Get Mystery Box with random crypto!

ውጥረቱ አሳስቦናል:- ኢምባሲዎች መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች በሰ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

ውጥረቱ አሳስቦናል:- ኢምባሲዎች
መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች በሰሜን #ኢትዮጵያ የተፈጠረው ውጥረት አሳስቦናል ሲሉ ገለጹ
#የካናዳ፣ #ፈረንሳይ፣ #ጀርመን፣ #ጣሊያን፣ #ጃፓን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና #አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል “አጨቃጫቂ ቦታዎች” ሲሉ በገለጿቸው የደቡብ ትግራይ አከባቢዎች የተፈጠረው ውጥረት አስግቶናል ሲሉ ገለጹ።

ሁሉም አካላት ትጥቅ የማስፈታት፣ ተዋጊዎችን የመበተን እና መልሶ የማቋቋም እንዲሁም ተፈናቃዮችን በሰላማዊ መንገድ ወደ ቀያቸው የመመለስ ጥረት እንዲፋጥኑ ጠይቀዋል።

ሁኔታዎች እንዲረጋጉ እና ንጹሃንን ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የሚታየው ውስብስብ የፖለቲካ እና የጸጥታ ቀውስ መፍትሔ ሊያገኝ የሚችለው እና ዘላቂ ሰላም የሚሰፍነው ሁሉን አቀፍ ንግግር በባለድርሻ አካላት መካከል ሲደረግ ብቻ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
@ayuzehabeshaofficial