Get Mystery Box with random crypto!

ከጅጅጋ የደረሰኝ ጥቆማ ነው ሰላም አዩ ዛሬ ጠዋት አንድ አነስ ያለች ሱቅ እቃ ለመግዛት ጎራ ባ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

ከጅጅጋ የደረሰኝ ጥቆማ ነው
ሰላም አዩ ዛሬ ጠዋት አንድ አነስ ያለች ሱቅ እቃ ለመግዛት ጎራ ባልኩበት ስዓት ከብልፅግና ቢሮ ነው የመጣነው የሚሉ ሰዎች ከሱቁ መጡ እና የሱቁን ባለቤት 1000 እንድሰጣቸው ጠየቁት ፥የሱቁ ባለቤት የምን ብር ብሎ ጠየቀ የብልፅግና ድጋፍ ነው ተባለ፤ ባለቤቱም እንደሌለው እና እንደማይከፍል ነገራቸው ፥እነሱም ካልከፈልክ ብለው  አሸጉት።
የሱቁም ባለቤት የሄዱ መስሎት የታሸገውን ከፈተው ነገር ግን ሰዎቹ አድፍጠው ይመለከቱ ስለነበር ወዳው መጡና ወደ ቀበሌ ለመውሰድ ሞከሩ ሰውየውም አልሄድም እያለ ጭቅጭቅ ተነሳ እና የሱቁ አከራይ ከሰወቹ ጋር በመደራደር 600 ብር ሰጥቷቸው ከዚያ ሄዱ።
ይህን አይነት መርህ እና ህግ አልባ የሆኑ ስራዎች በጅግጅጋ ከተማ ተደጋጋሚ ተግባራት ሆነዋል፤ ህዝቡም እየተማረረ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ሰሞኑን የታቤላ ብለው 2000ብር በፎጅድ ደረሠኝ አሰየተቀበሉ ነው፣በተለይ ሀበሻ ብለው በሚያስቡት ሰው ላይ ነው ይሄን የሚፈፅሙት።
ይሄ ነገር መስተካከል አለበት።

ተጨማሪ መረጃዎች እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial