Get Mystery Box with random crypto!

የእውነት ሚዛን(ቴቄል)

የቴሌግራም ቻናል አርማ apostolicanswers — የእውነት ሚዛን(ቴቄል)
የቴሌግራም ቻናል አርማ apostolicanswers — የእውነት ሚዛን(ቴቄል)
የሰርጥ አድራሻ: @apostolicanswers
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.77K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ገጽ የተሃድሶን ምንፍቅና በእውነት ሚዛን እየመዘንን ቴቄል እንላለን።
"ቴቄል ማለት፥ በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀለህም ተገኘህ ማለት ነው" (ት. ዳን 5፡27)
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCPLJimNlqTFBnlbsh_vccgg
ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት
@AbuNak
@beorthodox

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-22 20:22:37
306 viewsመሸ በከንቱ, 17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:22:37 Melito the Philosopher, bishop of Sardis
If therefore it might come to pass by the power of your grace, it has appeared right to us your servants that, as you, having overcome death, do reign in glory, so you should raise up the body of your Mother and take her with you, rejoicing, into heaven. Then said the Savior [Jesus]: "Be it done according to your will" (The Passing of the Virgin 16:2-17 [A.D. 300]).
Timothy of Jerusalem
Therefore the Virgin is immortal to this day, seeing that he who had dwelt in her transported her to the regions of her assumption (Homily on Simeon and Anna [A.D. 400]).
Epiphanius, Panarion
“If the Holy Virgin had died and was buried, her falling asleep would have been surrounded with honour, death would have found her pure, and her crown would have been a virginal one...Had she been martyred according to what is written: 'Thine own soul a sword shall pierce', then she would shine gloriously among the martyrs, and her holy body would have been declared blessed; for by her, did light come to the world." 78:23 (A.D. 377)
John the Theologian
The Lord said to his Mother, "Let your heart rejoice and be glad. For every favor and every gift has been given to you from my Father in heaven and from me and from the Holy Spirit. Every soul that calls upon your name shall not be ashamed, but shall find mercy and comfort and support and confidence, both in the world that now is and in that which is to come, in the presence of my Father in the heavens". . . And from that time forth all knew that the spotless and precious body had been transferred to paradise (Falling Asleep of the Holy Mother of God)
308 viewsመሸ በከንቱ, 17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 11:32:08 (የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 9)
----------
31፤ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።

32፤ ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።

ስታንቀላፋ ቅዱሳንን አታይም ክርስቶስንም አታይም ስታቀላፋ ፕሮቴስታንት ትሆናለህ ስትነቃ ቅዱሳንን ታያለህ ፤ክርስቶስን ታያለህ ኦርቶዶክስም ትሆናለህ
ከክርስቶስ ጋ ከሆንክ ቅዱሳንን በሥጋ ከዚህ ምድር የተለዮትን በክብር ታያቸው አለህ
ከክርስቶስ ስትለይ ቅዱሳን ሙተዋል በኛ ዘንድ የሉም ምንም አያውቁም አይናገሩም ምንም አይሠሩም ትላለህ
ከክርስቶስጋ ስትሆን በሥጋ ሞተ ከዚህ የተለዩት ትንቢት ሲናገሩ ታያለህ ።
የፕሮቴስታንቱ ዓለም በእንቅልፍ ውስጥ ስለሆነ በዚህ ቡድን ውስጥ ያለ ሰው ክርስቶስን ማዬት አይችልም ቅዱሳንን ማዬት አይችልም በዚህ ቡድን ውስጥ ያለ ሰው ከክርስቶስ የተለዬ ስለሆነ ክርቶስን አያይም ቅዱሳንን አያይም ።ለዚህም ነው ቅዱሳን ምንም አያቁም በሥጋ ከተለዩ በኋላ አያማልዱም አብረውን አይሆኑም አናያቸውም የሚሉት ምክንያቱም በእንቅልፍ ቅስጥ ናቸው ከክርስቶስም የተለዩ ናቸው ።
እነ ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት በእንቅልፍ ውስጥ ሳሉ ሳይሆን ቅዱሳንን ያዩት ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ነው ።በዚህ መጽሐፍ ከክርስቶስጋ ከሆነን እና በእንቅልፍ ውስጥ ካልሆንን ክርስቶስንም ቅዱሳንንም በክብር ማዬት እንዴምንችል አስረዳን
@felgehaggnew
@felgehaggnew
425 viewsመሸ በከንቱ, 08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 10:57:06 መዳን ከቤተክርስቲያን ውጪ

IGNATIUS OF ANTIOCH

“ወንድሞቼ ሆይ አትሳቱ፡ ማንም ጠብ አጫሪውን [ማለትም ተንኮለኛ ነው] ቢከተል የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስም።
ማንም እንግዳ በሆነ ትምህርት የሚመላለስ ከሆነ [ማለትም መናፍቅ ነው]
በሕማማት [በክርስቶስ] ድርሻ የለውም።
እንግዲህ የምታደርጉትን ሁሉ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንድታደርጉ በአንድ ቁርባን ትጠቀሙ ዘንድ ተጠንቀቁ፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ አንድ ጽዋ በደሙም አንድነት አለና፤
አንድ መሠዊያ፣ አንድ ኤጲስ ቆጶስም እንዳለ፣ ከሊቃነ ጳጳሳትና ከአገልጋዮቼ ከዲያቆናት ጋር” (Letter to the Philadelphians 3:3–4:1 [A.D. 110]).

IRENAEUS

“እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሐዋርያትን፣ ነቢያትን፣ አስተማሪዎችን፣ እና ሌሎች የመንፈስ ሥራዎችን ሁሉ አስቀምጧል፣ ከእነርሱም አንዳቸውም ቢሆኑ ቤተ ክርስቲያንን የማይከተሉ ተካፋዮች አይደሉም።
ነገር ግን በመጥፎ አእምሮ አልፎ ተርፎም በሚብስ አሠራር ራሳቸውን ሕይወትን ያታልላሉ።
ቤተ ክርስቲያን ባለችበት የእግዚአብሔር መንፈስ አለ; የእግዚአብሔር መንፈስ ባለበት ቤተ ክርስቲያንና ጸጋው ሁሉ በዚያ አሉ።”(Against Heresies3:24:1 [A.D. 189]).

CYPRIAN OF CARTHAGE

“ከቤተክርስቲያኑ የተለየ እና ከአመንዝራ ጋር የሚተባበር ከቤተክርስቲያን የተስፋ ቃል ተለይቷል፣ የክርስቶስን ቤተክርስቲያን የሚተው የክርስቶስን ሽልማት አያገኝም። እሱ ባዕድ፣ ዓለማዊ እና ጠላት ነው። ለእናቱ ቤተ ክርስቲያን ላልሆነው አባቱ አምላክ ሊሆነው አይችልም።” (The Unity of the Church 6, 1st ed. [A.D. 251]).
“ለኤጲስ ቆጶሳትና ለካህናቶች መታዘዝን እምቢ ካሉ የሕይወት መንገድ ወይም የመዳን መንገድ እንዳለ አያስቡ፤ እግዚአብሔር በኦሪት ዘዳግም መጽሐፍ እንዲህ ይላልና፡— ለመስማት እንቢ ብሎ የሚኮራ ሁሉ። በዚያም ወራት ማንም ቢሆን ካህኑ ወይም ዳኛው ያ ሰው ይሙት” (ዘዳ. 17፡12። ከዚያም በእርግጥም በሰይፍ ተገድለዋል. . . አሁን ግን ትዕቢተኞች እና ትዕቢተኞች ከቤተክርስቲያን ሲባረሩ በመንፈስ ሰይፍ ተገድለዋል። የእግዚአብሔር ቤት አንድ ብቻ ነውና በውጭ ሊኖሩ አይችሉምና፥ ከቤተክርስቲያንም በቀር ለማንም መዳን አይቻልም። (Letters 61[4]:4 [A.D. 253]).
“በዘላለም ሕይወት እና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የኃጢአት ስርየት ታምናለህን ስንል የኃጢአት ይቅርታ ከቤተክርስቲያን በስተቀር አይሰጥም ማለት ነው”(ibid., 69[70]:2 [A.D. 253]).
“ጴጥሮስ ራሱ አንድነትን እያሳየና እያጸደቀ፣ ከአንዲት ቤተ ክርስቲያን አንዲት ጥምቀት በቀር መዳን እንደማንችል ያዘዘንና አስጠንቅቆናል። እንዲህ ይላል፡- ‘በኖኅ መርከብ ጥቂቶች ማለትም ስምንት ነፍሳት በውኃ ድነዋል። በተመሳሳይም ጥምቀት ያድናችኋል” (1ኛ ጴጥሮስ 3፡20-21)። በምን ያህል አጭር እና መንፈሳዊ ማጠቃለያ የአንድነት ቁርባንን አስቀምጧል! ጥንተ ክፋቱ በጠፋበት በዚያ የዓለም ጥምቀት፣ በኖኅ መርከብ ያልነበረው በውኃ ሊድን አልቻለም። እንደዚሁ በአንዲት ታቦት ሥርዓተ ምሥጢር መሠረት በጌታ አንድነት በተቋቋመችው ቤተ ክርስቲያን ያልተጠመቀ በጥምቀት ሊድን አይችልም” (ibid., 73[71]:11).
“[ኦ] ከቤተክርስቲያን ውጭ መንፈስ ቅዱስ የለም፣ ጤናማ እምነት ደግሞ ሊኖር አይችልም፣ በመናፍቃን መካከል ብቻ ሳይሆን፣ በጥላቻ በተመሰረቱት መካከልም ሊኖር አይችልም።(Treatise on Rebaptism 10 [A.D. 256]). @felgehaggnew
@felgehaggnew
595 viewsመሸ በከንቱ, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 21:36:20 ከዚህም በኋላ በሙሽራይቱ መጋረጃ ውስጥ ለምእመናን ምሳ ይሆን ዘንድ ሙሽራው ይሠዋባታል፤ መሥዋዕቱንም ከማየቷ የተነሣ ጉልበቶቿ ይብረከረካሉ፤ በደሙ ጽዋ ውስጥ ደሙ ሲንጠፈጠፍ ባየችም ጊዜ አንጀቷ ይላወሳል፤ ሥጋውን በፍርሃት፤ ትበላለች ደሙንም በመንቀጥቀጥ ትጠጣለች፤ ከዚህም በኋላ የሃይማኖት ነበልባል በልቡናዋ ውስጥ ይቀጣጠላል፤ ከሆዷም ውስጥ የፍቅር ሞገድ ይናወጣል፡፡

አሁንም በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ላይ የክህደትን ቃል የተናገረውን የአርጌንስን ነቀፋ እነሆ ፈጽመን ፍጥረቱን ሁሉ ፈጥሮ ለሚገዛ ለእግዚአብሔር አብ ምስጋና፣ የመንግሥትና የነገሥታት ጌታ ለሆነው ለወልድ ስግደት፣ ልቡና ያሰበውን ኩላሊት የመላለሰውን መርምሮ ለሚያውቅ ለመንፈስ ቅዱስ ጌትነት ይገባል እንላለን፡፡ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ልቡናው ስንኩል ዐሳቡ ብኩን የሆነ የአርጌንስ ነቀፋው ተፈጸመ የጽዮን ወገን የምሆን የቄስ ልጅ የምሆን እኔ ጊዮርጊስ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ መለኮት የአንዱ ከአንዱ በለጠ እንዳይባል ለሥላሴ አንድነት ሦስትነት ሃይማኖት ቀንቼ እየደረስኩ በቃሌ አጻፍኳት በባሕርና በየብስ በበረሃና በደሴት ለእርሱ ክብር ምስጋና የሚገባው ነው ሥጋዊ ደማዊ የሆነ ፍጥረት ለእርሱ ሊሰገድለት ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ @felgehaggnew
@felgehaggnew
550 viewsመሸ በከንቱ, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 21:36:20 መጽሐፈ ምሥጢር ከሚባለው ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ድርሰት የተወሰደ

“…እነሆ ቅዱስ ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስን “የክርስቶስ ሕይወት” በማለት ሰየመው መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስ ሕይወት ከሆነ እንዴት አያየውም? ከማየት ዐሳብ ይቀድማልና ከውጫዊ እይታ የአእምሮ እይታ ይበልጣልና ዳግመኛ ቅዱስ ጳውሎስ የሰውን ዐሳብ ከራሱ ከሰውየው በቀር የሚያውቅ የለም፡፡ እኛ ግን የተሰወረውን ገልጦ ጥልቁን መርምሮ የሚያውቅ የእግዚአብሔር መንፈስ አለን” 1ቆሮ.2፥11 አለ፡፡ አንተ ግብዝ ሆይ አብን እንደሚያውቀው ዕወቅ /አስተውል/፡፡ በወንጌል እንደተነገረው ወልድ ብቻውን ምንም ምን ሊያደርግ አይችልም ከአብ ያየውን ይሠራል እንጂ፡፡ አብ የሚሠራውን ወልድም ይህንኑ እንደእሱ ይሠራል፣ አብ ልጁን ይወዳልን የሚሠራውንም ሥራ ሁሉ ያሳየዋል፡፡ ከዚህም የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል፣ እናንተም ታውቁና ታደንቁ ዘንድ ስለ መንፈስ ቅድስም አስቀድመን ነገርናችሁ፡፡ በደለኞች ሆይ ከዛሬ ጀምሮ “ወልድ ከአብ ያንሳል አያህለውም” አትበሉ፡፡ “መንፈስ ቅዱስም ከወልድ ያንሳል አያህለውም ” አትበሉ፡፡

እኛ ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ባሕርይ፤ አንድ መንግሥት አንድ መገለጥ አንድ አኗኗር አንድ ሥልጣን አንድ አመለካከት አንድ መለኮት አንድ ዐሳብ አንድ ፈቃድና ሥርዐት አላቸው እንላለን፡፡ ፈቃዳቸው አንድ ነው ዐሳባቸው አንድ ነው፣ ሥርዐታቸውና ሕጋቸው አንድ ነው፣ ኀይላቸው አንድ ነው፣ እንደ አሕዛብ ልማድ ሦስት አማልክት አይባሉም፡፡ በሦስት አካል አንድ አምላክ ይባላሉ እንጂ፡፡ አንዱ አንዱን አይከተለውም ሁለተኛውም ሦስተኛውን አይከተለውም ከያዕቆብ አስቀድሞ ይስሐቅ ከይስሐቅ አስቀድሞ አብርሃም እንደነበረ ሁሉ ከአንዱ በፊት አንዱ አልነበረም፡፡

የአብ አኗኗር ከወልድ በፊት አልነበረም የመባርቅት ብልጭታ መታየት ታህል የዐይን ሽፋን እንቅስቃሴን የምታህል አይቀድመውም፡፡ እናት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ታመናለች እንዲህም ታሳምናለች፡፡

እናታችንም ቤተ ክርስቲያን በረድኤተ እግዚአብሔር ጥላ ሥር ጸንታ ትኖራለች፡፡ አቤቱ በረድኤት ጥላ ሥር ጸንቶ የሚኖር ማን ነው? መቅደስህም በተሠራበት ቦታ አድሮ የሚኖር ማነው? ተብሎ እንደተጻፈ በሙሽራዋ ክርስቶስ ደስ እያላት የወልድን ኀይል አምና በምእመናን ፀንታ ትኖራለች፡፡ ቀኝ ክንዱ ታቅፈዋለች ግራ ክንዱም ከራሴ በታች ናት ተብሎ እንደተጻፈ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃንነት ወደ ገነት ዓፀዶች ትመራለች፡፡ መንፈሰ ረድኤትህ መርቶ ወደ ምድረ ጽድቅ ያድርሰኝ ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ /መዝ.14፥1/

ከዚህም በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቅን ስትፈልግ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ትመለሳለች፤ በዮርዳኖስ ወንዝ ለልጁ በመሰከረ በእግዚአብሔር አብ ስም አንድ ጊዜ ትጠመቅ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ትወርዳለች፡፡ ዳግመኛም በዘካርያስ ልጅ በዮሐንስ እጅ በተጠመቀ በእግዚአብሔር ወልድ ስም ትጠመቅ ዘንድ ሁለተኛ ትወርዳለች፡፡ ዳግመኛም በዘካርያስ ልጅ በዮሐንስ እጅ በተጠመቀ በእግዚአብሔር ወልድ ስም ትጠመቅ ዘንድ ሁለተኛ ትወርዳለች የርግብ መልክ ባለው አካል አምሳል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በተቀመጠ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም ሦስተኛ ትጠመቃለች፡፡

ከዚህም በኋላ ከዮርዳኖስ ወንዝ ወጥታ አመተ ክርስቶስ ትባል ዘንድ ቅብዓ ሜሮንን ተቀብታ ማዕተበ ክርስትናን ገንዘብ ታደርጋለች፡፡ ቅብዓ ሜሮን የሃይማኖት ኀይል ነውና ሐዋርያት በዲዲስቅልያ መጽሐፋቸው እንደገለጹት በጥምቀት የተወለደ ሰው አምላክ ከድንግል የተወለደውን ልደት ይመስላል፤ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም እንደተወለደ ከርሷም ከተወለደ በኋላ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ተገኘ፡፡
በጥምቀት የተወለደ ሰውም እንደዚሁ ነው ከውኃውም ከወጣ በኋላ ወደ ጥምቀተ ባሕር የገባበትና የወጣበት ምልክቱ አይገኝም፤ መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው ተብሎ በመዝሙረ ዳዊት እንደተነገረ ዱካህም ከጥልቅ ውኃ ውስጥ ነው ፍለጋህም አይታወቅም፡፡

ወደ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አርእስተ ነገር እንመለስ፡፡ ከዚህም በኋላ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሰላም የተሰበከላችሁን የወንጌል ኀይል ተጫምታችሁ ያለውን ቃል ሰምታ የወንጌልን ቃል ጫማ በመጫማት አካሔዷን አሳምራ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትገባለች ኤፌ.6፥15 በራሷም ላይ የዕንቊን ዘውድ ትቀዳጃለች ይኸውም የሃይማኖት አክሊል ነው ዳግመኛም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በራሳችሁ ላይ የሚያድነውን የራኀስ ቊር ድፉ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ በእጃችሁ ያዙ ይሄውም የእግዚአብሔር ቃል ነው ብሎ እንደተናገረ፡፡ ኤፌ.6፥17 በጣቶቿ ላይም የክብር ቀለበትን ታደርጋለች ይሔውም የድኅነት ምልክት የሆነ የክብር ማዕተብ ነው፡፡

ከዚህም በኋላ አብርሃም ወዳለባት ይስሐቅም በበግ መሥዋዕትነት ወደ ዳነባት ከምድር እስከ ሰማይ ድረስ የእግዚአብሔር መላእክትም ሲወጡባትና ሲወርዱባት ያዕቆብ ባያት የወርቅ መሰላል ወደ ሙሸራው አዳራሽ ትገባለች፤ በእስራኤል ልጆች በደል ምክንያት ምስክር የሚሆኑ ሕግና ትእዛዝ የተጻፈባት ሙሴ የተሸከማት ጽላት ናት መልከጼዴቅም የቤተ ክርስቲያንን ምሥጢረ ቊርባን ሥርዐት የሚገልጽ የኅብስትና የወይን ግብር ያቀረበባት ናት ዘፍ.14፥18

ዳዊትም አቤቱ አንተ ታቦትህን ይዘህ ወደምታርፍባት ቦታ ተነሥ፡፡ እያለ የእግዚአብሔር ሕግ በተጻፈባት ታቦት ተነሥ፤ እያለ የእግዚአብሔር ሕግ በተጻፈባት ታቦት ፊት ምስጋና ያቀረበባት ናት አሳፍ የተቀኘላት፣ የቆሬ ልጆችም በምስጋና መሰንቆዎች የሚዘመሩላት የቆሬ ልጆችም በምስጋና መሰንቆዎች የሚዘምሩላት ናት፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ ዐለቱን ሰንጥቆ የደብተራ ኦሪቱን ንዋየ ቅድሳት ያስቀመጠባት፣ የተሠነጠቀችውን ዐለት መልሶ እንደነበረችው ያደረጋት፣ እንደ ብረት መዝጊያም የሆነችለት፣ ቁልፎቿንም ለፀሐይ አደራ የሰጠባት ናት፡፡ መዝ.131፥8፣ ተረፈ ኤር.83፥18

ኤልያስ መልአኩ ያቀረበለትን የተዘጋጀ ኅብስት የበላባት፣ በተመገበው ምግብ ኀይልም ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት የተጓዘባት ናት፡፡ ዕዝራ ሱቱኤል መጻሕፍተ ብሉያትን የምታሳውቀውን ከመልአኩ ዑራኤል እጅ ተቀብሎ የምስጋና ጽዋን የጠጣባት፣ አእምሮውም በዕውቀት ተሞልቶ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት ብሉያትን አፉ ከመናገር ሳያቋርጥ የቆየባት ናት፡፡ /1ነገ.19፥5-8 ዕ.ሱ.3 40/ ዘካርያስ ነጫጭና ጥርኝ ፈረሶችን ያየባት ናት፡፡ ዘካ.1፥8

ዳንኤልም የእሳት ሠረገላን ያየባት ናት፤ ዘመናት የማይወስኑት አምላክ ከሰው ልጅ ጋር ከበላያቸው ላይ የተቀመጠባቸውን ዙፋኖች ዳንኤል ያየባት ናት፤ ዕንባቆም በሁለቱ እንስሳት መካከል እግዚአብሔርን ያየባት ነቢያትም ሁሉ ደስ የሚያሰኝ ድምጽ የትንቢት ምስጋናን የሚያሰሙባት ናት፡፡ የገሊላ ሕፃናትም ኅሊናን የሚመስጥ፣ ልቡናን የሚማርክ፣ አጥንትን የሚያለመልመውን ማኅሌታዊ ምስጋናን የሚያመሰግኑባት ናት፡፡ ዳን.7፥9፣ ዕን.3፥2

ጴጥሮስ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ የተቀበለባት፤ ጳውሎስም የቤተ ክርስቲያን ብርሃን ይሆን ዘንድ የተጠራባት፤ ዮሐንስም እንደነጋሪት ድምጽ እያሰማ ምሥጢረ መለኮትን የሰበከላት፤ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን በአምሳለ እሳት የተቀበሉባት ናት፡፡ የእግዚአብሔርን መሥዋዕት የሚያቀርቡበትን መንበረ ታቦት ለመጐብኘት ማኅበረ መላእክት የሚፈሯት ማኅበረ ሰማዕታትም የመከራቸውን ዋጋ ተቀብለው የክብር አክሊልን የሚቀዳጁባት ናት፡፡
502 viewsመሸ በከንቱ, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 11:38:37 https://www.tiktok.com/@semagnderese/video/7122338710649146629?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7071239457273824773
https://www.tiktok.com/@semagnderese/video/7122338710649146629?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7071239457273824773
770 viewsመሸ በከንቱ, 08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 07:04:05 ወንድሞቹ እኅቶቹ የሚባሉት ደግሞ ፦ ከእናት አባት የተወለደ እኅት ወንድም እንደሚባል አባቱን አብን አባት እናቱን ወላዲተ አምላክን እናት በማድረግ የክርስቶስ ወንድሞች ይባላሉ ። እሱ ብቻም አይደለም ። ክርስቶስን በመከራና በኑሮ የሚመስሉ በሕግ በመከራ በኑሮ የሚመስሉት እንደ ክርስቶስ የሚኖሩ እንነዚህ ክርስቲያኖች ተብለው ይጠራሉ። ማቴዎስ ፲፩፥፳፭ ላይ ከእኔ ተማሩ እኔም የዋህ ቸር በልቤም ትሁት ነኝ ይላል ፦ ስለዚህ ክርስቶስን እያዩ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ይባላሉ ። አሁን ብዙ የእምነት ድርጅቶች አሉ ። በክርስትና ስም ብቻ ከ፴ ሺ በላይ የመጡ አሉ ። ግን እኛ ከእነሱ የምንለየው በምንድን ነው ሲባል ፦ ክርስቶስን እያየን እሱን መስለን በኑሮ እንኖራለን ነው ። ሌሎቹ በአፍ የክርስቶስ ነን ይላሉ ። እኛ ደግሞ በኑሮ እንመስለዋለን ። አባቱን አባት አድርገን በጥምቀት እንወለዳለን ። አባቱን እሱን መንፈስ ቅዱስን አባት አድርገን በጥምቀት እንወለዳለን ። እናቱን ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክን እናት አድርገን በምልጃ በጸጋ ከእርሷ እንወለዳለን ። እርሱ ከድንግል እንደ ተወለደ እኛም ከድንግል ጥምቀት እንወለዳለን ይላል አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ።
ለምን ?፦ እመቤታችን ጌታን ከወለደች በኋላ ማሕተመ ድንግልናዋ እንዳልተለወጠ ሁሉ ጥምቀትም ከባሕሩ ተጠምቀው ከወጡ በኋላ ሰውየው ገብቶ የወጣበት ባህር ጎድጉዶ አይገኝም ። ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወለደ እኛም ከድንግል ጥምቀት እንወለዳለን ።
እንደ ተጠመቀ እንጠመቃለን
እንደ ተሰደደ እንሰደዳለን
እንደ ፆመ እንፆማለን
እንደ ተራበ እንራባለን
እንደ ተገረፈ እንገረፋለን
እንደ ተቸገረ እንቸገራለን
እንደ ተሰቀለ እንሰቀላለን
እንደ ታመመ እንታመማለን
እንደ ሞተ እንሞታለን
እንደ ተራቆተ እንራቆታለን
እንደ ተነሳ አብረነው እንነሳለን
እንደ ዐረገ እናርጋለን ዘላለም አብረነው እንኖራለን ማለት ነው ።
እንዲህ የሚሆኑ ክርስቲያኖች ተብለው ይጠራሉ ማለት ነው ። ከክርስቶስ ጋር የታመመ ከክርስቶስ ጋር ይነሳል ። እርሱን መስለውት የሚኖሩ በሁለተናቸው በቃሉ የሚኖሩ በሃይማኖቱ በሕይወቱ ቃሉን የሚሰሙ ቃሉን ሰምተው የሚያደርጉ ። በመስማት አትጸድቁም ብሏል ቅዱስ ጳውሎስ ። ስለዚህ ቃሉን ሰምተው የሚያደርጉ ። ቃሌን እየሰማ በቃሉ ድኛለሁ የሚል ሳይሆን ቃሌን ሰምቶ በቃሌ የሚኖር ቃሉን ሰምቶ የሚያደርግ ሃይማኖቱን የሚያምን የባህርይ አምላክ ነው ብሎ የሚያምን ኹሉም እናምነዋለን ይላሉ የባህርይ አምላክ ነው ትንሳኤ ሕይወት መድኃኒት ሥግው ቃል በተዋሕዶ ብለው የሚያምኑ ። ስለዚህ ሃይማኖቱን የሚያምኑ ቃሉን የሚያደርጉ መንገዱን የሚከተሉ እነዚህ ክርስቲያኖች ይባላሉ ።
ክርስቶስ የተሰቀለው መቼ ነው ?፦ በዕለተ አርብ ። የተነሳውስ ?፦ ዕለተ እሁድ።
ከዕለተ አርብ እና ከዕለተ እሁድ ማንን ትወዳላችሁ !?
አርብ ብትሉ ክርስቲያን አይደላችሁም ። እንዴት ብትሉ ፦ ክርስቲያን የሚባለው ከክርስቶስ ጋር ታሞ ከክርስቶስ ጋር አብሮ የሚነሳ ነው ። አርብን የማትወዷት ከሆነ አብራችሁ መታመም አልፈለጋችሁም ማለት ነው ። ብዙዎቹ በክርስቶስ ስም የተመሰረቱ ድርጅቶች ኹሉ የክርስቶስ የመስቀሉ ጠላቶች ናቸው ። ዕለተ አርብን አይወዱትም ። ክርስቶስ ተነስቷል አድኖኛል እዳ ከፍሎልኛል እንጂ አብረውት ሕማሙን መሳተፍ አይችሉም ። መስቀሉን መሸከም አይወስዱም ። መፆም መጸለይ መስገዱን አይወስዱም ። ለፈቃዳቸው እንጂ ለፈቃዱ መኖር አይወዱም አይፈልጉም ። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ፊልጲስዮስ ፫ ላይ ሲናገር ብዙዎች የክርስቶስ መስቀል እንቅፋት ሆነው ይመላለሳሉ እያለቀስኩ እላለሁ መጨረሻቸው ጥፋት ነው ብሎ ይናገራል ። ስለዚህ አብረውት የታመሙ አብረው ይነሳሉ ።
ሥጋወደሙ በመስቀል ላይ የተፈተተልን መቼ ነው?
ዕለተ አርብ
ዲያቢሎስ በመስቀል የተቀጠቀጠው መቼ ነው?
ዕለተ አርብ
ሲዖል የተበረበረችው መቼ ነው?
ዕለተ አርብ
ገነት የተከፈተው መቼ ነው?
ዕለተ አርብ
የንስሃ በር የተከፈተው መቼ ነው?
ዕለተ አርብ
ነፍሳት ከሲዖል የወጡት መቼ ነው?
ዕለተ አርብ
እና አርብን ምን አድርጋችሁ ነው ምትጠሏት ?፦ አርብን የሚወድ እሁድን ያገኛል ። አብረውት መከራ የሚቀበሉ ክርስቲያኖች ይባላሉ ። አብረው የታመው አብረውት ይነሳሉ ። አብረውት ዝቅ ያሉ ልዑል አምላክ ሲሆን እርሱ ዝቅ እንዳለ መሸሽ እየቻሉ መካድ እየቻሉ ማጭበርበር እየቻሉ በክርስቶስ ስም ዝቅ ያሉት አብረውት ያርጋሉ ። እንግዲህ እኛ ወደ ታች አንወርድም የፈጠረንን ተከትለን እናርጋለን እንጂ !!!
እንግዲህ ወደታች አንወርድም የፈጠረንን ተከትለን ወደ ሰማይ እናርጋለን እንጂ!!!
ከማኅሌት ወደ ዘፋኝነት አትውረዱ!
ከአንድነት ወደ ዘረኝነት አትውረዱ!
ከፆም ወደ ሆዳምነት አትውረዱ!
ስለዚህ በምግባር ወደ ታች ያልወረደ በሰማይ ከክርስቶስ ጋር አብሮት ያደርጋል ። በዚህ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ተብለው ይጠራሉ ማለት ነው ።
ከአህዛብ የምንለየው የተገለጠው እግዚአብሔር ነው ብለን ስለምናምን ከሎሎቹ
በክርስቶስ ስም ከሚጠሩት ከሌሎቹ ደግሞ የምንለየው በክርስቶስ ፈቃድ ለእራሳችን ሳይሆን ለክርስቶስ ስለምንኖር ነው።
መጨረሻ ላይ በክርስቶስ ስም ስለምንሞት ነው ።
ሮሜ ፲፬፥፰ ላይ ብንሞትም ለክርስቶስ እንሞታለን ብንኖርም ለክርስቶስ እንኖራለን ። በክርስቶስ ስም ተጠምቀው በክርስቶስ ስም ኑረው በክርስቶስ ስም የሚሞቱ #ክርስቲያኖች ተብለው ይጠራሉ።
ለአባታችን ቃለ ሕይወት ቃለ በረከት ያሰማልን በእድሜ በጸጋ ያቆይልን።
የተማርነውን በልቡናችን ያሳድርልን።
ጸሐፊ ራሔል የተዋሕዶ ተማሪ @felgehaggnew @felgehaggnew
657 viewsመሸ በከንቱ, 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 07:04:04 ለዚህ ነው ክርስቲያን #ታንቆ_መሞት አይችልም እሚባለው ለምንድን ነው ፦ እራሱን መግደል የማይችለው ታንቆም ሆነ መርዝ ጠጥቶ ኤሌትሪክ ጨብጦ ወይም ገደል ተንከባሎ ክርስቲያን እራሱን መግደል የማይችለው የራሱ ስላልሆነ ነው ። እንግዲያውስ የማን ነው ? የእግዚአብሔር ደም የተዋጀ የክርስቶስ በግ ነው ። እንደዚህ ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ ? እኔ የራሴ አይደለሁም ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ !? የራሴ አይደለሁም ያለ ሰው እኔ አሁን የክርስቶስ እቃ ነኝ ብዬ ካሰብኩ ፦ በዚያውም አንድ ክርስቲያን ክርስቲያን የሚባለው ምን ሲያሟላ ነው የሚለውን እያየን እንሔዳለን ። አሁን ይኸ መጽሐፍ የኔ ከሆነ የኔ መጽሐፍ ነው እኔ አስቀምጨዋለሁ እኔ እስከማነሳው እዚሁ ይጠብቃል ማለት ነው ። ክርስቲያን የእግዚአብሔር ዕቃ ከሆነ እግዚአብሔር ወደ ፈለገው እስኪያነሳው ድረስ እግዚአብሔር አስቀመጠው ቦታ የሚኖር ነው ። የክርስቶስ ሕዋስም ከሆነ በክርስቶስ ይኖራል ። አንድ ሃሳብ ልንገራችሁ ፦ እራስ እና አካል አለ ብያችኃለሁ ። እራስ እና አካል በአንድ ላይ እንዲኖሩ የሚያደርጉ ኹለት መሠረታዊ ነገሮች አሉ ።
ሰው ያለ አፍንጫ መኖር ይችላል።
ያለ ጆሮ መኖር ይችላል።
ያለ እጅም መኖር ይችላል።
ያለ እግርም መኖር ይችላል።
መኖር የማይችላቸው ኹለት መሠረታዊ ነገሮች አሉ ።
ያለ ደም እና ያለ እስትንፋስ መኖር አይችልም ። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ከሆነች ክርስቲያንም የክርስቶስ ሕዋስ ከሆን እነዚህ ሕዋሳት እንዲንቀሳቀሱ ኹለት ነገሮች ያስፈልጓቸዋል ።
#እስትንፋስ እና #ደም
እንደ እስትንፋስ #ስርዓተ_ቤተ_ክርስቲያንና_ጸሎት ።
እንደ ደም ደግሞ #ቅዱስ_ቁርባን ያስፈልገዋል።
አንድ ክርስቲያን ክርስቲያን ተብሎ የሚጠራው በሥርዓት እና በጸሎት ሲኖር እንደገና ደግሞ በቅዱስ ቁርባን ሲኖር ነው ። ለምን አንድ ሕዋስ ደም መውሰድ ካቆመ ይደርቃል ተቆርጦ ይጣላል ። ክርስቲያን መቁረብ ያቆመ ዕለት ሥጋው እና ደሙን አልቀበልም ያለ ዕለት ከክርስቶስ ተቆርጦ የወጣ ነው:። ከኅብረቱ ይጠፋል ማለት ነው ። እስትንፋሱ ሲቋረጥ ሳንባው መተንፈስ ሲያቆም ሰውዬው ሞተ እንደምንለው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ጸሎት እስትንፋስ ነው ።
የተክሊል ስርዓት
የጦም ስርዓት
የስግደት ስርዓት
የጋብቻ ስርዓት
የምንኩስና ስርዓት
የክህነት ስርዓት
የጵጵስና ስርዓት
ማንኛውም ስርዓት አለው ። ስርዓት በእስትንፋስ የተመሰለበት ምክንያት ፦ በመንፈስ ቅዱስ ስለሚመሰል ነው ። ስርዓት የሌላት ቤተክርስቲያን ይላል ቅዱስ አትናቴዎስ ዘአንጾኪያ ስርዓት የሌላት ቤተክርስቲያን እርሷ የክርስቶስ አካል አይደለችም ። ስርዓት የሌለው ክርስቲያን እርሱ ከክርስቶስ ተቆርጦ የወጣ ሕዋስ ነው ። ተቆርጦ የተጣለ ሰንረለት ነው ። በእስትንፋስ የተመሰለው በመንፈስ ቅዱስ ስለሚፈጸም ነው ማለት ነው ። ስለዚህ የክርስቶስ አካላት በክርስቶስ የምንኖር ነን ። ቅዱስ ጳውሎስ ፩ይ ተሰሎንቄ ፩፥፩ ላይ ሲናገር በእግዚአብሔር አባታችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለሆነችው ለተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን ይላል ። እና ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ይኸን ሲተረጉም ምን ይላል ፦ ወዮ በሰይጣን ፈቃድ እየኖሩ በእግዚአብሔር አባታችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተብለው ለሚጠሩ ክርስቲያን ሐፍረትን አፍርላቸዋለሁ ይላል ።
በሰይጣን ፈቃድ እየኖሩ #እየዘፈኑ በክርስቶስ ነን ማለት አይችሉም ።
እየገደሉ በክርስቶስ አምነናል ማለት አይችሉም ። እየጠነቆሉ እየጨፈሩ እየቀሙ በክርስቶስ ነን ማለት አይችሉም ። በእግዚአብሔር አባታችን ማለት ምንኛ ኩራት ነው ።በሚጠፋ በሚሞት በሚያልፍ ንጉሥ ሳይሆን በሕያው እግዚአብሔር ስም የሚጠሩ ክርስቲያኖች ተብለው ይጠራሉ ። መመከቻቸውም ክርስቶስ የሆነ።
በመጨረሻ ክርስቲያኖች ማለት እንደ ክርስቶስ ስለዚህ እዚህ ላይ ክርስቲያን ክርስቲያን ተብሎ የሚጠራው እንደ ክርስቶስ ሲኖር ነው በሚለው እናጠቃልለዋለን ማለት ነው ። ክርስቶስ በሰማይ አባቱ አብ የባህርይ አባቱ ነው እኛም የክርስቶስ የባህርይ አባቱ ለእኛ የጸጋ አባታችን ነው ። የክርስቶስ አባት የባህሪይ አባታችን ከሆነ የክርስቶስ እናት እናታችን ነች ። ማቴዎስ ፲፪፥፵፫ ጀምሮ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምር አንድ ሰው መጣና እናትህ እና ወንድሞችህ ይፈልጉሃል አለው ። አይ እናቴስ ማናት ወንድሞቼስ እነማን ናቸው እናቴና ወንድሞቼ የኔን ቃል የሚሰሙ ናቸው ብሎ መለሰ ይለናል ።
እና ሊቃውንቱ ሲተረጉሙት ፦ እናትህና ወንድሞችህ ይጠሩሃል ያለ ሰው ማነው ይሉና ጉባዔ መፍታት የሚፈልግ #ይሁዳ ነው እንጂ ሌላ ማን ይሆናል ይላሉ ። ጉባዔ የሚፈታ ይሁዳ ነው ። ታዲያ እናትና ወንድሞችህ ይፈልጉሃል ሲባል ክርስቶስ እናቱን ነቅፎ ነው እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው ያለ ሲባል ከእናታችሁ ከአባታችሁ ይልቅ ለሰማይ አባት ለሰማይ እናት መንናችሁ ኑሩ አባቴ ሰማያዊ እናቴም ሰማያዊት እርስቴም ሰማያዊ ዘመዶቼም ሰማያውያን ልብሴም ሰማያዊ ምግቤም ሰማያዊ ጫማዬም ሰማያዊ ጋሻዬም ሰማያዊ ሕሊናዬም ሰማያዊ ሕጉም ሰማያዊ ሃይማኖቴም ሰማያዊ ነው በሉ ለማለት ነው እንጂ እናትን ነቅፎስ አይደለም ብሎ ይናገራል ። እናቴና ሞንድሞቼ ለዚህ ነው ተመልከቱ የሰማይ አባት አብጁ ለማለት ነው ።
አንድ መነኩሴ በገዳም ሲኖር ባህታዊ ነው። ሄዱና አባትህኮ ሞተ አሉት ፦ እርሱም አንተ ለምን ትሰድበኛለህ አባቴ የማይሞት የዘላለም ሕያው ነው ብሎ መለሰ። አባትህ ጎንደሬ ነው ጎጃሜ ነው ትግራይ ነው አማራ ኦሮሞ ቤንሻንጉል ጉምዝ ጉራጌ ነው ስትባሉ #ለምን_ትሰድበኛለህ የኔ አባት የዘላለም አባት ነው በሉ እርሱም ሕያው እግዚአብሔር ነው ። የሰማይ አባት ይኑራችሁ ።
ሊቃውንት ሲተረጉሙት ፦ እናቴና ወንድሞቼ ይኸንን ቃሌን የሚሰሙት ናቸው ። ክርስቲያኖች ማለት የክርስቶስ እናቶች የክርስቶስ ወንድሞች የክርስቶስ እኅቶች ማለት ናቸው ። ሰው የክርስቶስ እናት እንዴት ይሆናል ነው እሺ ወንድሞቹስ ይሁኑ እናቱ እንዴት ነው የምንሆነው ነው ስለዚህ ክርስቲያን ማለት የክርስቶስ እናት ነው ማለት ነው እንዴት? እናቱ ድንግል ማርያም በድንግልና እንደ ጸነሰችው አረጋዊ መንፈሳዊ ከመ ወላዲተ አምላክ ይላል ። እሷ በድንግልና ቅዱስ ገብርኤልን ሰምታ እንደ ጸነሰች ክርስቲያኖች የሕሊናና የእዝነ ነፍስ የእዝነ ሥጋ ድንግልናቸውን ጠብቀው የጆሮአቸውን ድንግልና ጠብቀው ለመናፍቅ ለፍልስፍና ለረከሰ ትምህርት ሳያስደፍሩ ድንግልናቸውን ጠብቀው ለክርስቶስ ሕያው ቃል ብቻ ጆሮአቸውን ከፍተው ቃሉን ሰምተው ከመምህራን ጸንሰው ምግባርን የሚወልዱ ክርስቲያኖች እንደ እናቱ እንደ ድንግል ማርያም የክርስቶስ እናቶቹ ይባላሉ ።
475 viewsመሸ በከንቱ, 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 07:04:04 ስለዚህ ተመልከቱ የማይታየው እግዚአብሔር የማይታወቀው እግዚአብሔር በአቅማችን እናውቀው ዘንድ ፀሐይን ሙቀን ባንጨርስ ለብርድ ያህል ጥቂት እንደምንሞቀው ውቅያኖስን ጠጥተን እንደማንጨርሰው እንኳን ለጥም ያህል ጥቂት እንደምንጠጣው ሁሉ እግዚአብሔርን ጨርሰን ባናውቀውም በፈቀደው መጠን ለልጅነት የሚረባንን እውቀት ስለእርሱ እንድናውቅ ፈቅዶልናል ። ያንን ደግሞ እራሱ ካልተናገረ እራሱ ካልተገለጠ ፍጥረት ስለ እርሱ በመናገር የፈጣሪን ነገር ማወቅ አይቻልም ። ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕያው ሥግው ቃል እራሱ እግዚአብሔር የሆነው ቃል እግዚአብሔር ቃል ተገልጦ ስለእራሱ ነገረን ።
ለእግዚአብሔርሰ አልቦ ዘርእዮ ግሙራ አላ ወልድ ዋሕድ ዘሀሎ ውስተ ሕፅነ አቡሁ ውእቱ ነገረነ ።
" እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ ነገረን እንጂ።"
(የዮሐንስ ወንጌል ፩፥፲፰ )
ስለ እግዚአብሔር የሚነግረን ማነው ከተባለ ስለ እግዚአብሔር የሚነገረን እውቀት ትክክል የሚሆነው እግዚአብሔር እራሱ ከነገረን ብቻ ነው ። ስለዚህ ሌሎቹ ሃይማኖቶች ወይም ሌሎቹ የእምነት ድርጅቶች የሚሉት ስለምናመልከው አምላክ በትንቢት ተነግሮናል በራዕይ ተገልጦልናል ነው ። እኛ ግን የምንለው ስለምናመልከው ሕያው አምላክ ስለ ቅዱስ እግዚአብሔር እግዚአብሔር በሥጋ ተገልጦ ነግሮናል ነው ። ለምን ሲባል ፦ እግዚአብሔር ካልተናገረ በቀር ስለ እግዚአብሔር ማወቅ የሚችል ስለሌለ ። እግዚአብሔር እንዲገለጥ ያደረገውም ስለዚህ ነው ። ስለዚህ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ትክክል ናት የምንለው እራሱ እግዚአብሔር ስለ እራሱ ካልተናገረ በቀር እግዚአብሔርን የሚያውቅ ስለሌለ እግዚአብሔር እራሱ ተገልጧል ብላ የምታምን ይህቺ ቤተክርስቲያን ስለሆነች እግዚአብሔር በልብነቱ በአብ ልብነት ተመክሮ በወልድ ቃልነት ተነግሮ በመንፈስ ቅዱስ ሕያውነት ጸንቶ የተመሰረተ እግዚአብሔር ስሩ የሆነለት ዛፍ ምን ይባላል ክርስትና ተብሎ ይጠራል ። ከክርስቶስ የሚለው ። ይህ ማለት ምን ማለት ነው ክርስቶስ እራስ የሆነላት ክርስቶስ እራስ የሆነለት ቤተክርስቲያን አካል የሆነችለት እሱ ሕዋስ የሆነ ክርስቲያን ተብሎ ይጠራል ። ክርስቶስ እራስ ቤተ ክርስቲያን አካል ምእመናን ሕዋሳት የሆኑላት ይቺ ምን ትባላለች ክርስትና የክርስትና ሃይማኖት የሚባለው እርሱ ነው ። ክርስቲያኖች የሚባሉት ክርስቶስ እራሳቸው ቤተ ክርስቲያን አካላቸው እነሱ ሕዋሳት የሆኑ አንድ ማኅበር ማለት ነው ። ኤፌሶን ፩፥፳፫ ላይ ከክርስቶስ በላይ ሌላ አምላክ የለም አብም አንድ ናቸው በሥልጣን ፤ መንፈስ ቅዱስም አንድ ነው ። ስለዚህ ከክርስቶስ ክርስቶስን እራስ አድርጎ ቤተክርስቲያንን አካል አድርጎ የበቀለ ሕዋስ ማለት ነው ። የክርስቶስ ሕዋስ ማለት ነው ክርስቲያን ። እንደ ጣት እንደ ጥፍር እንደ ዐይን እንደ ጆሮ አንድ እራስ አለ አንድ አንገት አለ አንድ አካል አለ ብዙ ሕዋሳት አሉ ። አንድ እራስ እንዳለ አንድ እግዚአብሔር አለ ። አንድ አንገት እንዳለ አንድ ሃይማኖት አለ ። አንድ አካል እንዳለ አንዲት ቤተ ክርስቲያን አለች ። ብዙ ሕዋሳት እንዳሉ ብዙ ክርስቲያኖች ይኖራሉ ማለት ነው ። ብዙ ክርስቲያኖች መሆናችን ብዙ ሕንጻ አሁን እዚህ የልደታ እዚያ የጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲን ቢኖር እንዚህ ሁሉ አንዲት ቤተክርስቲያን ናቸው ። ለምን ፦ ሰው ብዙ ጣት ብዙ ጥፍር ብዙ ጠጉር እያለው ነገር ግን አንድ ሰው ይባላል ። ከክርስቶስ አንድነት የቤተክርስቲያን አንድነት የተመሰረተ ስለሆነ ስለዚህ ክርስቲያን ማለት የክርስቶስ ሕዋስ ማለት ነው።
ሦስተኛ ክርስቲያን ማለት በክርስቶስ ማለት ነው ። በክርስቶስ ማለት በክርስቶስ ስም የተጠራ ማለት ነው ። በክርስቶስ ስም የሚመካ በክርስቶስ ስም የሚመክት ለክርስቶስ ስም የታመነ በክርስቶስ ስም የሚሞት ማለት ነው ። መኃልይ ዘሰሎሞን ፩፥፩ ጀምሮ ስታነቡ ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው ይላል ። ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው ማለት ፦ ክርስቶስ የሚለው ስም ክርስቲያን በሚባሉት ላይ እንደ ዘይት ፈሶባቸው ይኖራል ነው ። ስለዚህ ተመልከቱ ክርስቲያን ማለት የክርስቶስ የስሙ ዙፋን የስሙ ማደሪያዎች የስሙ መጠሪያዎች የስሙ መገለጫዎች ማለት ናቸው ። ስምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው እርሱ ክርስቶስ ነው ክርስቶስ የሚለው ስም በውስጣችን በልባችን በራሳችን በመላ ሕይወታችን ላይ ከመኖሩ የተነሳ ክርስቲያኖች ተብለን እንጠራለን ነው ። ስለዚህ ክርስቲያንን ማንሳት ክርስቶንስን ማንሳት ነው ክርስቲያንን መንቀፍ ክርስቶስን መንቀፍ ነው ። በክርስቶስ ስም የከበሩ ማለት ነው ። ዘይት ያረፈበት ሁሉ ያበራል ። በዘይት የተጠረገ ብረት ዝገቱ ይለቅለታል ይጠራል ያበራል ያጥበረብራል ። የክርስቶስ ስም በላያችን ላይ ከማደሩ የተነሳ ለስሙ ታምነን ከመኖራችን የተነሳ በዚህ ምክንያት የጠራን እንሆናለን ማለት ነው ። ስለዚህ በክርስቶስ ስም የተጠራን ማለት ነው ። በስሜ ስለተጠራችሁ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ በክርስቶስ ስም የሚኖሩ ክርስቲያኖች ይባላሉ ማለት ምን ማለት ነው ብዙ ሰዎች በክርስቶስ ስም እንኖራለን ይላሉ ። ስሙን ሕይወት መድኃኒት እንደሆነ የሚያምኑ ስሙን እንደ ነቢይ እንደ አማላጅ እንደ ሐዋርያ እንደ መልአክ የሚቆጥሩ ሳይሆኑ ስሙ ሕይወት ነው መድኃኒት ነው ብለው የሚያምኑ ለዚያ ስም የሚሞቱ ትሞታላችሁ ሲባሉ ክርስቶስ ትንሳኤ ነው የሚሉ ትጠፋላችሁ ሲባሉ ክርስቶስ ሕይወቴ ነው የሚሉ ለዚህ ስም ኑረው በዚህ ስም ተጠምቀው በዚህ ስም ከብረው በዚህ ስም መክተው ለዚህ ስም የሚሞቱ እነዚህ ክርስቲያኖች ይባላሉ ። እንደ ክርስቶስ ማለት ነው ። ወይም የክርስቶስ ማለት ነው ። እስኪ የክርስቶስ ከሚለው እንጀምር የክርስቶስ ሕዋስ ነን ብለናል ። የክርስቶስ ከሆን ሰው የራሱ አይደለም ማለት ነው ። ክርስቲያን የራሱ ሁኖ አያውቅም ። እንግዲያ የማነው የክርቶስ ነን ። እምንሞተው ለምንድነው ታዲያ
እምንሞተው
እምንታረደው
እምንቃጠለው
እምንገደለው
እምንሰደደው
ሐብት የምንዘረፈው
ከሀገር የምንሰደደው ለምንድነው የእኛ ስላልሆንን ነው ። የክርስቶስ ስለሆን ለክርስቶስ ሙተን በክርስቶስ ተነስተን ለመኖር ነው ። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በዋጋ ተገዝታችኃልና የራሳችሁ አይደላችሁም ያለው ። የክርስቲያን አንዱ የጠጉር ዘለላው እንኳን ቢሆን የእግዚአብሔር ደም ተከፍሎበታል ። ይኸን ታውቃላችሁ ?
370 viewsመሸ በከንቱ, 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ