Get Mystery Box with random crypto!

ራያ በርተክላይ ውጊያ ተከፍቷል ትናንት ከደቡብ ትግራይ የተፈናቀሉ ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ አደ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

ራያ በርተክላይ ውጊያ ተከፍቷል
ትናንት ከደቡብ ትግራይ የተፈናቀሉ ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ የሚለውን እንደሽፋን በመጠቀም ትናንት ጀምሮ በራያ በርተክላይ ላዕላይ ዳዩ ቀበሌ የህወሓት ታጣቂዎች ተኩስ መክፈታቸውን መዘገቤ ይታወሳል። ከደቂቃዎች በፊት ወደ አካባቢው ደውዬ የነበረ ሲሆን ትናንት አመሻሹን ተኩሱ ቆሞ የነበረ ቢሆንም ዛሬ 5:00 ጀምሮ በርተክላይ ከፍተኛ ውጊያ መጀመሩን ገልፀውልኛል። የአማራ ክልል አድማብተና እና የህወሓት ታጣቂዎች በዚህ ሰዓት የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በራያ አላማጣ ታኦ በሚባል ቦታ ተኩስ ያለ ሲሆን ሞርተር 82 ፣ አርቢጅ ( ላውንቸር ) እና ዲሽቃ እየተጠቀሙ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቼ ገልፀዋል።
ትናንት በነበረው ተኩስ ንፁሃንን ጨምሮ ከሁለቱም ተዋጊ ሀይሎች በኩል ሰዎች ሞተዋል ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከሁለት ሳምንት በፊት በመቀሌ ተጀምሮ የነበረውን ፖለቲካዊ ውይይት ለማጠናከር ትናንት በአዲስ አበባ ተጨማሪ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ(አዩዘሀበሻ)።
========================
ጥቆማ
የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial