Get Mystery Box with random crypto!

ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ dwamharic_news — ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ dwamharic_news — ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @dwamharic_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 2.98K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል
DW AMHARIC NEWS IS A GLOBAL NEWS AND INFORMATION CHANNEL FROM A GERMAN INTERNATIONAL BROADCASTER DEUTSCHE WELLE (DW)
Contact @DWCOMMENTBOT

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2021-01-31 21:27:19
#Attention

ኮልፌ አጠና ተራ (እፎይታ አካባቢ) የተከሰተውን ከፍተኛ የእሳት አደጋ ተከትሎ በግርግሩ ሰዎች ላይ ዝርፊያ እየተፈፀመ መሆኑን የኮልፌ አጠና ተራ ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል። አባላቶቻችን የፌደራል የፀጥታ አካላት በቦታ እንዲሰማሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot
829 viewsedited  18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-31 10:34:18
"...የኮሮና ክትባት በሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ ይገባል" - ጤና ሚኒስቴር

የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት እስከ መጪው ሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባና 20 ከመቶ ለሚሆኑ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚዳረስ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የክትባት ስራውን የሚያስተባብር ግብረሃይል በብሄራዊ ደረጃ መቋቋሙ ተገልጿል።

በጤና ሚኒስቴር የክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች የሚኒስትሯ (ዶ/ር ሊያ ታደሰ) ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ሙሉቀን ዮሃንስ ፥ ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር እና ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ጋር በመቀናጀት የኮሮና መከላከያ ክትባትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

የእቅድ እና አጠቃላይ የዝግጅት ስራን በሚመለከት የክትባቱን ሥራ የሚያስተባብር ግብረሃይል ከልማት አጋር ድርጅቶች ፣ ከመንግስት ኤጀንሲዎች ፣ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተውጣጥቶ በብሔራዊ ደረጃ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡

Via EPA
@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot
1.0K viewsedited  07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-31 09:42:51
#MinistryofRevenues

በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ64 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል መድኃኒት፣ የምግብ ምርቶች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የትምባሆ ውጤቶች፣ አደንዛዥ ዕፆች እና የኤልክትሮኒክስ ዕቃዎች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot
904 viewsedited  06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 23:39:23
#update

ኢትዮጵያ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎቿን ከሳዑዲ አረቢያ እየመለሰች ትገኛለች።

ዛሬ 76 ህፃናትን ጨምሮ ሶስት መቶ አርባ አንድ ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ወደ አገር የተመለሱት ዜጎች ከህፃናት ውጭ ያሉት 265 ሴቶች መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot
905 viewsedited  20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 22:40:18
#Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,099
• በበሽታው የተያዙ - 656
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ - 601

አጠቃላይ 137,021 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ2,091 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 122,588 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

241 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot
897 viewsedited  19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 19:20:48
የአዲስ አበባ ካቢኔ ውሳኔ ፦

በአዲስ አበባ ለመምህራን ይከፈል የነበረውን የቤት አበል ከብር 850 ወደ ብር 3,000 እንዲሻሻል ወሰኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድሩ ካሁን በፊት በከተማው ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩ መምህራን 5,000 የመኖርያ ቤት አቅርቦ ነበር።

ለሁሉም መምህራን በፍጥነት ቤት ማዘጋጀት ባለመቻሉ ፤ ለሁሉም መምህራን 3000 የኢት ብር የቤት አበል ክፍያ እንዲከፈላቸው የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ዛሬ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

Via Addis Ababa Press Secretary
@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot
922 viewsedited  16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 17:59:05
መቀሌ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር መዘጋጀቱን አስታወቀ።

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ተቀብሎ መደበኛ የመማር ማስተማሩን ሥራ ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው የሚቀበላቸው ተማሪዎች ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ዓመት ድረስ የሚማሩ እንደሆነ ተመልክቷል።

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ከሰተ ለገሰ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው 13 ሺህ ተማሪዎችን ይቀበላል።

ተማሪዎችን ከአውቶቡስ መነኸሪያ እና መቀሌ ከተማ ተቀብለው ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማስገባት የተማሪዎች ህብረት አመራሮች ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው የሚቀበላቸው ተማሪዎች ያለምንም ችግር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የምግብ ፣ መኝታ ፣ መማሪያ ክፍሎች የኤሌክትሪክ መብራት እና የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት መሰናዳታቸውን ዶክተር ከሰተ አስታውቀዋል።

የጊቢው የማፅዳት ስራ መጠናቀቁን አመልክተው የመማር ማስተማር ስራው የሚካሄደው የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በሚያስችል መንገድ እንደሆነ አስረድተዋል።

ከሁሉም የሀገራችን ክልሎች ለሚመጡ ተማሪዎች ከጥር 28 እስከ 30/ 2013 ዓ.ምባሉት ቀናት ውስጥ የእንኳን ደህና መጣችሀ አቀባበል ይደረጋል ብለዋል።

ከአቀባበሉ በኋላ የመማር ማስተማሩ ሥራ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የመማሪ ማስተማር ስራ ሲጀመር በመልካም ሥነ-ምግባር ትምህርታቸውን መከታተል እንደሚጠበቅባቸውም አስታውቀዋል። (ENA)

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot
901 viewsedited  14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 17:58:47
በትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በደቡብ ጎንደር ዞን ሰዴ ሙጃ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት ማለፉን የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዋና ክፍል ገለፀ።

መነሻውን ከባሕር ዳር ያደረገው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ሰዴ ሙጃ ወረዳ ሲደርስ 200 ሜትር ከሚረዝም ገደል በመግባቱ ነው የ24 ሰዎች ህይወት ያለፈው።

በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በደብረ ታቦር እና በፈለገሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ አብመድ ዘግቧል።

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot
806 viewsedited  14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 17:36:34
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን አቃቂ ወረዳ ላይ በመስኖ የለማን የስንዴ ማሳን ጎብኝተዋል።

በኦሮሚያ ክልል በ130,000 ሄክታር መሬት ላይ የቆላ ስንዴን በመስኖ የማምረት ሥራ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት።

ይህም በ300,000 ሄክታር ላይ ሊከወን የታቀደው ሥራ አንድ አካል ነው ያሉ ሲሆን ከውጪ የሚገባን ስንዴም በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ያለንን ፍላጎት እና ዐቅም በተግባር ያሳያል ብለዋል።

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot
798 viewsedited  14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 17:36:34
757 views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ