Get Mystery Box with random crypto!

Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የሰርጥ አድራሻ: @ayuzehabeshaofficial
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 182.82K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2024-04-23 09:06:32
17.7K viewsAyu, 06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 09:05:53
ማስታወቂያ
ቁጠባ ከጀመሩ ከ10 ቀን ጀምሮ ብድር የሚያገኙበት ብቸኛ ተቋም

ግሎባል ቁጠባና ብድር

የስራ መኪና ግዥ እስከ ብር 3,000,000

50% የቆጠበ በ1 ወር ከ15 ቀን!
40% የቆጠበ በ2 ወር !
30% የቆጠበ በ2 ወር ከ15 ቀን!
25% የቆጠበ በ3 ወር የስራ መኪና ግዥ ብድር የሚያገኝ ይሆናል።

ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለኮንደሚኒዬም ቤት ቅድመ ክፍያና ሙሉ ክፍያ፣ ግዥ፣ ለስራ መነሻና ማስፋፊያ የሚሆን ብድር ቁጠባ ከጀመሩ ከ10 ቀን ጀምሮ እስከ ብር 6,000,000. ብድር አመቻችተናል።

የተቋሙ አባል በመሆንና ቁጠባ በመጀመር ራስዎንና ቤተሰብዎን ይጥቀሙ!!!

ግሎባል ቁጠባና ብድር ከኢቶፒካር አስመጭ ጋር በመተባበር!

አድራሻ:- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት ቅዱስ ፕላዛ 6ኛ ፎቅ!

#ስልክ ቁ.  0118-12-66-16
                  0956-23-24-25
                  0979-25-26-27

ወደ ቴሌ ግራም ገፃችን ለመግባት
https://t.me/globalsavingandcredit
21.0K viewsAyu, 06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 19:11:09
ውጥረቱ አሳስቦናል:- ኢምባሲዎች
መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች በሰሜን #ኢትዮጵያ የተፈጠረው ውጥረት አሳስቦናል ሲሉ ገለጹ
#የካናዳ፣ #ፈረንሳይ፣ #ጀርመን፣ #ጣሊያን፣ #ጃፓን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና #አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል “አጨቃጫቂ ቦታዎች” ሲሉ በገለጿቸው የደቡብ ትግራይ አከባቢዎች የተፈጠረው ውጥረት አስግቶናል ሲሉ ገለጹ።

ሁሉም አካላት ትጥቅ የማስፈታት፣ ተዋጊዎችን የመበተን እና መልሶ የማቋቋም እንዲሁም ተፈናቃዮችን በሰላማዊ መንገድ ወደ ቀያቸው የመመለስ ጥረት እንዲፋጥኑ ጠይቀዋል።

ሁኔታዎች እንዲረጋጉ እና ንጹሃንን ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የሚታየው ውስብስብ የፖለቲካ እና የጸጥታ ቀውስ መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለው እና ዘላቂ ሰላም የሚሰፍነው ሁሉን አቀፍ ንግግር በባለድርሻ አካላት መካከል ሲደረግ ብቻ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
@ayuzehabeshaofficial
26.3K viewsAyu, edited  16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 18:48:54
በመዲናዋ የሰራተኛ ምደባን በመቃወም ስራ ያልገቡ ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ቀረበ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተደረገውን የመንግስት ሰራተኞች ምዘና ተከትሎ የተከናወነውን የሰራተኛ ምደባ በመቃወምና በሌሎች ግላዊ የጥቅም ጥያቄዎች ምክንያት ስራ ያልገቡ ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ቢሮ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሰራተኞች ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት የስራ ድልድል መደረጉንና ሰራተኞች በተቻለ መጠን በሚኖሩበት ወረዳ እና ክፍለ ከተማ አካባቢ እንዲመደቡ መደረጉን የከተማዋ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ቢሮ የስራ አመራር ዘርፍ ሀላፊ አቶ መላኩ ጉራቻ ተናግረዋል፡

ምደባው ከተከናወነ በኋላ በሁሉም ክፍለ ከተማ አገልግሎቶች ሳይቋረጡ እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ በዚህ ሁኔታ ግን መመሪያውን በመቃወም እና በሌሎች ምክንያቶች ወደ ስራ ገበታቸው ያልተመለሱ ሰራተኞች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

አሁንም በምደባው ላይ ቅሬታ እየቀረበ በመሆኑ ወደ ስራ ገበታቸው ያልተመለሱ ሰራተኞችን ሙሉ ቁጥር አሁን ላይ ማወቅ እንደማይቻል አመላክተዋል፡፡

በስራ ምደባው 3ሺ 266 ሰራተኞች ከነበሩበት ደረጃ ዝቅ ሳይደረጉ፤ ወደ ሌላ ቦታ በማዘዋወር መመደባቸውን ሃላፊው አስታውቀዋል፡፡
@ayuzehabeshaofficial
26.2K viewsAyu, edited  15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 14:19:24
ወላይታ
የወላይታ ዞን ዳሞት ሶሬ ወረዳ ፖሊስ አባላት በጉሩሞ ላዲሳ 01 ቀበሌ አንዲት ወጣት ከቤተሰቦቿ ጋር ባለመግባባት በተፈጠረው ጭቅጭቅ ራሷን ለማጥፋት አቮካዶ ዛፍ ላይ ብትወጣም ፖሊሶች በደረሳቸው ጥቆማ ህይወቷን ታድገዋል። ከወጣችበት በሰላም አውርደዋታል።
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
16.8K viewsAyu, 11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 13:28:49 ከጅጅጋ የደረሰኝ ጥቆማ ነው
ሰላም አዩ ዛሬ ጠዋት አንድ አነስ ያለች ሱቅ እቃ ለመግዛት ጎራ ባልኩበት ስዓት ከብልፅግና ቢሮ ነው የመጣነው የሚሉ ሰዎች ከሱቁ መጡ እና የሱቁን ባለቤት 1000 እንድሰጣቸው ጠየቁት ፥የሱቁ ባለቤት የምን ብር ብሎ ጠየቀ የብልፅግና ድጋፍ ነው ተባለ፤ ባለቤቱም እንደሌለው እና እንደማይከፍል ነገራቸው ፥እነሱም ካልከፈልክ ብለው  አሸጉት።
የሱቁም ባለቤት የሄዱ መስሎት የታሸገውን ከፈተው ነገር ግን ሰዎቹ አድፍጠው ይመለከቱ ስለነበር ወዳው መጡና ወደ ቀበሌ ለመውሰድ ሞከሩ ሰውየውም አልሄድም እያለ ጭቅጭቅ ተነሳ እና የሱቁ አከራይ ከሰወቹ ጋር በመደራደር 600 ብር ሰጥቷቸው ከዚያ ሄዱ።
ይህን አይነት መርህ እና ህግ አልባ የሆኑ ስራዎች በጅግጅጋ ከተማ ተደጋጋሚ ተግባራት ሆነዋል፤ ህዝቡም እየተማረረ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ሰሞኑን የታቤላ ብለው 2000ብር በፎጅድ ደረሠኝ አሰየተቀበሉ ነው፣በተለይ ሀበሻ ብለው በሚያስቡት ሰው ላይ ነው ይሄን የሚፈፅሙት።
ይሄ ነገር መስተካከል አለበት።

ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
17.6K viewsAyu, edited  10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 12:28:15
በመጪው ሰኔ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የአገልግሎት 500 ብር የመክፈል እና ደረሰኝ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በደብዳቤ ማሳወቁን ተመልክቻለሁ።
አዩዘሀበሻ
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
18.2K viewsAyu, 09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 12:21:13
የመውጫ ፈተና መቼ ይሰጣል
ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ አሳውቋል።
አዩዘሀበሻ
ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
17.1K viewsAyu, edited  09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 12:20:58
ማስታወቂያ #የቻናል_ጥቆማ
ለኢንጅነሮች ተማሪዎች እናconstruction ዘርፍ ለይ ለተሰማሩት ሁሉ

የኮንስትራክሽ፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ አርክቴክቸር
      ተማሪ ነዎት?
በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት?
በአማርኛ እና እንግሊዘኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መፅሀፍቶች፣ ቪድዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን እውቀቶች ለማግኝት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣
የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣
እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣
በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት

እንግዲያውስ ለርስዎ የሚሆን ምርጥ እና ጠቃሚ  ቻናል እንጠቁመዎት

Join us :-

on Telegram

https://t.me/ethioengineers1
https://t.me/ethioengineers1

on tiktok

tiktok.com/@ethiocons
tiktok.com/@ethiocons
16.1K viewsAyu, 09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 11:48:03
ከቴሌ እውቅና ውጪ ሕገ-ወጥ የስልክ መስመሮችን ሲጠቀሙ ነበር የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሐረሪ ክልል ጄኔላ ወረዳ ሕገ-ወጥ የስልክ መስመሮችን ከቴሌ እውቅና ውጪ ሲጠቀሙ ነበር የተባሉ 4 ግለሰቦች ከነ እቃው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎች በድብቅ ከቴሌ እውቅና ውጪ የስልክ መስመሮችን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ወደ ውጪ ሀገራት በማስደወል ሕገ-ወጥ አገልግሎት ሲሰጡ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጄኔላ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መፍቱህ ከድር ተናግረዋል፡።

በሕገወጥ መንገድ አገልግሎት ይሰጥ የነበረው የስልክ መስመር የመንግስትን ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳና በቴሌ አገልግሎት ላይ ኪሳራ የሚያስከትል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ተጠርጣሪዎች በድብቅ ግለሰቦችን ወደ ውጪ ሀገራት በከፍተኛ ገንዘብ በማስደወል የግል ጥቅማቸውን በሕገ-ወጥ መንገድ ያገኙ እንደነበር የክልሉ ፖሊስ መረጃ አመልክቷል፡፡
በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር የገባ ባለ አንቴና የስልክ ማሽን፣ ብዛት ያላቸው ሲም ካርዶች፣ ሞባይሎች፣ የዋይፋይ ሳጥኖች፣ የተለያዩ ኬብሎች፣ ፍላሾችና አንቴና መያዛቸውም ተጠቅሷል፡፡
#FBC
መረጃ ለማድረስ እንዲሁም ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይፃፉልን
http://t.me/ayulaw
17.4K viewsAyu, 08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ