Get Mystery Box with random crypto!

'የኢራን ጥቃት 99% ከሽፏል:-እስራኤል ብዙ የተወራለት የኢራን አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች በትናንቱ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

"የኢራን ጥቃት 99% ከሽፏል:-እስራኤል
ብዙ የተወራለት የኢራን አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች በትናንቱ ጥቃት ምንም ሳይሰሩ መክሸፋቸው አለምን እያነጋገረ ነው።
ኢራን ትናንት ምሽት ከ300 በላይ ሰው አልባ ድሮኖች እና ሚሳኤሎችን ነበር እስራኤልን ለመምታት ያስወነጨፈችው።  ይህን ተከትሎ እስራኤል የኢራንን ጥቃት "አይረን ዶም" በተሰኘው ማምከኛ 99% ጥቃት ሳያደርሱ አየር ባየር አክሽፈናል ብላለች።
በጥቃቱ 12 ሰዎች ሲቆስሉ በአንድ ወታደራዊ ቤዝ ላይ መጠነኛ ጉዳት ከማድረስ ባለፈ ሌላ ያደረሰው ጉዳት የለም ሲል የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ  ተናግረዋል።
የኢራኑ ቃል አቀባይ በበኩሉ "ጥቃታችንን በሚገባ ፈፅመናል፣ ከዚህ በኋላ ሌላ ጥቃት ላይኖር ይችላል" ሲሉ ገልፀዋል።
እስራኤል በበኩሏ የአፀፋ መልስ እንደምትሰጥ ዝታለች።
በነገራችን ላይ የኢራን ድሮኖች ከኢራን ተነስተው እስራኤል ለመድረስ በትንሹ ሰባት ሰዓታትን ይፈጃል[አዩዘሀበሻ]።
ቪዲዮ:- እስራኤል የኢራንን ጥቃት ስታከሽፍ
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial