Get Mystery Box with random crypto!

ፀድቋል የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ቲክቶክ ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

ፀድቋል
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ቲክቶክ ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል።
የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሹ ዚ ቼው ፥ " የትም አንሄድም። ለመብታችን በፍርድ ቤት እንታገላለን። ሀቁ እና ህገ መንግስቱ ከጎናችን ናቸው፣ እናሸንፋለን ብለን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል። ቲክቶክ ከአሜሪካ እንዲሁም ከአውሮፓ ሀገራት ከካምፓኒዎች በሚያገኘው ገቢ ውጤታማ ሆኖ እራሱን እያሻሻለ እዚህ የደረሰ ቢሆንም የቲክቶክ ባለቤት ለአሜሪካ ባለሀብቶች ቲክቶክን ለአሜሪካ አሳልፎ የማይሸጥ ከሆነ በአሜሪካ ሙሉ ለሙሉ መታገዱ አይቀርም። ይህ ከሆነ ደግሞ ቲክቶክ ከአሜሪካ ካምፓኒዎች የሚያገኘውን የማስታወቂያ ገቢ ስለሚያጣ ኪሳራ ሊያጋጥመው ስለሚችል ቲክቶክ አደጋ ውስጥ መውደቁ አይቀሬ ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ የአውሮፓ ሀገራትም ቲክቶክን ለመዝጋት እየተዘጋጁ ያሉም አሉ።
ከኬንያ እንዲሁም ከደቡብ አፍሪካ ጥቂት ከምፓኒዎች በስተቀር ቲክቶክ ከአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከማስታወቂያ ምንም የሚያገኘው ጥቅም የለም።
አዩዘሀበሻ
"ለፈጣን መረጃ ቻናላችንን Join አድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial