Get Mystery Box with random crypto!

የእውነት ሚዛን(ቴቄል)

የቴሌግራም ቻናል አርማ apostolicanswers — የእውነት ሚዛን(ቴቄል)
የቴሌግራም ቻናል አርማ apostolicanswers — የእውነት ሚዛን(ቴቄል)
የሰርጥ አድራሻ: @apostolicanswers
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.77K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ገጽ የተሃድሶን ምንፍቅና በእውነት ሚዛን እየመዘንን ቴቄል እንላለን።
"ቴቄል ማለት፥ በሚዛን ተመዘንህ፥ ቀለህም ተገኘህ ማለት ነው" (ት. ዳን 5፡27)
YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCPLJimNlqTFBnlbsh_vccgg
ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት
@AbuNak
@beorthodox

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-20 07:04:04 #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን ።
#ክርስቲያን_ማለት_ምን_ማለት_ነው !?
#በመጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ_ገብረ_ኪዳን_ግርማ
ክርስቲያን ወይም ክርስትና ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ቃል ከማየታችን በፊት አንዳንድ ሰዎች ስለ ክርስትና ለምሳሌ ፦ የሌላ እምነት ተቋም ተከታይ የሆኑ ሰዎች እኔ ክርስቲያን ያልሆንኩት #ክርስቲያን የሚለው ቃል ሰዎች ያወጡት ስም ስለሆነ ነው ብለው ማብራሪያ የሚሰጡ ሰዎችም አሉ ። ክርስቲያን የሚለው ስም #በአንጾኪያ የወጣ ስም ስለሆነ ሰዎች ባወጡት ሃይማኖት ስለማልመራ በዚህ ምክንያት ወደ ሌላ እምነት ተቀይሪያለሁ ብለው በሌላ ቦታ የተናገሩ ሰዎችም አሉ ። እና ስማቸውን የእግዚአብሔር መንግስት በሚጠራበት ቦታ የመናፍቅ ስም እየጠራን ጊዜ ስለምናባክን ለትምህርታቸው ሃሳቡ ይደርሳቸዋል እነሱም ይሰሙታል ማለት ነው ።
እና ክርስቲያን የሚለው ስም በአንጽኪያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተብለው ተጠሩ ይላል ። ያንን ቀድሞ የነበረው ስም በአንጾኪያ የተገለጠበት ነው እንጂ ክርስቲያን የሚለው ስም በአንጾኪያ የወጣ ስም አይደለም ።
ክርስቲያን ማለት፦
#ከ_ክርስቶስ
#በ_ክርስቶስ
#ለ_ክርስቶስ
#የ_ክርስቶስ እና
#እንደ_ክርስቶስ ማለት ነው ። አምስት ሃሳቦችን ያዝን ማለት ነው ።
#ከ_ክርስቶስ ማለት ፦ ክርስቶሳዊ ማለት ነው ።
ከክርስቶስ ማለት ፦ ክርስቶስ ሥር ሁኖት እሱ ቅርንጫፍ የሆነ ማለት ነው ። ክርስቶስ ግንድ ሁኖት እሱ ቅርንጫፍ የሆነ ነው።ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐንስ ፲፭፥፩ ላይ እኔ እውነተኛ የወይን ግንድ ነኝ ተካዩም አባቴ ነው እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ ብሎ ይናገራል ። ስለዚህ ክርስቶስ ጉንድ ሁኖ ከክርስቶስ የበቀሉ ከክርስቶስ ስርነት የበቀሉ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ወይም የክርስትና ሃይማኖትን ሰው ሊያጠፋው አይችልም የሚባለው ምክንያት ዛፍ ሆኖ ስሩ በመጥረቢያ ሊቆረጥ አይቻልም ። በመቆፈሪያ ቆፍሮ ሊደረስበትም አይቻልም ። በምንም ነገር ተቆፍሮ አይገኝም ። ምክንያቱም ስራችን ሕያው ስር እግዚአብሔር ስለሆነ ። ቅዱስ ቄርሎስም ይናገራል ፦ ሃይማኖት ስሩ እንተ ይትመውት ሃይማኖት ማለት የማትነቀል የማትደርቅ የማትፈርስ የማትበሰብስ ሕያው ሥር ማለት ናት ይላል ። የሚደርቅ ሥር ያለው ዛፍ ስሩን ብንቆርጥበት ዛፉ ይነቀላል ቅርንጫፉም ይደርቃል ። የእኛ ግን ፦ ዛፉም እራሱ ክርስቶስ ነው ። ስሩም እራሱ ክርስቶስ ነው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው ። ቅርንጫፎቹም እኛ ነን ማለት ነው ።
ከክርስቶስ የበቀልነ ሕያው ሥር ያለን ሥጋዊ ደማዊ ያልመሰረተን ታይቶ የሚጠፋ ማለዳ የተናገረውን ማታ የሚለውጥ ሥጋዊ ደማዊ ሰው ያልመሰረተው ሰማያዊ ቅርንጫፍ ምድራዊ ሥር ያለው ሃይማኖት ይሄ ምን ይባላል ክርስትና ወይም ክርስቲያን ይባላል ። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ #ቀዳማዊ ልደት አለው ። በምድር #ዳህራዊ ልደት አለው ። ስለዚህ በአባቱ ልብነት በእሱ ቃልነት በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት ጸንተው የሚኖሩ ክርስቲያኖች ተብለው ይጠራሉ ። ስለዚህ ከክርስቶስ የተገኘ ነው ። ክርስትና አንጾኪያ ላይም የተመሰረተ አይደለም ኢየሩሳሌም ላይም የተመሰረተ አይደለም ። ክርስትና መቼ የነበረ ነው ከተባለ ክርስትና ቅድመ ዓለም የነበረ ነው።
ማለት ምን ማለት ነው ፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር ፪ይ ጤሞቴዎስ ፩ ላይ ሲናገር እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ የወሰነውን በልጁ ገለጠው ይላል ። ስለዚህ ክርስትና በሕሊና አምላክ የነበረ በሗላ በነቢያት የተገለጠ ለመላእክት የታየ በሐዋርያት የተሰበከ ነው ማለት ነው ። ሃይማኖት እግዚአብሔር ነው ። ሃይማኖት እግዚአብሔር ከሆነ ለእግዚአብሔር መጀመሪያ የለውምና ሃይማኖት መቼ ተጀመረ ማለት ጥያቄው እራሱ ስህተት ነው ማለት ነው ። ምክንያቱም ሃይማኖት እግዚአብሔር ነው ። ሃይማኖት አይሻሻልም አይታደስም አይቃለልም የሚባለው ሃይማኖት እግዚአብሔር ነው ። እግዚአብሔር ከሆነ ለእግዚአብሔር መነሻ የለውም ለእግዚአብሔር መድረሻ የለውም ። ሃይማኖት አማኝ ሳይኖር ሃይማኖት ነበረ ። አማኝ ሊሞት ይችላል ሊጠፋ ይችላል ሊክድ ይችላል ሃይማኖት ግን ዘለዓለም ነበረ አለ ይኖራልም ። ስለዚህ ከክርስቶስ የተነሱ ክርስቶስ የመሰረተው ማለት ነው ። ለዚህ ነው እውነተኛ ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብቻ ነው የምንለው እኛ ስለምንከተለው የእኛ ሃይማኖት ስለሆነ አይደለም ። እንግዲያው ለምንድንነው ነው ሲባል ፦ እግዚአብሔር ስውር ነው ። እግዚአብሔርን ፍጥረት መርምሮ የሚደርስበት ከሆነ እግዚአብሔር አይደለም ማለት ነው ። እነ ቅዱስ አትናቴዎስም ተናግረዋል ። እግዚአብሔርን አንተ መርምረህ የምትደርስበት ከሆነ እግዚአብሔርን ትቼ አንተን አመልክሃለሁ ብለው ይናገራሉ ። እግዚአብሔር ከሕሊና በላይ ከመመርመር ውጭ ነው ። ታዲያ ከሕሊና በላይ የሆነውን እግዚአብሔር የሚመረምር ልብን ሁሉ ጸጥ ረጭ አድርጎ የሚያሳርፍ እግዚአብሔር አንተ የልብን ኃይል ስፋት ምላት ርቀት ትገዛዋለህ ሕሊና ልመርምር ልመርምር ማለቱን ሁሉ እንዳይመረምር አድርገህ ትወስናለህ አለ ቅዱስ ዳዊት ። የበቃም በቅቶ እግር ያለውም ተሽከርክሮ ክንፍ ያለው በሮ አይምሮ ያለውም ተመራምሮ ሃይማኖትን ጨርሶ ሊያውቀው አይችልም ። ሃይማኖት በሰዎች ተመርምሮ ከታወቀ ሒሳብ ይሆናል እንጂ ሃይማኖት አይደለም ። ሃይማኖት ሃይማኖት የሚሆነው ሰዎች ሳያውቁት የቀረ እንደሆነ ነው ። ቅዱስ ኤጲፋኖስም ይናገራል ፦ እግዚአብሔር ልዑል እግዚአብሔር የተባለው ከሕሊና በላይ ስለሆነ እንጂ ሰዎች መርምረው ከደረሱበት እግዚአብሕር ልዑል አይደለም ። ልዑል የሚባለው ከፍጥረታት በላይ ስለሆነ ነው ይላል ። ስለዚህ ያ የማይመረመረው እግዚአብሔር ሰው መርምሮ ስለማይደርስበት እራሱን ካልገለጠ በቀር ፍጥረት ሊያገኘው አይችልም ። ስለዚህ የክርስትና ሃይማኖት እራሱ እግዚአብሔር ተገልጦ የተናገረው ነው ነው ። እግዚአብሔርን ፈልጎ ማግኘት ማን ይችላል
መላእክት ካገኙት እንዴት እግዚአብሔር ይሆናል የሚመረመር እግዚአብሔር እግዚአብሔር አይደለም ። የሚመረመር እግዚአብሔር የለም ። የማይመረመር እግዚአብሔር እንጂ!!! አንድ አምላክ፦ የሚመረመር ከሆነ እርሱ ፍጡር እንጂ አምላክ አይደለም። የሚታወቅ ከሆነ እርሱ ፍጡር እንጂ አምላክ አይደለም ። ስለዚህ ተመልከቱ እግዚአብሔር ስለ እራሱ ካልገለጠ በቀር ስለ እግዚአብሔር ማወቅ የሚችል የለም ።
አልቦ ዘየአምሮ ለአብ ዘእንበለ ለወልድ ባሂቲቱ ወአልቦ ዘያአምሮ ለወልድ ዘእንበለ አባይቲቱ ወለዘፈቀደ ወልድ ይክሥት ሎቱ ማቴዎስ ፲፩፥፳፭-፳፰ ከወልድ በቀር አብን የሚያውቀው የለም ከአብም በቀር ወልድን የሚያውቀው የለም ከመንፈስ ቅዱስም በቀር አብ ወልድን የሚያውቅ የለም ከአብና ከወልድም በቀር መንፈስ ቅዱስን የሚያውቅ የለም ።
455 viewsመሸ በከንቱ, 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 14:42:51 https://vm.tiktok.com/ZMNmVxeaE/?k=1
686 viewsመሸ በከንቱ, 11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:32:57 " #ያመነ #የተጠመቀም #ይድናል፥ #ያላመነ #ግን #ይፈረድበታል።" የሚለው ጥቅስ ሳያምን ስለተጠመቀ ነው የሚፈረድበት አያስብልም ያላመነ ግን ይፈረድበታል አለ እንጂ ሳያምን በመጠመቁ ይፈረድበታል አይልም እንደዚያም ከሆነ ያ ሰው ሳይምንም ሳይጠመቅም ቢቀር አይፈረድብትም ወደ ማለት ሊያደርስ ነው ሰዎች ይሄን ጥቅስ ለሕጻናት ጥምቀት ለመቃወም ሲጠቅሱት ያስቀኛል ይሄ ጥቅስ ሕጻናትን የሚጨምር ከሆነ ያላመነ ግን ይፈረድበታል ስለሚል ህጻናት ቢሞቱ ባለማመናቸው ይፈረድባቸዋል ሊሉን ነው
690 viewsመሸ በከንቱ, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:32:57 አንድ መነኩሴ በገዳም ሲኖር ባህታዊ ነው። ሄዱና አባትህኮ ሞተ አሉት ፦ እርሱም አንተ ለምን ትሰድበኛለህ አባቴ የማይሞት የዘላለም ሕያው ነው ብሎ መለሰ። አባትህ ጎንደሬ ነው ጎጃሜ ነው ትግራይ ነው አማራ ኦሮሞ ቤንሻንጉል ጉምዝ ጉራጌ ነው ስትባሉ #ለምን_ትሰድበኛለህ የኔ አባት የዘላለም አባት ነው በሉ እርሱም ሕያው እግዚአብሔር ነው ። የሰማይ አባት ይኑራችሁ ። በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን
659 viewsመሸ በከንቱ, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 22:27:22

934 viewsአቡ (ወንዴ), 19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 20:25:57 ኧረ ርዕስ አሰጣጥ ዉ... አገላለጹ እኔን እንደሆነ ስሜን ሳይ ነው ያወኩት። እና እላችኋለሁ "እኛም ደንግጠን ነበር"...hehe ለማንኛውም እስኪ እንደ ተሞክሮ ነገር ከመምህር ተስፋዬ ጋር ያደረኩትን ቆይታ ተካፈሉ



1.7K viewsአቡ (ወንዴ), edited  17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 13:54:15 ስለመርገመ በለስ አንብቡ ቀኑም ዛሬ አይደል በዚያውም ሙስሊሞች ለሚጠይቋችሁ በቂ መልስ ይዟል ይሄን በጽሑፍ የሚቀይር ፈቃደኛ የሆነ ካለ @Semagnd btlkulgn desylegnal
1.9K viewsመሸ በከንቱ, edited  10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 13:45:08
@felgehaggnew
@felgehaggnew
1.6K viewsመሸ በከንቱ, 10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 13:45:08
@felgehaggnew
@felgehaggnew
1.5K viewsመሸ በከንቱ, 10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 13:45:08
@felgehaggnew
@felgehaggnew
1.1K viewsመሸ በከንቱ, 10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ