Get Mystery Box with random crypto!

Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የሰርጥ አድራሻ: @ayuzehabeshaofficial
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 181.69K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2024-04-16 12:48:25 ከአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ በኋላ በኦሮሚያ ክልል በህቡዕ ተላልፏል የተባለውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ገደብ ጥሪን ተከትሎ በአንዳንድ አከባቢዎች ላይ የትራንስፖርት ፍሰት መስተጓጐል ቢያጋጥምም በአብዛኛው ሰላማዊ እንቅስቃሴ አለ

ባለፈው ሳምንት በትውልድ ቀዬያቸው መቂ የተገደሉት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ በኋላ በኦሮሚያ ክልል በህቡዕ ተላልፏል የተባለውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ገደብ ጥሪን ተከትሎ አንዳንድ አከባቢዎች ላይ የትራንስፖርት ፍሰት መስተረጓጎል ሲያጋጥም በሌሎች አከባቢዎች ደግሞ እንቅስቃሴው በመደበኛ ሁኔታ ስለመቀጠሉ ተገልጿል፡፡

ከባለፈው ቅዳሜ ሚያዚያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በውል ከማይታወቅ አካል ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል በተባለው በዚህ ጥሪ መሰረት ከከተሞች ወደ ከተሞች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲገቱ መጠየቁን ማህበረሰቡ በስጋት ያነሳዋል፡፡ መሰል የእንቅስቃሴ ገደቦች እስካሁንም በኑሮ ውድነት፣ በግጭት እና ስራ አጥነት የተፈተነውን የማህበረሰቡን ህይወት ይብልጥ እንደምፈትንም እየተገለጸ ነው፡፡

ትናንት ማምሻውን ከአዲስ አበባ ወደ ሃዋሳ በሞጆ፣ ባቱ እና ሻሸመኔ በኩል በርካታ የኦሮሚያ ክልል ከተሞችን አቆራርጠው ወደ ሃዋሳ ለስራ ያቀኑት ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ በዚህ መስመር ከመደበኛ ጋር የተጠጋ የትራንስፖርት ፍሰት ማስተዋላቸውን አንስተዋል፡፡ “መንገድ አንግዲህ አንዳንዶቹ ክፍት ነው ይላሉ አንዳንዶቹ ግን እንደወትሮ አይደለም ይላሉ፡፡ እኔ ግን ትናንት ከአዲስ አበባ ወደ ሃዋሳ ስመጣ ምንም ያስተዋልኩት ችግር የለም፡፡ በመደበኛ እንቅስቃሴ ነው የመጣሁት፡፡ አሁን ዛሬም ከሻሸመኔ ወደ አዳማ የሄዱ ጓደኞቼ ነበሩ መቂ ላይ ካለው መጠነኛ ስጋት ውጪ በሰላም ገብተዋል” ብለዋል፡፡

ሌላው በትናንትናው እለት ከሀዋሳ በዚሁ ተመሳሳይ መስመር ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ አስተያየት ሰጪም የተለመደው የትራንስፖርት ፍሰት ማስተዋላቸውን ገልጸው፤ ከትናንሽ የግል ተሽከርካሪዎች እስከ ትላልቅ የህዝብ ማመላለሻ ባሶች እና የጭነት ተሽከርካሪዎች ስጓዙ መመልከታቸውን አስረድተዋል፡፡ “እኛ በመጣንበት ከሃዋሳ ወደ ባቱ በዚያም በፍጥነት መንገድ በኩል ምንም አላየንም፡፡ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ነው አዲስ አበባ የገባነው፡፡ ትላልቅ የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ጨምሮ ሁሉም ስሄድ ተመልክተናል” ነው ያሉት፡፡

ጥሪው ቀርቧል ከተባለበት ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስከዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ወዳሉ ከተሞችም መደበኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ስደረግ ሰንብቷል፡፡ ከዚህም መስመር አልፎ ከአዳማ ወደ አሰላ እና ከአሰላ ወደ በቆጂ ያለውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ይዞታ የጠየቅናቸው አንድ የበቆጂ ከተማ ነዋሪ እንዳሉት፡ “ባለፈው ሳምንት አከባቢ በነዳጅ እጥረት ነው በሚል ከተስተጓጎለው መደበኛ ፍሰት ውጪ ባሁኑ ዛሬንም ጨምሮ ትራንስፖርት በመደበኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ነው” ይላሉ፡፡

ከምዕራብ ኦሮሚያ ነቀምቴ ከተማ አስተያየታቸውን የሰጡን ነዋሪ ደግሞ “ከተማ ውስጥ የባጃጅ እንቅስቃሴ አለ መደበኛ ነው፡፡ ምንም ከተለመደ ውጪ የሆነ ነገር የለም፡፡ ግን ከከተማ ወደ ከተማ መንቀሳቀስ አስቸጋሪ ነው፡፡ አሁን ምዕራብ ወለጋ ባለሚ በምትባል ከተማ መኪና ስለመቃጠል ሰምተናል” ብለዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ተነስተው በሲሚንቶ ግብዓቶቿ ወደ ምትታወቀው የምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ የምንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች እንደወትሮ መንገድ ላይ ባይታዩና የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርትም መንገድ ላይ በዝተው እንደወትሮ ባይስተዋሉም መንገድ ግን ክፍት ነው ይላሉ፡፡ “መንገድ ክፍት ነው ዛሬ ነው ወደ እንጭኒ ከተማ የመጣሁት፡፡ ግን እንደ ወትሮ አይደለም፡፡ ይህን የትራንስፖርት ገደብ ስባል እንጂ ማን እንደሚጠራው አናውቅም፡፡ አሁን ዛሬ በተለይ ከተለመደው እንቅስቃሴው ቀንሷል” ነው ያሉት፡፡
#ዶቼቨሌ #አዩዘሀበሻ
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
21.2K viewsAyu, edited  09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 12:47:34
18.8K viewsAyu, 09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 12:27:59
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ማጀቴ ዙሪያ እንዲሁም በኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ ዙሪያ በርግቢ በሚባል ቦታ ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች እና በፋኖ ሀይሎች መካከል እስከ ትናንት ድረስ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ከባድ የተባለ ውጊያ ማድረጋቸውን ነዋሪዎቹ ገልፀውልኛል። በነበረው ውጊያ በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ደርሷል ብለዋል። ዛሬ ተኩሱ በመጠኑ ጋብ ብሏል ብለዋል[አዩዘሀበሻ]።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
20.2K viewsAyu, edited  09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 12:27:43
አለምን እያነጋገረ ያለ ድንቅ የ ቴክኖሎጂ ምርት

በጥቂት ጊዜያት ዉስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘዉ ተች ሴንሰር የተገጠመለት ተቆጥረዉ የማያልቁ አገልግሎቶችን ከስልክ ጋር ተገናኝቶ መስጠት የሚችለዉ W26 pro max ለእናንተ

W26 PRO MAX Special with
Earbuds

ለወንድም ለሴትም የሚሆን ዘረፈ ብዙ ጥቅምች ያሉት smartwach ከ pro wireless earpode ጋር

   የራሱ ቻርጀር እና power bank ያለዉ
የልብ ምትዋን  ይለካል
ስፖርት ስንሰራ ምን ያህል ካሎሪ እንዳቃጠልን ያሳውቃል
ብዙ ሰአት ስንተኛ ይቀሰቅሰናል
ስልካችን ሲጠፋ ለመፈለጊያ ያግዘናል
ቴክስት መላክ እንዲሁም መቀበል የሚያስችል
ከስልክ ጋ በ Bluetooth ተገናኝቶ ስልክ መደወል እንዲሁም ማናገር ያቻላል
  wireless charger እና በሁለት አይነት የእጅ መሳርያ የቀርበ
  Blood Oxygen Detection
Stress & Mood Testing

አዲስ አበባ ዉስጥ ነፃ እና ፈጣን  የዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን።

ዋጋ  2199 ብር ብቻ
       ፈጥነዉ ይደዉሉ
0909812211
    +251712148785

  ወይም ስልክና አድራሻዎን
@AAU_Shop  ላይ ይላኩልን።

ተጨማሪ እቃዎችን ለማየት
@AAU_Market ን ይቀላቀሉ።
18.9K viewsAyu, 09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 13:41:35
ራያ በርተክላይ ውጊያ ተከፍቷል
ትናንት ከደቡብ ትግራይ የተፈናቀሉ ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ የሚለውን እንደሽፋን በመጠቀም ትናንት ጀምሮ በራያ በርተክላይ ላዕላይ ዳዩ ቀበሌ የህወሓት ታጣቂዎች ተኩስ መክፈታቸውን መዘገቤ ይታወሳል። ከደቂቃዎች በፊት ወደ አካባቢው ደውዬ የነበረ ሲሆን ትናንት አመሻሹን ተኩሱ ቆሞ የነበረ ቢሆንም ዛሬ 5:00 ጀምሮ በርተክላይ ከፍተኛ ውጊያ መጀመሩን ገልፀውልኛል። የአማራ ክልል አድማብተና እና የህወሓት ታጣቂዎች በዚህ ሰዓት የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በራያ አላማጣ ታኦ በሚባል ቦታ ተኩስ ያለ ሲሆን ሞርተር 82 ፣ አርቢጅ ( ላውንቸር ) እና ዲሽቃ እየተጠቀሙ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቼ ገልፀዋል።
ትናንት በነበረው ተኩስ ንፁሃንን ጨምሮ ከሁለቱም ተዋጊ ሀይሎች በኩል ሰዎች ሞተዋል ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከሁለት ሳምንት በፊት በመቀሌ ተጀምሮ የነበረውን ፖለቲካዊ ውይይት ለማጠናከር ትናንት በአዲስ አበባ ተጨማሪ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ(አዩዘሀበሻ)።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
23.2K viewsAyu, 10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 12:08:41 አሜሪካ በሀገሯ በጊዜያዊነት ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተጨማሪ የመኖሪያ ጊዜ ፈቀደች
በጊዜያዊነት ወደ አሜሪካ የገቡ ኢትዮጵያዊያን ለተጨማሪ 18 ወራት እንዲኖሩ ፈቃድ አግኝተዋል
አሜሪካ በአማራ እና ኦሮሚያ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰትን እንደ ምክንያት ጠቅሳለች
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በነበረበት ወቅት ወደ አሜሪካ በጊዜያዊነት የገቡ ኢትዮጵያዊያን ለ18 ወራት እንዲቆዩ የመኖሪያ ፈቃድ ሰጥታ ነበር፡፡
ለአጭር ጊዜ ቪዛ አግኝተው ለጉብኝት፣ ትምህርት እና ሌሎች ምክንያቶች ወደ አሜሪካ የገቡ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንደሚቸገሩ በወቅቱ አመልክተው ነበር፡፡
አሜሪካም ከኢትዮጵያዊያኑ ሀገራችን ጦርነት እና ሌሎች የፖለቲካ ቀውስ ላይ በመሆኗ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ እንቸገራለን በሚል ለቀረበላት ጥያቄ ለ18 ወራት መኖር እንደሚሉ የመኖሪያ ፈቃድ ሰጥታ ነበር፡፡
ለነዚህ ኢትዮጵያዊያን አመልካቾች የተሰጠው የ18 ወራት ጊዜ የፊታችን ሰኔ ላይ የሚያበቃ የነበረ ሲሆን እነዚህ በጊዜያዊነት ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ለተጨማሪ 18 ወራት እንዲኖሩ እንደተፈቀደላቸው ተገልጿል፡፡
የሀገሪቱ የሀገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ አሁንም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመኖራቸው ምክንያት ለአጭር ጊዜ ወደ አሜሪካ የመጡ ኢትዮጵያዊያን ለተጨማሪ 18 ወራት እንዲኖሩ እንደፈቀደ አስታውቋል፡፡
በአሜሪካ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ከፈረንጆቹ ሰኔ 2024 እስከ ታህሳስ 2025 ድረስ የሚቆዩበት የመኖሪያ ፈቃድ እንደሚሰጡ ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡
አልአይን
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
24.0K viewsAyu, edited  09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 12:01:30
ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ከታየባቸው 5 የአፍሪካ ሀገራት ዉስጥ ተካተተች
ኢትዮጵያን ጨምሮ 5 የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው አዲስ ሪፖርት አስታውቋል።

እኤአ በ 2024 ከፍተኛ የምግብ የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት ከተከሰተባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ዝምባብዌ ፣ ሴራሊዮን ማላዊ ፣ ናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ ከ 1 እስከ 5 ባለው ደረጃ ተቀምጠዋል። በተቋሙ ጥናት መሰረት በኢትዮጵያ የምግብ ሸቀጦች ግሽበቱ 29.4 ደርሷል ብሏል ጥናቱ።

በአብዛኛዎቹ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የዋጋ ግሽበት በአመዛኙ እየቀነሰ መሆኑን ጥናቱ ጠቅሷል።

በተቃራኒው በየአመቱ ባለ ሁለት አሃዝ የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ፣ ማላዊ፣ ናይጄሪያ፣ ሴራሊዮን እና ዚምባብዌ መታየቱን አመላክቷል። በደረጃ ሰንጠረዡ ጋና ፣ አንጎላ ፣ ብሩንዲ ፣ ጋምቢያ እና ጊኒ ከ6 እስከ 10ኛ ደረጃዎች ላይ ተገኝተዋል።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
22.2K viewsAyu, 09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 12:01:14
አለምን እያነጋገረ ያለ ድንቅ የ ቴክኖሎጂ ምርት

በጥቂት ጊዜያት ዉስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘዉ ተች ሴንሰር የተገጠመለት ተቆጥረዉ የማያልቁ አገልግሎቶችን ከስልክ ጋር ተገናኝቶ መስጠት የሚችለዉ W26 pro max ለእናንተ

W26 PRO MAX Special with
Earbuds

ለወንድም ለሴትም የሚሆን ዘረፈ ብዙ ጥቅምች ያሉት smartwach ከ pro wireless earpode ጋር

   የራሱ ቻርጀር እና power bank ያለዉ
የልብ ምትዋን  ይለካል
ስፖርት ስንሰራ ምን ያህል ካሎሪ እንዳቃጠልን ያሳውቃል
ብዙ ሰአት ስንተኛ ይቀሰቅሰናል
ስልካችን ሲጠፋ ለመፈለጊያ ያግዘናል
ቴክስት መላክ እንዲሁም መቀበል የሚያስችል
ከስልክ ጋ በ Bluetooth ተገናኝቶ ስልክ መደወል እንዲሁም ማናገር ያቻላል
  wireless charger እና በሁለት አይነት የእጅ መሳርያ የቀርበ
  Blood Oxygen Detection
Stress & Mood Testing

አዲስ አበባ ዉስጥ ነፃ እና ፈጣን  የዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን።

ዋጋ  2199 ብር ብቻ
       ፈጥነዉ ይደዉሉ
0909812211
    +251712148785

  ወይም ስልክና አድራሻዎን
@AAU_Shop  ላይ ይላኩልን።

ተጨማሪ እቃዎችን ለማየት
@AAU_Market ን ይቀላቀሉ።
19.9K viewsAyu, 09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 11:50:32 ኢምግሬሽን ለምሰሩ ቀና ትብብራችሁን እሻለሁ
ኢምግሬሽን ውክልና አንቀበልም በማለቱ ብዙ ሰዎች እየተንገላቱ መሆኑን ትናንት መዘገቤ ይታወሳል
አንድ የአዩዘሀበሻ አባል የሚከተለውን ልኮልኛል
የሚገርምህ እኔ በሥራ ጉዳይ አዲስ አበባ ነው የምኖረው ባለቤቴ ደግሞ በሥራ ጉዳይ ትግራይ አዲግራት ዪኒቨርስቲ ሌክቸር ነች እና ስኮላርሽፕ ለሞምላት ያለፈው ሕዳር አሻራ ለመስጠት እርጉዝ ስለ ነበረች አየር ትኬት ወደ 10,000.00 ብር ወጪ አውጥተን እዚህ መጥታ አሻራ ሞልታ ተመልሳ ፖስፓርቱን ለመውሰድ ስለ ውክልና ምንም ኢንፎርሜሽን ስላልሰጡን በአዲግራት ፍርድ ቤት ውክልና አሰርታ ልካልኝ በስንት መከራ ሰልፍ ተሰልፌ ፖስፓርቷ ለመውሰድ ስጠይቅ አይቻልም አሉኝ። ድጋሜ እንዳትመጣ በቅርቡ ወልዳለች እንዳትቆይ ደግሞ በዪኒቨርስቲው ስኮላር ዕድል መጣላት እና እባክህ ተባበረኝ። የፍርድ ቤት ውክልና ደግሞ አንቀበልም ይላሉ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ለዕግድ የሚሰራ ለውክልና ለምን አይሰራም?
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ከስር ባለው ሊንክ ይፃፉልን
http://t.me/ayulaw http://t.me/ayulaw
18.7K viewsAyu, edited  08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 11:37:28
"የኢራን ጥቃት 99% ከሽፏል:-እስራኤል
ብዙ የተወራለት የኢራን አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች በትናንቱ ጥቃት ምንም ሳይሰሩ መክሸፋቸው አለምን እያነጋገረ ነው።
ኢራን ትናንት ምሽት ከ300 በላይ ሰው አልባ ድሮኖች እና ሚሳኤሎችን ነበር እስራኤልን ለመምታት ያስወነጨፈችው።  ይህን ተከትሎ እስራኤል የኢራንን ጥቃት "አይረን ዶም" በተሰኘው ማምከኛ 99% ጥቃት ሳያደርሱ አየር ባየር አክሽፈናል ብላለች።
በጥቃቱ 12 ሰዎች ሲቆስሉ በአንድ ወታደራዊ ቤዝ ላይ መጠነኛ ጉዳት ከማድረስ ባለፈ ሌላ ያደረሰው ጉዳት የለም ሲል የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ  ተናግረዋል።
የኢራኑ ቃል አቀባይ በበኩሉ "ጥቃታችንን በሚገባ ፈፅመናል፣ ከዚህ በኋላ ሌላ ጥቃት ላይኖር ይችላል" ሲሉ ገልፀዋል።
እስራኤል በበኩሏ የአፀፋ መልስ እንደምትሰጥ ዝታለች።
በነገራችን ላይ የኢራን ድሮኖች ከኢራን ተነስተው እስራኤል ለመድረስ በትንሹ ሰባት ሰዓታትን ይፈጃል[አዩዘሀበሻ]።
ቪዲዮ:- እስራኤል የኢራንን ጥቃት ስታከሽፍ
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
19.6K viewsAyu, edited  08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ