Get Mystery Box with random crypto!

ከዚህም በኋላ በሙሽራይቱ መጋረጃ ውስጥ ለምእመናን ምሳ ይሆን ዘንድ ሙሽራው ይሠዋባታል፤ መሥዋዕቱን | የእውነት ሚዛን(ቴቄል)

ከዚህም በኋላ በሙሽራይቱ መጋረጃ ውስጥ ለምእመናን ምሳ ይሆን ዘንድ ሙሽራው ይሠዋባታል፤ መሥዋዕቱንም ከማየቷ የተነሣ ጉልበቶቿ ይብረከረካሉ፤ በደሙ ጽዋ ውስጥ ደሙ ሲንጠፈጠፍ ባየችም ጊዜ አንጀቷ ይላወሳል፤ ሥጋውን በፍርሃት፤ ትበላለች ደሙንም በመንቀጥቀጥ ትጠጣለች፤ ከዚህም በኋላ የሃይማኖት ነበልባል በልቡናዋ ውስጥ ይቀጣጠላል፤ ከሆዷም ውስጥ የፍቅር ሞገድ ይናወጣል፡፡

አሁንም በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ላይ የክህደትን ቃል የተናገረውን የአርጌንስን ነቀፋ እነሆ ፈጽመን ፍጥረቱን ሁሉ ፈጥሮ ለሚገዛ ለእግዚአብሔር አብ ምስጋና፣ የመንግሥትና የነገሥታት ጌታ ለሆነው ለወልድ ስግደት፣ ልቡና ያሰበውን ኩላሊት የመላለሰውን መርምሮ ለሚያውቅ ለመንፈስ ቅዱስ ጌትነት ይገባል እንላለን፡፡ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ልቡናው ስንኩል ዐሳቡ ብኩን የሆነ የአርጌንስ ነቀፋው ተፈጸመ የጽዮን ወገን የምሆን የቄስ ልጅ የምሆን እኔ ጊዮርጊስ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ መለኮት የአንዱ ከአንዱ በለጠ እንዳይባል ለሥላሴ አንድነት ሦስትነት ሃይማኖት ቀንቼ እየደረስኩ በቃሌ አጻፍኳት በባሕርና በየብስ በበረሃና በደሴት ለእርሱ ክብር ምስጋና የሚገባው ነው ሥጋዊ ደማዊ የሆነ ፍጥረት ለእርሱ ሊሰገድለት ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ @felgehaggnew
@felgehaggnew