊዜን የተባለ ስፍራና መንጌ የተባለ ወረዳ የጸጥታ ችግር እንደነበርና እና ሌሎችም አካባቢዎች የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች በከተማው እንዳይከሰቱ ቀድሞ ለመከላከል ያለመ መሆኑንም አመልክተዋል። በአካባቢው የተለያዩ ዝርፍያዎች እና ግድያዎችም በመታየታቸው መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ባለሥልጣኑ እንደገለጹትም የሰዓት እላፊው ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ ነው። በተለያዩ ስፍራዎች ሁከት ለመቀስቀስ አልመው የሚንቀሳቀሱ ያሏቸውን ኃይሎችን ለመቆጣጠርም የሰዓት እላፊ ገደቡ ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚቆይም አመልክተዋል።