Get Mystery Box with random crypto!

'...የኮሮና ክትባት በሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ ይገባል' - ጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

"...የኮሮና ክትባት በሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ ይገባል" - ጤና ሚኒስቴር

የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት እስከ መጪው ሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባና 20 ከመቶ ለሚሆኑ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚዳረስ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የክትባት ስራውን የሚያስተባብር ግብረሃይል በብሄራዊ ደረጃ መቋቋሙ ተገልጿል።

በጤና ሚኒስቴር የክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች የሚኒስትሯ (ዶ/ር ሊያ ታደሰ) ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ሙሉቀን ዮሃንስ ፥ ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር እና ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ጋር በመቀናጀት የኮሮና መከላከያ ክትባትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

የእቅድ እና አጠቃላይ የዝግጅት ስራን በሚመለከት የክትባቱን ሥራ የሚያስተባብር ግብረሃይል ከልማት አጋር ድርጅቶች ፣ ከመንግስት ኤጀንሲዎች ፣ ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተውጣጥቶ በብሔራዊ ደረጃ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡

Via EPA
@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot