Get Mystery Box with random crypto!

የጊብሰን ትምህርት ቤት የሰጠው ምላሽ ደርሶኛል ለተከበራችሁ ውድ የጊብሰን ትምህርት ቤቶች ሥርዓ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የጊብሰን ትምህርት ቤት የሰጠው ምላሽ ደርሶኛል
ለተከበራችሁ ውድ የጊብሰን ትምህርት ቤቶች ሥርዓት ወላጆች እና አሳዳጊዎች፣


ጉዳዩ: ለሁሉም የጊብሰን ት/ቤቶች ሥርዓት ወላጆች እና ለ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈታኝ  ተማሪዎች ወላጆች ወቅታዊ መረጃን ማሳወቅ ይሆናል ፡፡

በመጀመሪያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ በቅርቡ የተማሪዎቻችን ከተማ አቀፍ ፈተናዎች መሳተፍን በሚመለከት ያልተረጋጋ ሁኔታ እየተፈጠረ ቢሆንም እርስዎን እና ቤተሰቦች በጥሩ ጤንነት እና መንፈስ ሆነው ይህ መልዕክት እንደሚደርሶት ተስፋ አደርጋለሁ።

እንደሚታወቀው ከትምህርት ቢሮ ኃላፊ በተሰጠ መመሪያ መሰረት የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን በተከበረው ጊብሰን ት/ቤቶች ስርዓት ስም ክልላዊ ፈተና እንዳይወስዱ አግዷል። ይልቁንም እነዚህ ተማሪዎች ቀድሞ ምንም ግንኙነት በሌላቸውና በማያውቋቸው የመንግሥት ትምህርት ቤቶች እንደሚመደቡ ተገልጿል። በቀላሉ ለመረዳት እንደሚቻለው፣ ይህ ያልተጠበቀ ድርጊት በትምህርት ቤታችን ማህበረሰቦች መካከል ግራ መጋባት እና ስጋት ፈጥሯል።

ይህ ውሳኔ ኢፍትሐዊ፣ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ እና የተማሪዎቻችንን ህጋዊ መብት ያልተከተለ ነው የሚለው የትምህርት ቤታችን ጽኑ አቋም መሆኑን ለማሳወቅ እወዳለሁ። ይህንን እገዳ ከዚህ ቀደም ላላወቁ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የከፍተኛ ተቋማት ባለስልጣናት በማሳወቅ ይህ ሁኔታ ተስተካክሎ ተማሪዎቻችን ሰላማዊና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለክልላዊ ፈተና የመቅረብ መብታቸውን እንዲጠቀሙበት እንዲደረግ ቅሬታችንን አቅረበናል።

ከዚህ ውሳኔ ጀርባ ያሉት ሁለቱ የትምህርት ቢሮ አመራሮች አቅጣጫቸውን በሌሎች ላይ በማድረግ ውሳኔያቸውን አስገድደው እየተገበሩ ይገኛሉ። ከሥነ ምግባር ውጭ የሆነ ተግባር እንድንፈጽም ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ በየደረጃው ከተጋለጠ በኋላ በአጸፋውን ተማሪዎቻችንን ከክልላዊ ፈተና ከመከልከል ባለፈ የሁሉም ተማሪዎች የሪፖርት ካርድ ውድቅ ለማድረግ እና በመቀጠልም የጊብሰን ት/ቤቶችን ስርዓትን ሙሉ በሙሉ እንዘጋለን በማለት በማስፈራራት የትምህርት ቤታችንን ማህበረሰብ እየጎዱ ይገኛሉ።

አሁን የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ለዚህ እገዳ ተጠያቂ የሆኑ አመራሮች ተግባራቸውን በማስፋፋት አስቀደመው ለክልላዊ ፈተና የተመዘገቡ በሌሎች የትምህርት ቤታችን ቅርንጫፎች በተለይም በቦሌ እና በሲኤምሲ ቅርንጫፎች ላይ ተግባራቸውን ቀጥለዋል። እነዚህ ኃላፊዎች ወላጆች ልጆቻቸውን ምንም ግንኙነት በሌላቸው እንዲሁም ባልተማሩባቸው የተለያዩ ትምህርት ቤቶች በድጋሚ እንዲመዘገቡ በመጠየቅ ላይ ናቸው። ይህም የልጆቻችን የረጅም ጊዜ  ጥረት እና ድካም መና በማስቀረት ከፍተኛ ጉዳት ይኖረዋል። በሌላ በኩል ግን የሀገሪቱን የትምህርት ደህንነት ማጎልበት በሚገባቸው ግለሰቦች የሚፈጽሙትን ሥነ ምግባር የጎደላቸው ድርጊቶች ማሳያ ነው።

ከእነዚህ ክስተቶች አንፃር ተማሪዎቻችንን በመደገፍ በአንድነት መቆም እና የእነዚህን መሪዎች የተሳሳቱ ተግባራት ማጋለጥ የጋራ ሀላፊነታችን ነው።ሁሉም የጂ.ኤስ.ኤስ ወላጆች ለመብታቸው እና ለልጆቻቸው መብት በሀገሪቱ ህጎችና ስርዓቶች መሰረት በሰላም እና በትዕግስት እንዲሟገቱ አሳስባለሁ። የህግ የበላይነት ሊሰፍን ይገባል ይህም ፍትህን ለማረጋገጥ እና  የተማሪዎቻችንን የትምህርት ጉዞ ተጨማሪ መስተጓጎልን እንዳይፈጠር ለመከላከል በጣም ውጤታማው እርምጃ ነው።

እያንዳንዳችሁ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ከትምህርት ቤቱ ጋር በአንድነት እንድትቆሙ እና የከፋፍለህ ግዛ ስልታቸው ወጥመድ ውስጥ እንዳትገቡ አሳስባለሁ። በጋራ፣ የልጆቻችንን የትምህርት መብቶች እናስከብራለን ከዚህም ባለፈ በትጋት የሰሩባቸውን የትምህርት እድሎች እናረጋግጣለን። በህጋዊ መንገድ መብትን ለመጠየቅ እገዛ ወይም መመሪያ ከፈለጉ፣ እባክዎን የትምህርት ቤቱን አስተዳደር ለማግኘት አያመቱ። በእያንዳንዱ እርምጃች ላይ የእኛ ድጋፍ አይለያችሁም ፣ ለዚህም ዝግጁነታችንን እናሳውቃለን።

በአሳደራችሁት እምነትዎ እና እያደረጋችሁ ላላችሁት ትብብር ከልብ እመሰግናለን። በዚህ ፈታኝ ወቅት የሚኖሩ ለውጦችን በወቅቱ ለእርስዎ ለማሳወቅ ቃል እንገባለን። ለፍትሃዊነት እና ጥራት ላለው ትምህርት ባለን ታማኝነት የምናደርገውን ጥረት በተስፋ እና በቆራጥነት እንቀጥል።
የትምህርት ቤቱ ፕሬዚዳንት
"ለፈጣን መረጃ ቻናላችንን Join አድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial