Get Mystery Box with random crypto!

የሀገሪቷን የታክስ ኦዲትን ጥራት የሚቆጣጠረው ተቋም ማንነት ግልፅ አይደለም ተባለ የታክስ ኦዲት | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የሀገሪቷን የታክስ ኦዲትን ጥራት የሚቆጣጠረው ተቋም ማንነት ግልፅ አይደለም ተባለ
የታክስ ኦዲትን ጥራት የሚቆጣጠረው ተቋም ማንነት ግልጽና በታክስ ቢሮ ድረገጽ የሚወጡ ወቅታዊ የግብር መረጃዎች ለማግኘት አዳጋች መሆኑ በዘርፉ የተደረገዉ የፖሊሲ ሰነድ አመላክቷል።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የአዉሮፓ ቻምበር የሀገሪቷን የግብር አስተዳደርን በማሻሻል ላይ ያተኮረ የፖሊሲ ሰነድ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል ።

በዚህ የፖሊሲ ሰነድ በተደጋጋሚ የሚደረጉ አድካሚ ኦዲቶችና ወጥ ባልሆነ የግምገማ ቴክኒኮች ምክንያት በአንድ ኦዲት ተቀባይነት ያገኘ ወጪ በሌላ ኦዲት ዉድቅ የሚደረግበት ግልፅ ያልሆነ አሰራር መኖሩን በዝርዝር አስቀምጧል።

በግብር ኦዲተሮች ያልተገደበ ስልጣን እንዲሁም ዓለም አቀፍ የግብር ስምምነቶች ካላቸዉ የእዉቀት ዉስንነት ጋር ተዳምሮ የንግድ ስራ ሂደቱን አስቸጋሪ ማድረጉን ይሁ የፖሊሲ ሰነድ ዳሰሳ አመላክቷል ።

በገቢዎች ሚኒስትርና እንደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ባሉ የመንግስት መስሪያቤቶች የሚወጡ የግብር መመሪያዎች አለመጣጣም ደግሞ በግብር ከፋዮች ዘንድ ግራ መጋባት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑን ጠቁሟል።
"ለፈጣን መረጃ ቻናላችንን Join አድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial