Get Mystery Box with random crypto!

Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የሰርጥ አድራሻ: @ayuzehabeshaofficial
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 181.69K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2024-04-19 10:34:20
ለስራም ሆነ ለትምህርት ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገር መላክ በስራ እና ክህሎት ሚኒቴር ኃላፊነት የሚተገበር መሆኑ ተገለጸ
ዜጎችን ለስራም ሆነ ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ፍቃድ ለስራና ክህሎት ሚኒስቴር ብቻ የተሰጠ ሃላፊነት መሆኑን በሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጫ ዴስክ ሃላፊ አቶ ተክሌ ተስፉ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ኤጀንሲዎች ሰዎችን ካናዳና ወደ ሌሎችም የውጭ ሀገራት ስራ እናስቀጥራችኃለን በሚል የሚስተላለፉት ማስታወቂያ ፈጽሞ ፈቃድ የሌለው እና ህገ ወጥ መሆኑን በመጥቀስ በጥቆማና በፍለጋ ሲደረስባቸው እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ሃላፊው ገልጸዋል።

ለኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጠቱንም መቆጣጠሩንም የሚመለከተው የመንግስት ተቋም ስራና ክህሎት ሚኒስቴር መሆኑን በመናገር በፌደራልም በክልልም ያሉ ኤጀንሲዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፈቃድ ከተሰጣቸው ብቻ ስራው ላይ መሰማራት እንደሚችሉ አቶ ተክሌ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እየተበራከቱ የመጡት ህገ ወጥ ኤጀንሲዎች በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እርምጃ እንደሚወሰድባቸውና ህጋዊ በሆነ አሰራር ላይ ብቻ ተመስርተው የዜጎችን የስራ ሁኔታ እንደሚያግዙ የዴስክ ሃላፊው አመላክተዋል።

ዜጎችን ወደ ውጭ እንልካለን የሚሉ ህገ ወጦች ምንም አይነት እውቅና የሌላቸው በመሆኑ ሲደረስበት ከፖሊስ ጋር በመሆን እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተነግሯል።

የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
13.0K viewsAyu, edited  07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 10:03:24
እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረች
እስራኤል ከኢራን ለተቃጣባት የሚሳኤልና ድሮን ጥቃቶች የአጸፋ እርምጃ መውሰዷ ተገለጸ።

እስራኤል ኢስፋሃን በተባለ የማዕከላዊ አራን አካባቢ ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ላይ በድሮኖች ጥቃት መሰንዘሯ ነው የተጠቀሰው።

ይህን ተከትሎ ኢራን የጸረ-ሚሳኤል መከላከያ ማስወንጨፏንና የተተኮሱባትን ሦስት ድሮኖች መታ መጣሏን አስታውቃለች።

ኢስፋሃን የኢራን አየር ኃይል እና የኒዩክሌር ጣቢያ የሚገኝ ከተማዋ ሲሆን በአካባቢው የተሰማው ፍንዳታ ኢራን ያስወነጨፈቻቸው የጸረ ሚሳኤል መከላከያ መሆኑን አገሪቱ ባወጣችው መረጃ ገልጻለች።

የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ የአየር በረራዎች ተስተጓጉለው እንደነበርና በአሁኑ ሰዓት በረራ መጀመሩን እንዲሁም አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን የአልጃዚራ ዘገባ አመላክቷል።

በፈረንጆቹ ሚያዝያ 1 ቀን እስራኤል ሶሪያ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ላይ ባደረሰችው ጥቃት 13 ዜጎቿ መገደላቸውን ተከትሎ በእስራኤል ላይ ባሳለፍነው ቅዳሜ 300 ሚሳኤልና የድሮን ጥቃት ማድረሷ ይታወሳል።

ለኢራን ጥቃት እስራኤል አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ እንደነበርም የሚታወስ ነው።
የሁለቱ አገራት የሰሞኑ ግጭትን ተከትሎ አገራት ዜጎቻቸውን ወደ እስራኤል እንዳይጓዙ እያስጠነቀቁ ነው።

ከስውር ጦርነት አልፎ ወደ ይፋዊና ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው የሁለቱ አገራት የሰሞነኛ ፍጥጫ በቋፍ ላይ የነበረ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ወደለየለት ጦርነት እንዳይከተው ተሰግቷል።

የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
13.7K viewsAyu, 07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 09:44:16
ኬንያ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሄራዊ የሀዘን ቀን አወጀች
በኬንያ በሄሊኮፕተር አደጋ የሀገሪቱ ጦር ዋና አዛዥን ጨምሮ 9 የኬንያ ጦር አባላት መሞታውን ተከትሎ ብሄራዊ የሀዘን ቀን አውጃለች።

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ማምሻወን በሰጡት መግለጫ፤ “የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋውም የኬንያ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞዲ ኦጎላ ህይወታቸው ማፉን ስገልጽ በትላቅ ሀዘን ውስጥ ሆኜ ነው” ብለዋል።

ይህንን ተከትሎም በኬንያ ከነገ ጀምሮ የሚተገበር ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሄራዊ የሀዘን ቀን መታወጁን ፕሬዝዳነቱ አስታውቀዋል።

የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
13.5K viewsAyu, edited  06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 09:40:36
በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን (የኦሮሞ እና የትግራይና ማኅበረሰብ) አባላት ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቅ ሰልፍ አካሄዱ
ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት፣ የኦነግ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት የአቶ በቴ ዑርጌሳ ግድያን የሚቃወም ሰልፍ እና የሻማ ማብራት ሥነሥርዐት አከናወኑ። ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ይደርሳል ያሉትን ግድያ ተቃውመው ጦርነት እንዲቆም ጠይቀዋል። በሌላ በኩል በዚሁ አካባቢ ሰልፍ ያደረጉት ትውልደ ኢትዮጵያ የትግራይ ተወላጆች፣ ጦርነት እንዲቆም፣ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲከበር እና ተገቢው ርዳታ ወደ ክልሉ እንዲገባ የሚጠይቅ ሰልፍ አካሂደዋል ሲል የአሜሪካ ድምፅ ዘገባ ያመላክታል።

የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
13.3K viewsAyu, edited  06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 09:34:04 አሁንም ቢሆን ወንድም በወንድሙ፤ ወገን በወገኑ ላይ በመተኮስ የሚወሳሰብ እንጂ የሚፈታ ችግር የለም፡፡ በመንግሥት በተለይም በፌዴራል መንግሥት በኩል መሠረታዊዎቹን የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች በአግባቡ ከመመለስ ውጭ የኃይል አማራጭ መከተል አደጋው የከፋ ነው፡፡ ከግጭት አዙሪት መውጣት የሚቻለው መሠረታዊውን የሕዝብ ጥያቄ በሰከነ መንገድ፣ ከልብ በመመለስ ብቻና ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም፡-
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን፤ የትግሉ አስኳልና የ2010ሩ የፖለቲካ ለውጥ መነሻ በመሆኑ፤ ገዥው ብልጽግና ፓርቲና የሚመራው የኢፌዴሪ መንግሥት ጉዳዩን በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያየው በድጋሚ እናሳስባለን!
ምንጊዜም ቢሆን ትግላችን ሕዝባዊ መሰረት ያለው እንጅ በመዋቅር ላይ የሚንጠለጠል አይደለም፡፡ መዋቅር የሚያስፈልገው የሕዝብን የትግል ዓላማ በተሰናሰለ መልኩ ለማስፈጸም ነው፡፡ አሁንም ቢሆን መዋቅር በማፈረስ የሚጣል የማንነት ትግል አጀንዳ የለንም፡፡ ለአማራዊ ማንነታችን በዘላቂነት መከበር እንደቀደመው ጊዜ ሁሉ ሕዝባችን ኃይላችን፤ ጉልበታችን ሕዝባዊነታችን ሆኖ ይቀጥላል፡፡በመሆኑም ትግላችን ሕዝባዊ ሆኖ እንደሚዘልቅ እናረጋግጣለን!!
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መሆኑን በመጣንባቸው የትግል ምዕራፎች አስመስክረናል፡፡ ለዚህ እልፎችን በሰማዕትነት ለገበርንበት፣ የአማራ ሕዝብ የትግል አስኳል ሆኖ ለቀጠለው የወሰንና ማንነት ጥያቄያችን በዘላቂነት መመለስ እስከመጨረሻው ፀንተን እንቆማለን!! ‹ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ› በሚል በመላ አማራ ዋጋ የከፈሉ ወገኖቻችን ሁሉ ሰማዕትነታቸውን እንዘክራለን፤ ቃላቸውን እንፈጽማለን፤ መቼውንም ቢሆን የትግል አደራ አይታጠፍም; ዳግም በጅምላ አንገደልም!!

የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
13.1K viewsAyu, edited  06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 09:30:33
12.8K viewsAyu, 06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 09:29:32
ማስታወቂያ
ጥራቱ የተመሰከረለት ሻሎም የጥርስ ህክምና ክሊኒክ
አራት ኪሎ ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና
ኮተቤ 02 ጆሲ  ሙል ላይ በሚገኙ ክሊኒኮች የተሙላ የጥርስ ህክምና እየሰጠ ይገኛል።
የሚሰጣቸው አገልግሎቱች
የቁሸሾ ጥርስ   ማጠብ
የተቡረቡሮ ጥርስ መሙላት
በአበቃቀል የተበላሹ ጥርሳችንን ብሬስ ማስተካከል (በተመጣጣኝ ዋጋ እና አከፋፈል አማራጮች )
የጥርስ ስር ህክምና
የድድ  መድማት ችግር ላለባቸው
ሁሉንም አይነት ሰው ሰራሽ ጥርስ አንተክላለን ፤ ለተተከለዉም ዋስትና እንሠጣለን
ታክመው የማይድኖ ጥርሶች እንነቅላለን
አድራሻ   ቁጥር-4 ኪሎ ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ
,ቁጥር 2 - ኮተቤ 02 ጆሴ ሞል
ለበለጠ መረጃ  0911424242
ስለ ጥርስ ንፅህና አጠባበቅ እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት Telegram join

https://t.me/shalomdentalclinic
https://t.me/shalomdentalclinic
https://t.me/shalomdentalclinic
15.0K viewsAyu, 06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 17:18:45
በኢትዮጵያ በዓመት 46 ሚሊየን ሕዝብ ሊመግብ የሚችል ምግብ እየባከነ ነው ተባለ
የግብርና ሚኒስቴር አዲስ ያስተዋወቀው የግብርና ምርቶች አስተዳደርና አመራር ስትራቴጂ በኢትዮጵያ በየዓመቱ 474 ነጥብ 67 ቢሊየን ብር የሚያወጣ የምርት ብክነት መኖሩን አመላከተ።

ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም ብክነትን ለማስቀረት ሲሠራበት የቆየው ስትራቴጂ እህልና ጥራጥሬ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፥ አዲሱ ስትራቴጂ ተጨማሪ ሁለት ዘርፎችን አካቷል።

በእንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦ፣ በጥራጥሬ፣ በዕፅዋትና በሰብል ምርቶች በዓመት 46 ሚሊየን ሕዝብ ሊመግብ የሚችል ምግብ እየባከነ መሆኑንም አመላክቷል።

በየዓመቱ 161 ነጥብ 74 ቢሊየን ብር የሚያወጣ የሥጋና ወተት ምርቶች ብክነት እያጋጠመ መሆኑንም ጠቅሷል።

በተጨማሪም 312 ነጥብ 93 ቢሊየን ብር የሚያወጡ የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬዎች፣ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች እየባከኑ መሆኑም ነው የገለጸው።

የሃገሪቱን የምግብ ዋስትናና ሥነ ምግብ ሥርዓት ደኅንነት ከማረጋገጥ፣ ለግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ቀጣይነት ያለው ጥሬ ዕቃዎች ከማቅረብ፣ የወጪ ንግድን ከማበረታታት፣ የሥራ ዕድል ከማሳደግና ሁሉን አቀፍ የሆነ ሃገራዊ የልማት ስትራቴጂ ከመከተል አንፃር የግብርና ምርቶች ብክነት አስተዳደር ጉዳይ ችላ ተብሎ የቆየ መሆኑን ጠቅሷል።

እንደ ስትራቴጂው ማብራሪያ እያጋጠመ ያለው ብክነት የምርት ሒደት የሚያቀላጥፉ ግብዓቶችን፥ ማለትም ምርጥ ዘር፣ ውኃ፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ የግብርና ኬሚካሎች፣ መሬት፣ የእንስሳት መኖ እንዲሁም የእንስሳት መድኃኒቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ካለመቻል የመጣ መሆኑን አስረድተዋል።

የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
24.1K viewsAyu, edited  14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 16:09:20
የፓርላማው ድብድብ

የጆርጂያ ሕግ አውጭዎች ሰኞ ዕለት በተሰበሰበው ፓርላማ ውስጥ ተደባድበዋል።

የፓርላማ አባላቱ አወዛጋቢ በሆነው የውጭ ወኪሎች ረቂቅ ህግ ላይ በፓርላማ በተካሄደው ክርክር ወቅት የተቃዋሚው ፓርላማ አባል አሌኮ ኤሊሳሽቪሊ የገዥውን የጆርጂያ ድሪም ፓርቲ መሪ ማሙካ ምዲናራዜን በንግግራቸው ፊት ለፊት በቡጢ ከመቱ በኋላ ነው። 

በውጭ አገር ገንዘቦችን የሚቀበሉ ድርጅቶች እንደ የውጭ ወኪልነት እንዲመዘገቡ ወይም ሊቀጡ የሚችሉበት ሂሳቡ፣ ጆርጂያን ፖላራይዝድ አድርጓል እና በ2023 መጀመሪያ ላይ የጅምላ ሰልፎችን አድርጓል።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
23.0K viewsAyu, edited  13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 16:08:11
#የቻናል_ጥቆማ

ለኢንጅነሮች ተማሪዎች እናconstruction ዘርፍ ለይ ለተሰማሩት ሁሉ

የኮንስትራክሽ፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ፣ አርክቴክቸር
      ተማሪ ነዎት?
በጠቅላላ ኮንስትራክሽን የተሰማሩ ባለሙያ ነዎት?
በአማርኛ እና እንግሊዘኛ የሌክቸር ትምህርቶች፣ መፅሀፍቶች፣ ቪድዮዎች እና ጠቃሚ የኮንስትራክሽን እውቀቶች ለማግኝት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉን

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያዎች፣
የሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች፣
እጅግ ጠቃሚ የኮንስትራክሽን መረጃዎች፣
በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ሌክቸር የምታገኙበት

እንግዲያውስ ለርስዎ የሚሆን ምርጥ እና ጠቃሚ  ቻናል እንጠቁመዎት

Join us :-

on Telegram

https://t.me/ethioengineers1
https://t.me/ethioengineers1

on tiktok

tiktok.com/@ethiocons
tiktok.com/@ethiocons
22.2K viewsAyu, edited  13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ