Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ከታየባቸው 5 የአፍሪካ ሀገራት ዉስጥ ተካተ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ከታየባቸው 5 የአፍሪካ ሀገራት ዉስጥ ተካተተች
ኢትዮጵያን ጨምሮ 5 የአፍሪካ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው አዲስ ሪፖርት አስታውቋል።

እኤአ በ 2024 ከፍተኛ የምግብ የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት ከተከሰተባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ዝምባብዌ ፣ ሴራሊዮን ማላዊ ፣ ናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ ከ 1 እስከ 5 ባለው ደረጃ ተቀምጠዋል። በተቋሙ ጥናት መሰረት በኢትዮጵያ የምግብ ሸቀጦች ግሽበቱ 29.4 ደርሷል ብሏል ጥናቱ።

በአብዛኛዎቹ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የዋጋ ግሽበት በአመዛኙ እየቀነሰ መሆኑን ጥናቱ ጠቅሷል።

በተቃራኒው በየአመቱ ባለ ሁለት አሃዝ የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ፣ ማላዊ፣ ናይጄሪያ፣ ሴራሊዮን እና ዚምባብዌ መታየቱን አመላክቷል። በደረጃ ሰንጠረዡ ጋና ፣ አንጎላ ፣ ብሩንዲ ፣ ጋምቢያ እና ጊኒ ከ6 እስከ 10ኛ ደረጃዎች ላይ ተገኝተዋል።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial