Get Mystery Box with random crypto!

በርካታ የሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግር ጥቆማዎች እየደረሱኝ ነው - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

በርካታ የሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግር ጥቆማዎች እየደረሱኝ ነው - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን
በርካታ የሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግር ጥቆማዎች እየደረሱት መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ የጥቆማ መቀበያ ነጻ የስልክ መስመር ይፋ ካደረገ በኃላ በርካታ ጥቆማዎች እየደረሱት መሆኑን የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለኢቢሲ ሳይበር ተናግረዋል፡፡

የሚመጡ ጥቆማዎችን ተገቢነት በማጣራት ጥፋተኞችን ለሕግ ለማቅረብ ከፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የጥላቻ እና ሐሰተኛ ንግግሮች በአዋጁ መሰረት ከገንዘብ እስከ እስራት ቅጣት እንደሚያስከትሉ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ጠቁመዋል፡፡

ባለስልጣኑ የማህበራዊ የትስስር ገጽ አገልግሎት ሰጪዎች የኢትዮጵያን ሕግ እና ስርዓት አክብረው እንዲሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

ህዝቡ ለሀገራዊ ሰላም እና ለህዝቦች አንድነት ፀር የሆኑ የሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግሮችን ሲመለከት በ9192 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማዎችን እንዲሰጥ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡
የፌስቡክ ገፃችንን ከስር ባለው ሊንክ Follow ያድርጉ
https://www.facebook.com/ayuzehabesha.1999