Get Mystery Box with random crypto!

Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የሰርጥ አድራሻ: @ayuzehabeshaofficial
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 181.36K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2024-04-16 15:09:20
የራያ አላማጣ ከተማ የብልፅግና ፅ/ቤት ሃላፊ የነበሩት አቶ ሞላ ደርበው የህወሓት ታጣቂዎች ወደ አላማጣ ከተማ መጠጋታቸውን ተከትሎ ትናንት የቅርብ ጓዶቹን ይዞ ወደ ቆቦ በመሸሽ ላይ እያለ ከአላማጣ ከተማ በ5 km ርቀት ላይ አየር ማረፊያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ማን እንደገደለው ባይታወቅም ምሽት አካባቢ በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል ሲሉ የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል[አዩዘሀበሻ]።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
21.3K viewsAyu, edited  12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 14:47:24 የኤርትራ መግለጫ
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር፣ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር "ፈጽሞ ሊቀየር በማይችል ኹኔታ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሠምሯል" ሲል ከሁለት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ገልጿል
መግለጫው፣ ባኹኑ ወቅት በኹለቱ አገሮች መካከል ያለው ድንበር፣ በዓለማቀፉ የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ መሠረት "ባግባቡ የሚታወቅ እና በሕግ የተረጋገጠ ድንበር" መኾኑን ጠቅሷል። በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች ወይም በኤርትራ እና ትግራይ ሕዝቦች መካከል የሕግ ጥሰት ካልኾነ በስተቀር ሌላ ምንም ዓይነት ግጭት የሚያስነሳ ጉዳይ እንደሌለ በመግለጫዋ የጠቀሰችው ኤርትራ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከፍተኛ ውድመት ካስከተለው የኹለቱ አገሮች የድንበር ጦርነት ትልቅ ትምህርት ወስዷል ብላለች።
ሰሞኑን የኤርትራ ጦር የኢሮብ ተወላጆችን ማንነታቸውን ኤርትራዊ ብለው እንዲቀይሩ እና በኤርትራ ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሳተፉ እያስገደዱ መሆኑንና ወደ ብሄራዊ ግዳጅ አንሄድም ያሉ ሰዎችንም እያሰሩ መሆኑን አዩዘሀበሻ ከቀናት በፊት መዘገቡ ይታወሳል።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
21.7K viewsAyu, edited  11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 14:22:23
የታጠቁ ሀይሎች እና አስተዳደሮች እንዲፈርሱ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ተስማምተናል:-ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፀጥታና ሰላም  ምክር ቤት ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ ከደቂቃዎች በፊት ለመገናኛ ብዙሃን በትግርኛ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሌ/ጀኔራል ታደሰ ወረዳ በምዕራብ፣ ፀለምትና ደቡብ ትግራይ በግዳጅ በተያዙ አካባቢዎች የተቋቋሙ የታጠቁ ሃይሎች እና አስተዳደሮች እንዲፈርሱ ከፌደራል መንግስት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።
የፕሪቶሪያ ስምምነት ጊዜያዊ አማራጭ ሳይሆን የእኛ ስትራቴጂያዊ ምርጫ ነው ሲሉ መናገራቸውን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልፀዋል[አዩዘሀበሻ]።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
21.8K viewsAyu, edited  11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 14:13:01
በአዲስ አበባ የሚገኙ እድሮች እንዲመዘገቡ የሚያስገድድ ረቂቅ መመሪያ ወጣ
የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ እድሮች እንዲመዘገቡ የሚያስገድድ ረቂቅ መመሪያ መውጣቱን አስታውቋል።

በአዋጅ ቁጥር 74 /2014 የወጣውን የእድሮች አዋጅ በ84/2016 ተሻሽሎ ለማስፈፀሚያ መመሪያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶለታል።

መመሪያው እድሮች ቀብር ከማስፈፀም ባለፈ አባሎቻቸውን እንዲያገለግሉ፣ ከመንግስት ጋር በቅርበት እንዲሰሩ፣ አባሎቻቸውን እንዲያበዙ እና ህጋዊ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ ያግዛል ተብሏል።

እድር ያለው ማህበራዊ ፋይዳ ትልቅ በመሆኑ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ይሰራልም ነው የተባለው።

የእድሮችና የእድር ምክር ቤቶች የምዝገባና የእድሳት አሰጣጥ መመሪያ 151/2016 ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
21.2K viewsAyu, edited  11:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 13:57:55
በኮሪደር ልማት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ሆኑ
በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ምክንያት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጋቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከደጃች ውቤ በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

• ከዳኑ ሆስፒታል እስከ ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

• ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ሥራዎች ምክንያት ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በጥብቅ መከልከሉን ፖሊስ አሳስቧል።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
20.5K viewsAyu, edited  10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 13:49:03
ታዋቂው ጳጳስ በጩቤ ተወጉ
NB:- ምስሉ ሊረብሽ ይችላል
ታዋቂው  የኤሲሪያን  (አሶራውያን) ኦርቶዶክስ ቄስ ብጹዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል (ቢሾፕ ማር ማሪ) ሲድኒ ውስጥ በዘውትራዊውና የተመለደው ቀጥታ የሚሰራጭ  የስብከት መርሃ ግብራቸው ላይ ሳሉ ማንም ባልገመተው ሁኔታ አንድ ሰው በፍጥነት ተጠግቶ በጩቤ ፊትና አንገታቸው ላይ ወግቷቸዋል።

የጉባኤው አባላት ጳጳሱን ለመርዳት ሲጮሁ እና ሲጣደፉ ይሰማሉ።

አንድ ሰው በቁጥጥር ስር መዋሉን የኒው ሳውዝ ዌልስ ፖሊስ አስታውቋል።

በጥቃቱ አራት ሰዎች ቆስለዋል ሲል ኒው ሳውዝ ዌልስ ዘግቧል።
በፅኑ ህሙማን መርጃ ውስጥ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
20.1K viewsAyu, edited  10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 13:09:11
እስካሁን በ10 ሺህ የሚቆጠሩ የአላማጣና ኮረምነዋሪዎች ተፈናቅለዋል
ሰሞኑን በራያ አላማጣ ወረዳ ከትግራይ ክልል የተነሱ ታጣቂዎች ተኩስ በመክፈታቸው እና ወደ አላማጣ በመጠጋታቸው ምክንያት በ10ሺህ የሚቆጠሩ የአላማጣና ኮረም ነዋሪዎች ወደ ቆቦና ሰቆጣ ተፈናቅለዋል።
አንድ ከአላማጣ ከተማ ትናንት ወደ ቆቦ እንደተፈናቀሉ የነገሩን ተፈናቃይ እንዴት ናችሁ ያለን አካል የለም፣ በየበረንዳውና በየመንገዱ ተበትነናል ብለዋል። በመንገድ ላይ ከየት እንደተተኮሰ በማይታወቅ ጥይት ተመትተው የሞቱ ሠዎች እንዳሉም አመልክተዋል።
እንደ አስተያየት ሰጪው 10ሺህ ያክል ሰዎች ከአላማጣ ቆቦ ገብተዋል። እንደዚሁም ከኮረም ከተማ የሚፈናቀሉ ሠዎች ሰቆጣ ከተማ መግባታቸውን ትናንት ከቦታው የደረሱ ተፈናቃይ ተናግረዋል። በቆቦ እና በአላማጣ መካከል በምትገኘው ዋጃ ላይ የፀጥታ አካላት አባላት ተፈናቃዮችን አትሂዱ እያሉ ሲመልሷቸው መመልከታቸውንም ገልፀዋል። ቆቦ በተፈናቃዮች ተጨናንቃለች ብለዋል።
የወሎ አማራ የማንነትና ወሰን አስመላሽ ሊቀመንበርና የዓላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ „ምንም እንኳ የትግራይ ተዋጊዎች ከተሞችን መቆጣጠር ባይችሉም ከአላማጣ ከተማ አቅራቢያ ባሉ ተራራዎች ላይ አሉ” ብለዋል። ህብረተሰቡም ያለውን ሥጋት በመፍራት እየተፈናቀለ እንደሆነ ገልፀዋል።
ፎቶ:-የህወሓት ታጣቂዎች እንቅስቃሴ ከቦታው
አዩዘሀበሻ
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
20.8K viewsAyu, edited  10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 12:56:32 በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የሳል ሽሮፕን መድኃኒት ከገበያ ላይ እንዲሰበሰብ መመሪያ ሰጡ
እ.ኤ.አ በ 2021 በጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተመረተው የህፃናት ሳል ሽሮፕ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት የመድኃኒት ባለስልጣናት ከገበያዉ ላይ እንዲሰበሰብ ተደርጓል፡፡

ይህ የሆነው የናይጄሪያ መድሃኒት ኤጀንሲ ከፍተኛ መጠን ያለው መርዛማ እና ለሞት ሊዳርግ የሚችል ንጥረ ነገር እንደያዘ ካስጠነቀቀ በኋላ ነው።በታንዛኒያ እና በዚምባብዌ የሚገኙ የመድኃኒት ተቆጣጣሪዎች ሽሮፑ ላይ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወሰድ በቅርቡ የጠየቁ ሲሆኑ የዚምባብዌ የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ሽሮፕ ወደ ሀገር ውስጥ ስለመግባቱ ምንም አይነት ማስረጃ የለም ግን ብሏል ።

ባለፈው ሳምንት የናይጄሪያ ብሔራዊ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር እና ቁጥጥር ኤጀንሲ (ናፍዳክ) በሽርፑ ውስጥ ዲቲሊን ግላይኮልን የተባለ መርዛማ ንጥረ ነገር እንዳለ በላብራቶሪ ከተረጋገጠ በኃላ የቤኒሊን የሕፃናት ሕክምና ሽሮፕ ከገበያዉ ላይ እንዲሰበሰብ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ይህንኑ ተከትሎ ከጥቂት ቀናት በኋላ የኬንያ ፋርማሲ ቦርድ በናፍዳክ ምክር መሰረት የሽሮፑ ሽያጭ እንዲቆም ትዕዛዝ መሰጠቱ ተዘግቧል።

ከዚያም በደቡብ አፍሪካ እና በሩዋንዳ የመድኃኒት ባለስልጣናት ተከታትለዉ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ሽሮፑ እንዲሰበሰብ አዘዋል፡፡ዲቲሊን ግላይኮል በካሜሩን እና በጋምቢያ ውስጥ በቅርብ ጊዜ በደርዘን የሚቆጠሩ ህጻናት የሞት ምክንያት ሆኗል፡፡የሰው ልጅ ንጥረ ነገሩን መጠቀሙ በርካታ የጎንዮሽ ጉዳት የሚያስከትልበት ሲሆን አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳትን ጨምሮ ፣  ለሞት ሊዳርግ ይችላል።

ቤኒሊን የሕፃናት ሕክምና ሽሮፕ፣ ባች ቁጥር 329304 በደቡብ አፍሪካ በግንቦት 2021 የተመረተ ሲሆን ሚያዝያ 2024 የሚያበቃበት ቀን እንደሆነ ያለዉ ማስረጃ ያመላክታል፡፡የደቡብ አፍሪካው የመድኃኒት መቆጣጠሪያ ቡድን ባች 329303 መድኃኒቶች  በደቡብ አፍሪካ፣ ኢስዋቲኒ፣ ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ናይጄሪያ ተሽጠዋል።
#ዳጉ ጆርናል
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
20.7K viewsAyu, edited  09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 12:56:31
19.2K viewsAyu, 09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 12:48:25 ከአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ በኋላ በኦሮሚያ ክልል በህቡዕ ተላልፏል የተባለውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ገደብ ጥሪን ተከትሎ በአንዳንድ አከባቢዎች ላይ የትራንስፖርት ፍሰት መስተጓጐል ቢያጋጥምም በአብዛኛው ሰላማዊ እንቅስቃሴ አለ

ባለፈው ሳምንት በትውልድ ቀዬያቸው መቂ የተገደሉት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ በኋላ በኦሮሚያ ክልል በህቡዕ ተላልፏል የተባለውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ገደብ ጥሪን ተከትሎ አንዳንድ አከባቢዎች ላይ የትራንስፖርት ፍሰት መስተረጓጎል ሲያጋጥም በሌሎች አከባቢዎች ደግሞ እንቅስቃሴው በመደበኛ ሁኔታ ስለመቀጠሉ ተገልጿል፡፡

ከባለፈው ቅዳሜ ሚያዚያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በውል ከማይታወቅ አካል ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል በተባለው በዚህ ጥሪ መሰረት ከከተሞች ወደ ከተሞች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲገቱ መጠየቁን ማህበረሰቡ በስጋት ያነሳዋል፡፡ መሰል የእንቅስቃሴ ገደቦች እስካሁንም በኑሮ ውድነት፣ በግጭት እና ስራ አጥነት የተፈተነውን የማህበረሰቡን ህይወት ይብልጥ እንደምፈትንም እየተገለጸ ነው፡፡

ትናንት ማምሻውን ከአዲስ አበባ ወደ ሃዋሳ በሞጆ፣ ባቱ እና ሻሸመኔ በኩል በርካታ የኦሮሚያ ክልል ከተሞችን አቆራርጠው ወደ ሃዋሳ ለስራ ያቀኑት ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ በዚህ መስመር ከመደበኛ ጋር የተጠጋ የትራንስፖርት ፍሰት ማስተዋላቸውን አንስተዋል፡፡ “መንገድ አንግዲህ አንዳንዶቹ ክፍት ነው ይላሉ አንዳንዶቹ ግን እንደወትሮ አይደለም ይላሉ፡፡ እኔ ግን ትናንት ከአዲስ አበባ ወደ ሃዋሳ ስመጣ ምንም ያስተዋልኩት ችግር የለም፡፡ በመደበኛ እንቅስቃሴ ነው የመጣሁት፡፡ አሁን ዛሬም ከሻሸመኔ ወደ አዳማ የሄዱ ጓደኞቼ ነበሩ መቂ ላይ ካለው መጠነኛ ስጋት ውጪ በሰላም ገብተዋል” ብለዋል፡፡

ሌላው በትናንትናው እለት ከሀዋሳ በዚሁ ተመሳሳይ መስመር ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ አስተያየት ሰጪም የተለመደው የትራንስፖርት ፍሰት ማስተዋላቸውን ገልጸው፤ ከትናንሽ የግል ተሽከርካሪዎች እስከ ትላልቅ የህዝብ ማመላለሻ ባሶች እና የጭነት ተሽከርካሪዎች ስጓዙ መመልከታቸውን አስረድተዋል፡፡ “እኛ በመጣንበት ከሃዋሳ ወደ ባቱ በዚያም በፍጥነት መንገድ በኩል ምንም አላየንም፡፡ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ነው አዲስ አበባ የገባነው፡፡ ትላልቅ የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ጨምሮ ሁሉም ስሄድ ተመልክተናል” ነው ያሉት፡፡

ጥሪው ቀርቧል ከተባለበት ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስከዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ወዳሉ ከተሞችም መደበኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ስደረግ ሰንብቷል፡፡ ከዚህም መስመር አልፎ ከአዳማ ወደ አሰላ እና ከአሰላ ወደ በቆጂ ያለውን የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ይዞታ የጠየቅናቸው አንድ የበቆጂ ከተማ ነዋሪ እንዳሉት፡ “ባለፈው ሳምንት አከባቢ በነዳጅ እጥረት ነው በሚል ከተስተጓጎለው መደበኛ ፍሰት ውጪ ባሁኑ ዛሬንም ጨምሮ ትራንስፖርት በመደበኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ነው” ይላሉ፡፡

ከምዕራብ ኦሮሚያ ነቀምቴ ከተማ አስተያየታቸውን የሰጡን ነዋሪ ደግሞ “ከተማ ውስጥ የባጃጅ እንቅስቃሴ አለ መደበኛ ነው፡፡ ምንም ከተለመደ ውጪ የሆነ ነገር የለም፡፡ ግን ከከተማ ወደ ከተማ መንቀሳቀስ አስቸጋሪ ነው፡፡ አሁን ምዕራብ ወለጋ ባለሚ በምትባል ከተማ መኪና ስለመቃጠል ሰምተናል” ብለዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ተነስተው በሲሚንቶ ግብዓቶቿ ወደ ምትታወቀው የምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ የምንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች እንደወትሮ መንገድ ላይ ባይታዩና የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርትም መንገድ ላይ በዝተው እንደወትሮ ባይስተዋሉም መንገድ ግን ክፍት ነው ይላሉ፡፡ “መንገድ ክፍት ነው ዛሬ ነው ወደ እንጭኒ ከተማ የመጣሁት፡፡ ግን እንደ ወትሮ አይደለም፡፡ ይህን የትራንስፖርት ገደብ ስባል እንጂ ማን እንደሚጠራው አናውቅም፡፡ አሁን ዛሬ በተለይ ከተለመደው እንቅስቃሴው ቀንሷል” ነው ያሉት፡፡
#ዶቼቨሌ #አዩዘሀበሻ
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
21.2K viewsAyu, edited  09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ