Get Mystery Box with random crypto!

ኢምግሬሽን ለምሰሩ ቀና ትብብራችሁን እሻለሁ ኢምግሬሽን ውክልና አንቀበልም በማለቱ ብዙ ሰዎች | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

ኢምግሬሽን ለምሰሩ ቀና ትብብራችሁን እሻለሁ
ኢምግሬሽን ውክልና አንቀበልም በማለቱ ብዙ ሰዎች እየተንገላቱ መሆኑን ትናንት መዘገቤ ይታወሳል
አንድ የአዩዘሀበሻ አባል የሚከተለውን ልኮልኛል
የሚገርምህ እኔ በሥራ ጉዳይ አዲስ አበባ ነው የምኖረው ባለቤቴ ደግሞ በሥራ ጉዳይ ትግራይ አዲግራት ዪኒቨርስቲ ሌክቸር ነች እና ስኮላርሽፕ ለሞምላት ያለፈው ሕዳር አሻራ ለመስጠት እርጉዝ ስለ ነበረች አየር ትኬት ወደ 10,000.00 ብር ወጪ አውጥተን እዚህ መጥታ አሻራ ሞልታ ተመልሳ ፖስፓርቱን ለመውሰድ ስለ ውክልና ምንም ኢንፎርሜሽን ስላልሰጡን በአዲግራት ፍርድ ቤት ውክልና አሰርታ ልካልኝ በስንት መከራ ሰልፍ ተሰልፌ ፖስፓርቷ ለመውሰድ ስጠይቅ አይቻልም አሉኝ። ድጋሜ እንዳትመጣ በቅርቡ ወልዳለች እንዳትቆይ ደግሞ በዪኒቨርስቲው ስኮላር ዕድል መጣላት እና እባክህ ተባበረኝ። የፍርድ ቤት ውክልና ደግሞ አንቀበልም ይላሉ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ለዕግድ የሚሰራ ለውክልና ለምን አይሰራም?
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ከስር ባለው ሊንክ ይፃፉልን
http://t.me/ayulaw http://t.me/ayulaw