Get Mystery Box with random crypto!

650 ሺ ብር የተጠራው ሰንጋ አንድ ሰንጋ 650 ሽህ ብር ተጠርቷል።ሌላው 550 ሽህ ጥሪ ተሰምቷ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

650 ሺ ብር የተጠራው ሰንጋ
አንድ ሰንጋ 650 ሽህ ብር ተጠርቷል።ሌላው 550 ሽህ ጥሪ ተሰምቷል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሬ ከተማ አስተዳደር በአመት አንድ ጊዜ የሚውለው የሆሳዕና ገበያ ዘንድሮም የተለየ ነገር ታይቶበታል።
ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ሰንጋ 650 ሽህ ብር ተጠርቷል ።የሰንጋው ባለቤት ወጣት ሚጥዬ ታደለ ይባላል።650 ሽህ ብር የተጠራው የጅሩ ሰንጋ ገና አልተሸጠም።

ሌላው በዚሁ ገበያ የሞረትና ጅሩ ወረዳ የማንጉዶ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ አበበ በፍቃዱ  ለ1 አመት ያክል እንደ ልጄ ስንከባከበው ነበር ያሉትን ሰንጋ በ550 ሽህ ብር ሲሉ ጠርተዋል ሲል የከተማ አስተዳደሩ ሚዲያ አስነብቧል።የሁለቱም ሽያጭ ገና አልተፈፀመም።
የቴሌግራም ቻናላችንን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ያድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial