Get Mystery Box with random crypto!

Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የሰርጥ አድራሻ: @ayuzehabeshaofficial
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 181.69K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-04-25 13:32:29 ማስታወቂያ
አያት ( ዞን 2 ፣ 3፣ 8) የሚገኙ የአያት አክሲዮን ማህበር ቤቶች መረጃ
የመኖሪያ ቤቶቹ ስፋት
- ባለ 2 መኝታ   80፣ 85፣ 90 ፣ 95 እና
- ባለ 3 መኝታ   107፣ 110 ፣ 115 ፣ 120፣ 127 ፣ 138 እና 145

አብዛኞቹ 3 መኝታ ያላቸው የመኖሪያ ቤቶች ተጨማሪ የሰራተኛ ክፋል አላቸው።

ዋጋ:
102, 258 ብር እስከ 114,839 ብር / በካሬ እንደ ግንባታ ዓይነቱ (በከፊል /በሙሉ ግንባታ) እና ቤቱ እንደሚገኝበት የወለል መጠን የሚወሰን ሲሆን :

አከፋፈል

በ15% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤትነትን እድል የፈጠረ ! ቀሪው እንደ ውለታው/ ስምምነቱ መሰረት የግንባታው ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ተከትሎ የሚከፈል ይሆናል።

60% በ 7 ዙር  40% ቱን ቤትዎን ተረክበው እየኖሩበት ከ 15-30 ዓመታት በሚከፈል ብድር (በ9.5% ወለድ) የዱቤ አማራጭ ያመቻቸ ፣

ሙሉዉን ክፍያ በካሽ ለሚያጠናቅቁ የዋጋ ተመን ለውጥ ሳያገኛቸው በተዋዋሉበት የመጀመሪያ የዋጋ ስምምነት መሰረት  እንዲከፍሉ ተመቻችቷል::
የቅናሽ ፓኬጅ
100% ለሚከፍል የ 25% ቅናሽ
80% ለሚከፍል የ 20% ቅናሽ
60% ለሚከፋል የ 15% ቅናሽ
40% ለሚከፍል የ 10% ቅናሽ
25 % ለሚከፍል የ 6.5% ቅናሽ

በውጪ ምንዛሪ ለሚከፍሉ የ 5% ተጨማሪ ቅናሽ ያገኛሉ
"

አያት አክሲዮን ማህበር በ2015 ዓ.ም 51.3% ትርፍ ሲያተርፍ

የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የገዛ 513,000 ብር አትርፏል

የ 100,000ሺ ብር የገዛ 51,300 ብር አትርፏል

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር

ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2,500

በብር 250,000 ብር

ከፍተኛ የ 20 ሚሊዮን ብር

40% ቅድመ ክፍያ ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መክፈል ይችላሉ
አያት አ.ማ የተሰማራባቸው መስኮች:- በሪል እስቴት
በሆቴል እና ቱሪዝም
በማርብል ማምረቻ ኢንደስትሪ
በጠጠር ማምረቻ ኢንደስትሪ
በብሎኬት ማምረቻ ኢንደስትሪ
በእንጨት ብረታብረት ውጤቶች ማምረቻ ኢንዱስትሪ
በትምህርት ኢንቨስትመንት እና
በፋይናንሺያል ኢንቨስትመንት ናቸው።

ለበለጠ መረጃ እና ቤትዎን ለማስያዝ ፡ 0927715438/0903543582
ዬሴፍ
(የሽያጭ ተቆጣጣሪ)

አያት ዞሮ መግቢያዬ !
16.0K viewsAyu, 10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 12:24:36 የጊብሰን ትምህርት ቤት የሰጠው ምላሽ ደርሶኛል
ለተከበራችሁ ውድ የጊብሰን ትምህርት ቤቶች ሥርዓት ወላጆች እና አሳዳጊዎች፣


ጉዳዩ: ለሁሉም የጊብሰን ት/ቤቶች ሥርዓት ወላጆች እና ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈታኝ  ተማሪዎች ወላጆች ወቅታዊ መረጃን ማሳወቅ ይሆናል ፡፡

በመጀመሪያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ በቅርቡ የተማሪዎቻችን ከተማ አቀፍ ፈተናዎች መሳተፍን በሚመለከት ያልተረጋጋ ሁኔታ እየተፈጠረ ቢሆንም እርስዎን እና ቤተሰቦች በጥሩ ጤንነት እና መንፈስ ሆነው ይህ መልዕክት እንደሚደርሶት ተስፋ አደርጋለሁ።

እንደሚታወቀው ከትምህርት ቢሮ ኃላፊ በተሰጠ መመሪያ መሰረት የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን በተከበረው ጊብሰን ት/ቤቶች ስርዓት ስም ክልላዊ ፈተና እንዳይወስዱ አግዷል። ይልቁንም እነዚህ ተማሪዎች ቀድሞ ምንም ግንኙነት በሌላቸውና በማያውቋቸው የመንግሥት ትምህርት ቤቶች እንደሚመደቡ ተገልጿል። በቀላሉ ለመረዳት እንደሚቻለው፣ ይህ ያልተጠበቀ ድርጊት በትምህርት ቤታችን ማህበረሰቦች መካከል ግራ መጋባት እና ስጋት ፈጥሯል።

ይህ ውሳኔ ኢፍትሐዊ፣ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ እና የተማሪዎቻችንን ህጋዊ መብት ያልተከተለ ነው የሚለው የትምህርት ቤታችን ጽኑ አቋም መሆኑን ለማሳወቅ እወዳለሁ። ይህንን እገዳ ከዚህ ቀደም ላላወቁ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የከፍተኛ ተቋማት ባለስልጣናት በማሳወቅ ይህ ሁኔታ ተስተካክሎ ተማሪዎቻችን ሰላማዊና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለክልላዊ ፈተና የመቅረብ መብታቸውን እንዲጠቀሙበት እንዲደረግ ቅሬታችንን አቅረበናል።

ከዚህ ውሳኔ ጀርባ ያሉት ሁለቱ የትምህርት ቢሮ አመራሮች አቅጣጫቸውን በሌሎች ላይ በማድረግ ውሳኔያቸውን አስገድደው እየተገበሩ ይገኛሉ። ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነ ተግባር እንድንፈጽም ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ በየደረጃው ከተጋለጠ በኋላ በአጸፋውን ተማሪዎቻችንን ከክልላዊ ፈተና ከመከልከል ባለፈ የሁሉም ተማሪዎች የሪፖርት ካርድ ውድቅ ለማድረግ እና በመቀጠልም የጊብሰን ት/ቤቶችን ስርዓትን ሙሉ በሙሉ እንዘጋለን በማለት በማስፈራራት የትምህርት ቤታችንን ማህበረሰብ እየጎዱ ይገኛሉ።

አሁን የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ለዚህ እገዳ ተጠያቂ የሆኑ አመራሮች ተግባራቸውን በማስፋፋት አስቀደመው ለክልላዊ ፈተና የተመዘገቡ በሌሎች የትምህርት ቤታችን ቅርንጫፎች በተለይም በቦሌ እና በሲኤምሲ ቅርንጫፎች ላይ ተግባራቸውን ቀጥለዋል። እነዚህ ኃላፊዎች ወላጆች ልጆቻቸውን ምንም ግንኙነት በሌላቸው እንዲሁም ባልተማሩባቸው የተለያዩ ትምህርት ቤቶች በድጋሚ እንዲመዘገቡ በመጠየቅ ላይ ናቸው። ይህም የልጆቻችን የረጅም ጊዜ  ጥረት እና ድካም መና በማስቀረት ከፍተኛ ጉዳት ይኖረዋል። በሌላ በኩል ግን የሀገሪቱን የትምህርት ደህንነት ማጎልበት በሚገባቸው ግለሰቦች የሚፈጽሙትን ሥነ ምግባር የጎደላቸው ድርጊቶች ማሳያ ነው።

ከእነዚህ ክስተቶች አንፃር ተማሪዎቻችንን በመደገፍ በአንድነት መቆም እና የእነዚህን መሪዎች የተሳሳቱ ተግባራት ማጋለጥ የጋራ ሀላፊነታችን ነው።ሁሉም የጂ.ኤስ.ኤስ ወላጆች ለመብታቸው እና ለልጆቻቸው መብት በሀገሪቱ ህጎችና ስርዓቶች መሰረት በሰላም እና በትዕግስት እንዲሟገቱ አሳስባለሁ። የህግ የበላይነት ሊሰፍን ይገባል ይህም ፍትህን ለማረጋገጥ እና  የተማሪዎቻችንን የትምህርት ጉዞ ተጨማሪ መስተጓጎልን እንዳይፈጠር ለመከላከል በጣም ውጤታማው እርምጃ ነው።

እያንዳንዳችሁ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ከትምህርት ቤቱ ጋር በአንድነት እንድትቆሙ እና የከፋፍለህ ግዛ ስልታቸው ወጥመድ ውስጥ እንዳትገቡ አሳስባለሁ። በጋራ፣ የልጆቻችንን የትምህርት መብቶች እናስከብራለን ከዚህም ባለፈ በትጋት የሰሩባቸውን የትምህርት እድሎች እናረጋግጣለን። በህጋዊ መንገድ መብትን ለመጠየቅ እገዛ ወይም መመሪያ ከፈለጉ፣ እባክዎን የትምህርት ቤቱን አስተዳደር ለማግኘት አያመቱ። በእያንዳንዱ እርምጃች ላይ የእኛ ድጋፍ አይለያችሁም ፣ ለዚህም ዝግጁነታችንን እናሳውቃለን።

በአሳደራችሁት እምነትዎ እና እያደረጋችሁ ላላችሁት ትብብር ከልብ እመሰግናለን። በዚህ ፈታኝ ወቅት የሚኖሩ ለውጦችን በወቅቱ ለእርስዎ ለማሳወቅ ቃል እንገባለን። ለፍትሃዊነት እና ጥራት ላለው ትምህርት ባለን ታማኝነት የምናደርገውን ጥረት በተስፋ እና በቆራጥነት እንቀጥል።
የትምህርት ቤቱ ፕሬዚዳንት
"ለፈጣን መረጃ ቻናላችንን Join አድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
18.1K viewsAyu, edited  09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 12:24:05
17.3K viewsAyu, 09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 12:05:33
የሀገሪቷን የታክስ ኦዲትን ጥራት የሚቆጣጠረው ተቋም ማንነት ግልፅ አይደለም ተባለ
የታክስ ኦዲትን ጥራት የሚቆጣጠረው ተቋም ማንነት ግልጽና በታክስ ቢሮ ድረገጽ የሚወጡ ወቅታዊ የግብር መረጃዎች ለማግኘት አዳጋች መሆኑ በዘርፉ የተደረገዉ የፖሊሲ ሰነድ አመላክቷል።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የአዉሮፓ ቻምበር የሀገሪቷን የግብር አስተዳደርን በማሻሻል ላይ ያተኮረ የፖሊሲ ሰነድ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል ።

በዚህ የፖሊሲ ሰነድ በተደጋጋሚ የሚደረጉ አድካሚ ኦዲቶችና ወጥ ባልሆነ የግምገማ ቴክኒኮች ምክንያት በአንድ ኦዲት ተቀባይነት ያገኘ ወጪ በሌላ ኦዲት ዉድቅ የሚደረግበት ግልፅ ያልሆነ አሰራር መኖሩን በዝርዝር አስቀምጧል።

በግብር ኦዲተሮች ያልተገደበ ስልጣን እንዲሁም ዓለም አቀፍ የግብር ስምምነቶች ካላቸዉ የእዉቀት ዉስንነት ጋር ተዳምሮ የንግድ ስራ ሂደቱን አስቸጋሪ ማድረጉን ይሁ የፖሊሲ ሰነድ ዳሰሳ አመላክቷል ።

በገቢዎች ሚኒስትርና እንደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ባሉ የመንግስት መስሪያቤቶች የሚወጡ የግብር መመሪያዎች አለመጣጣም ደግሞ በግብር ከፋዮች ዘንድ ግራ መጋባት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑን ጠቁሟል።
"ለፈጣን መረጃ ቻናላችንን Join አድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
18.3K viewsAyu, edited  09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 11:53:51 አሜሪካ ዩክሬንን ለመርዳት የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን በድብቅ መላኳ ተነገረ
ዩክሬን ዩናይትድ ስቴትስ በድብቅ የሰጠችውን የረዥም ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን በሩሲያ ወራሪ ሃይሎች ላይ መጠቀም መጀመሯን የአሜሪካ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። መሳሪያዎቹ በመጋቢት ወር በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፀደቀው የ300 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ ጥቅል አካል ሲሆኑ በዚህ ወር ዩክሬን ደርሰዋል። በሩሲያ በተያዘችው የዩክሬን ግዛት ክሬሚያ ድራስ ኢላማዎችን ለመምታት ቢያንስ አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውለዋል ሲል የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋ።

ባይደን በተመሳሳይ አሁንም ለዩክሬን የ61 ቢሊዮን ዶላር የእርዳታ ፓኬጅ ፈርመዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ቀደም ለዩክሬን መካከለኛ ክልል የሚደርሱ የጦር ሃይል ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም አቅርባ ነበር። ነገርግን የበለጠ ኃይለኛ የጦር መሳሪያዎችን ለመላክ ፍቃደኛ ሳትሆን የቀረች ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በከፊል የአሜሪካን ወታደራዊ ዝግጁነት ለመጉዳት ያሳስባል በሚል ነበር። ሆኖም ባይደን በየካቲት ወር እስከ 300 ኪ.ሜ የሚተኮሱ የረዥም ርቀት የሚሳኤል ስርዓትን ለዩክሬን ለመላክ አረንጓዴ መብራትን በድብቅ መስጠታቸው ተነግሯል።

የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ቬዳንት ፓቴል "ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳኤል መሳሪያብ በፕሬዝዳንቱ ቀጥተኛ መመሪያ እንደሰጠች አረጋግጠዋል። ከመሳሪያዎቹ ውስጥ ምን ያህሉ እንደተላከ ግልጽ ባይሆንም የዩናይትድ ስቴትስ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ዋሽንግተን ተጨማሪ ለመላክ አቅዳለች ብለዋል።

ረጅም ርቀት የሚጓዙ ሚሳኤሎች ባለፈው ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ በክራይሚያ የሚገኘውን የሩሲያ አየር መንገድ ለመምታት ጥቅም ላይ መዋላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ስማቸው ያልገለጻቸውን የአሜሪካ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል። አዲሶቹ ሚሳኤሎች ማክሰኞ እለት በሞስኮ በተያዘችው የዩክሬን የወደብ ከተማ በርዲያንስክ ውስጥ በሩሲያ ወታደሮች ላይ በተሰነዘረ ጥቃትም ጥቅም ላይ ውለዋል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

በቅርብ ወራት ኪየቭ የጥይት ክምችቷ በመሟጠጡ እና ለሩሲያ ይህ ሁኔታ ቀጣይነት ያለው ትርፍ ስለሚያስገኝ በሚል ለምዕራቡ ዓለም የእርዳታ ጥሪዋን እያጠናከረች ትገኛለች።
"ለፈጣን መረጃ ቻናላችንን Join አድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
17.4K viewsAyu, edited  08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 11:53:43
16.6K viewsAyu, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 11:53:26
አለምን እያነጋገረ ያለ ድንቅ የ ቴክኖሎጂ ምርት

በጥቂት ጊዜያት ዉስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘዉ ተች ሴንሰር የተገጠመለት ተቆጥረዉ የማያልቁ አገልግሎቶችን ከስልክ ጋር ተገናኝቶ መስጠት የሚችለዉ W26 pro max ለእናንተ

W26 PRO MAX Special with
Earbuds

ለወንድም ለሴትም የሚሆን ዘረፈ ብዙ ጥቅምች ያሉት smartwach ከ pro wireless earpode ጋር

   የራሱ ቻርጀር እና power bank ያለዉ
የልብ ምትዋን  ይለካል
ስፖርት ስንሰራ ምን ያህል ካሎሪ እንዳቃጠልን ያሳውቃል
ብዙ ሰአት ስንተኛ ይቀሰቅሰናል
ስልካችን ሲጠፋ ለመፈለጊያ ያግዘናል
ቴክስት መላክ እንዲሁም መቀበል የሚያስችል
ከስልክ ጋ በ Bluetooth ተገናኝቶ ስልክ መደወል እንዲሁም ማናገር ያቻላል
  wireless charger እና በሁለት አይነት የእጅ መሳርያ የቀርበ
  Blood Oxygen Detection
Stress & Mood Testing

አዲስ አበባ ዉስጥ ነፃ እና ፈጣን  የዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን።

ዋጋ  2199 ብር ብቻ
       ፈጥነዉ ይደዉሉ
0909812211
    +251712148785

  ወይም ስልክና አድራሻዎን
@AAU_Shop  ላይ ይላኩልን።

ተጨማሪ እቃዎችን ለማየት
@AAU_Market ን ይቀላቀሉ።
17.5K viewsAyu, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 10:38:19
ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ እኚህን አባት ከየት መጣህ ? ለምን መጣህ ? ማን ነህ ? ምንድን ነህ ? እያሉ እየተሳለቁባቸው፣ሲያስጨንቋቸው እሳቸው ደግሞ "እንጀራ ፍለጋ ነው የመጣሁት ከጎጃም ነው ቢሉም" ወጣቶቹ "ጎጃም እንጀራ ጠፍቶ ነወይ" እያሉ እየተሰላቁ ሲደበድቧቸው አባትውም "ምንም ያደረኩት ነገር የለም፣በህግ አምላክ ተውኝ..." እያሉ ሲማፀኑ የሚያሳይ ምስል ተቀርፆ ወጥቶ መነጋገሪያ ሆኖ መክረሙ ይታወሳል።
ይህ የሆነው በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ለገጣፎ አቅራቢያ 44 ማዞሪያ ጅዳ ኩራ በተባለ ቦታ ሲሆን ከቀናት በፊት ተደብዳቢው አባትም ደብዳቢዎቹም ጅዳኩራ በተባለ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበረ ቢሆንም ድብደባ እና ወከባ የደረሰባቸው አባት(አቶ ብርሃኑ) ትናንት ከእስር ተፈተዋል።
እኚህ አባት ላይ ወከባ እና ድብደባ ፈፅመውባቸው የነበሩ7 ወጣቶች በፍ/ቤት ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል[አዩዘሀበሻ]።
"ለፈጣን መረጃ ቻናላችንን Join አድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
18.8K viewsAyu, edited  07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 10:38:12
ማስታወቂያ
ቁጠባ ከጀመሩ ከ10 ቀን ጀምሮ ብድር የሚያገኙበት ብቸኛ ተቋም

ግሎባል ቁጠባና ብድር

የስራ መኪና ግዥ እስከ ብር 3,000,000

50% የቆጠበ በ1 ወር ከ15 ቀን!
40% የቆጠበ በ2 ወር !
30% የቆጠበ በ2 ወር ከ15 ቀን!
25% የቆጠበ በ3 ወር የስራ መኪና ግዥ ብድር የሚያገኝ ይሆናል።

ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለኮንደሚኒዬም ቤት ቅድመ ክፍያና ሙሉ ክፍያ፣ ግዥ፣ ለስራ መነሻና ማስፋፊያ የሚሆን ብድር ቁጠባ ከጀመሩ ከ10 ቀን ጀምሮ እስከ ብር 6,000,000. ብድር አመቻችተናል።

የተቋሙ አባል በመሆንና ቁጠባ በመጀመር ራስዎንና ቤተሰብዎን ይጥቀሙ!!!

ግሎባል ቁጠባና ብድር ከኢቶፒካር አስመጭ ጋር በመተባበር!

አድራሻ:- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት ቅዱስ ፕላዛ 6ኛ ፎቅ!

#ስልክ ቁ.  0118-12-66-16
                  0956-23-24-25
                  0979-25-26-27

ወደ ቴሌ ግራም ገፃችን ለመግባት
https://t.me/globalsavingandcredit
በቲክቶክ አካውንታችን ቤተሰብ ይሁኑ
http://tiktok.com/@global.saving.and.credit
18.4K viewsAyu, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 10:21:08
ፀድቋል
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ቲክቶክ ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል።
የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሹ ዚ ቼው ፥ " የትም አንሄድም። ለመብታችን በፍርድ ቤት እንታገላለን። ሀቁ እና ህገ መንግስቱ ከጎናችን ናቸው፣ እናሸንፋለን ብለን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል። ቲክቶክ ከአሜሪካ እንዲሁም ከአውሮፓ ሀገራት ከካምፓኒዎች በሚያገኘው ገቢ ውጤታማ ሆኖ እራሱን እያሻሻለ እዚህ የደረሰ ቢሆንም የቲክቶክ ባለቤት ለአሜሪካ ባለሀብቶች ቲክቶክን ለአሜሪካ አሳልፎ የማይሸጥ ከሆነ በአሜሪካ ሙሉ ለሙሉ መታገዱ አይቀርም። ይህ ከሆነ ደግሞ ቲክቶክ ከአሜሪካ ካምፓኒዎች የሚያገኘውን የማስታወቂያ ገቢ ስለሚያጣ ኪሳራ ሊያጋጥመው ስለሚችል ቲክቶክ አደጋ ውስጥ መውደቁ አይቀሬ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ የአውሮፓ ሀገራትም ቲክቶክን ለመዝጋት እየተዘጋጁ ያሉም አሉ።
ከኬንያ እንዲሁም ከደቡብ አፍሪካ ጥቂት ከምፓኒዎች በስተቀር ቲክቶክ ከአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከማስታወቂያ ምንም የሚያገኘው ጥቅም የለም።
አዩዘሀበሻ
"ለፈጣን መረጃ ቻናላችንን Join አድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
18.2K viewsAyu, edited  07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ