Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ በዓመት 46 ሚሊየን ሕዝብ ሊመግብ የሚችል ምግብ እየባከነ ነው ተባለ የግብርና ሚኒስቴ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

በኢትዮጵያ በዓመት 46 ሚሊየን ሕዝብ ሊመግብ የሚችል ምግብ እየባከነ ነው ተባለ
የግብርና ሚኒስቴር አዲስ ያስተዋወቀው የግብርና ምርቶች አስተዳደርና አመራር ስትራቴጂ በኢትዮጵያ በየዓመቱ 474 ነጥብ 67 ቢሊየን ብር የሚያወጣ የምርት ብክነት መኖሩን አመላከተ።

ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም ብክነትን ለማስቀረት ሲሠራበት የቆየው ስትራቴጂ እህልና ጥራጥሬ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፥ አዲሱ ስትራቴጂ ተጨማሪ ሁለት ዘርፎችን አካቷል።

በእንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦ፣ በጥራጥሬ፣ በዕፅዋትና በሰብል ምርቶች በዓመት 46 ሚሊየን ሕዝብ ሊመግብ የሚችል ምግብ እየባከነ መሆኑንም አመላክቷል።

በየዓመቱ 161 ነጥብ 74 ቢሊየን ብር የሚያወጣ የሥጋና ወተት ምርቶች ብክነት እያጋጠመ መሆኑንም ጠቅሷል።

በተጨማሪም 312 ነጥብ 93 ቢሊየን ብር የሚያወጡ የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬዎች፣ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች እየባከኑ መሆኑም ነው የገለጸው።

የሃገሪቱን የምግብ ዋስትናና ሥነ ምግብ ሥርዓት ደኅንነት ከማረጋገጥ፣ ለግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች ቀጣይነት ያለው ጥሬ ዕቃዎች ከማቅረብ፣ የወጪ ንግድን ከማበረታታት፣ የሥራ ዕድል ከማሳደግና ሁሉን አቀፍ የሆነ ሃገራዊ የልማት ስትራቴጂ ከመከተል አንፃር የግብርና ምርቶች ብክነት አስተዳደር ጉዳይ ችላ ተብሎ የቆየ መሆኑን ጠቅሷል።

እንደ ስትራቴጂው ማብራሪያ እያጋጠመ ያለው ብክነት የምርት ሒደት የሚያቀላጥፉ ግብዓቶችን፥ ማለትም ምርጥ ዘር፣ ውኃ፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ የግብርና ኬሚካሎች፣ መሬት፣ የእንስሳት መኖ እንዲሁም የእንስሳት መድኃኒቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ካለመቻል የመጣ መሆኑን አስረድተዋል።

የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial