Get Mystery Box with random crypto!

ለስራም ሆነ ለትምህርት ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገር መላክ በስራ እና ክህሎት ሚኒቴር ኃላፊነት የሚተገበ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

ለስራም ሆነ ለትምህርት ዜጎችን ወደ ውጭ ሀገር መላክ በስራ እና ክህሎት ሚኒቴር ኃላፊነት የሚተገበር መሆኑ ተገለጸ
ዜጎችን ለስራም ሆነ ለትምህርት ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ፍቃድ ለስራና ክህሎት ሚኒስቴር ብቻ የተሰጠ ሃላፊነት መሆኑን በሚኒስቴሩ የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጫ ዴስክ ሃላፊ አቶ ተክሌ ተስፉ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ በተለያዩ ከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ኤጀንሲዎች ሰዎችን ካናዳና ወደ ሌሎችም የውጭ ሀገራት ስራ እናስቀጥራችኃለን በሚል የሚስተላለፉት ማስታወቂያ ፈጽሞ ፈቃድ የሌለው እና ህገ ወጥ መሆኑን በመጥቀስ በጥቆማና በፍለጋ ሲደረስባቸው እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ሃላፊው ገልጸዋል።

ለኤጀንሲዎች ፈቃድ መስጠቱንም መቆጣጠሩንም የሚመለከተው የመንግስት ተቋም ስራና ክህሎት ሚኒስቴር መሆኑን በመናገር በፌደራልም በክልልም ያሉ ኤጀንሲዎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፈቃድ ከተሰጣቸው ብቻ ስራው ላይ መሰማራት እንደሚችሉ አቶ ተክሌ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እየተበራከቱ የመጡት ህገ ወጥ ኤጀንሲዎች በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እርምጃ እንደሚወሰድባቸውና ህጋዊ በሆነ አሰራር ላይ ብቻ ተመስርተው የዜጎችን የስራ ሁኔታ እንደሚያግዙ የዴስክ ሃላፊው አመላክተዋል።

ዜጎችን ወደ ውጭ እንልካለን የሚሉ ህገ ወጦች ምንም አይነት እውቅና የሌላቸው በመሆኑ ሲደረስበት ከፖሊስ ጋር በመሆን እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተነግሯል።

የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial