Get Mystery Box with random crypto!

የካናዳ ኤምባሲ በሰሜን ፣ መካከለኛ እና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢዎች ዜጎቹ እንዳይቀሳቀሱ መክሯል | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የካናዳ ኤምባሲ በሰሜን ፣ መካከለኛ እና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢዎች ዜጎቹ እንዳይቀሳቀሱ መክሯል
ኤምባሲዉ በአዲስአበባ ጭምር ዜጎቹ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል
የካናዳ መንግስት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ በጥቅሉ አስፈላጊ እና አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር እንዳይጓዙ ሲል ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል። ኢትዮጵያ የሕዝባዊ አመፅ ፣ ብጥብጥ ፣ በትጥቅ ግጭት እና የወንጀል ድርጊት በዞቶባታል ሲል ባስቀመጠው ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ዜጎቹ አላስፈላጊ ጉዞን ያስወግዱ ሲልም አሳስቧል።

በዋነኛነት በሰሜን ኢትዮጵያ አማራ ፣ ትግራይ (ከመቐለ ከተማ ዉጪ ወደ አዲግራት ፣ አቢ አዲ ፣ አድዋ ፣ ሽሬ እና ማይጨዉ አካባቢዎች) እንዲሁም ወደ ቤኒሻንጉል ክልሎች ዜጎቹ አይጓዙ ሲል አስጠንቅቋል።

በተጨማሪም መካከለኛዉ ኢትዮጵያ ክፍል ጋምቤላ እና ሲዳማ ክልሎች እንዲሁም ሰሜን እና ምዕራብ ሸዋ እና ወደ አራቱ የወለጋ ዞኖች ዜጎቹ እንዳይጓዙ ጠይቋል። እንዲሁም ኢትዮጵያን ከኬንያ ፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ሱዳን ፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችም ዜጎቹ እንዲጠበቁ መክሯል።

ኤምባሲዉ የካናዳ ዜጎች በአዲስአበባ ጭምር ዜጎቹ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ከፍተኛ የተባለ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
Join @ayuzehabeshaofficial
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ @ayulaw