Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ለሚ እየተገነባ ላለው የሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ የሚያገለግሉ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ለሚ እየተገነባ ላለው የሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ የሚያገለግሉ ከባድ ማሽነሪዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ ነው
ለለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ የሚያገለግሉ ከባድ ማሽነሪዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ መሆኑን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) አስታወቀ።

ማሽነሪዎቹ በሐረር መርከብ ተጭነው ጅቡቲ ወደብ መራገፋቸውን ያስታወሰው ኢባትሎ÷ አሁን ላይም በከባድ የየብስ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ ይገኛሉ ብሏል።
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካ÷ በቀን ከ10 ሺህ ቶን በላይ ሲሚንቶ የማምረት አቅም እንዳለው ተጠቁሟል፡፡
ለሚ ሲሚንቶ በግንባታ ሒደት ላይ ሆኖ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን÷ ግንባታው ተጠናቅቆ ምርት ማምረት ሲጀምር ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር እንደሚችል የኢባትሎ መረጃ አመልክቷል፡፡
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial