Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የሚገኙ እድሮች እንዲመዘገቡ የሚያስገድድ ረቂቅ መመሪያ ወጣ የአዲስ አበባ ሴቶች፣ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

በአዲስ አበባ የሚገኙ እድሮች እንዲመዘገቡ የሚያስገድድ ረቂቅ መመሪያ ወጣ
የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ እድሮች እንዲመዘገቡ የሚያስገድድ ረቂቅ መመሪያ መውጣቱን አስታውቋል።

በአዋጅ ቁጥር 74 /2014 የወጣውን የእድሮች አዋጅ በ84/2016 ተሻሽሎ ለማስፈፀሚያ መመሪያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶለታል።

መመሪያው እድሮች ቀብር ከማስፈፀም ባለፈ አባሎቻቸውን እንዲያገለግሉ፣ ከመንግስት ጋር በቅርበት እንዲሰሩ፣ አባሎቻቸውን እንዲያበዙ እና ህጋዊ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ ያግዛል ተብሏል።

እድር ያለው ማህበራዊ ፋይዳ ትልቅ በመሆኑ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ይሰራልም ነው የተባለው።

የእድሮችና የእድር ምክር ቤቶች የምዝገባና የእድሳት አሰጣጥ መመሪያ 151/2016 ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial