Get Mystery Box with random crypto!

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ እኚህን አባት ከየት መጣህ ? ለምን መጣህ ? ማን ነህ ? ምንድ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ እኚህን አባት ከየት መጣህ ? ለምን መጣህ ? ማን ነህ ? ምንድን ነህ ? እያሉ እየተሳለቁባቸው፣ሲያስጨንቋቸው እሳቸው ደግሞ "እንጀራ ፍለጋ ነው የመጣሁት ከጎጃም ነው ቢሉም" ወጣቶቹ "ጎጃም እንጀራ ጠፍቶ ነወይ" እያሉ እየተሰላቁ ሲደበድቧቸው አባትውም "ምንም ያደረኩት ነገር የለም፣በህግ አምላክ ተውኝ..." እያሉ ሲማፀኑ የሚያሳይ ምስል ተቀርፆ ወጥቶ መነጋገሪያ ሆኖ መክረሙ ይታወሳል።
ይህ የሆነው በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ለገጣፎ አቅራቢያ 44 ማዞሪያ ጅዳ ኩራ በተባለ ቦታ ሲሆን ከቀናት በፊት ተደብዳቢው አባትም ደብዳቢዎቹም ጅዳኩራ በተባለ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበረ ቢሆንም ድብደባ እና ወከባ የደረሰባቸው አባት(አቶ ብርሃኑ) ትናንት ከእስር ተፈተዋል።
እኚህ አባት ላይ ወከባ እና ድብደባ ፈፅመውባቸው የነበሩ7 ወጣቶች በፍ/ቤት ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል[አዩዘሀበሻ]።
"ለፈጣን መረጃ ቻናላችንን Join አድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial