Get Mystery Box with random crypto!

ከቴሌ እውቅና ውጪ ሕገ-ወጥ የስልክ መስመሮችን ሲጠቀሙ ነበር የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

ከቴሌ እውቅና ውጪ ሕገ-ወጥ የስልክ መስመሮችን ሲጠቀሙ ነበር የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሐረሪ ክልል ጄኔላ ወረዳ ሕገ-ወጥ የስልክ መስመሮችን ከቴሌ እውቅና ውጪ ሲጠቀሙ ነበር የተባሉ 4 ግለሰቦች ከነ እቃው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎች በድብቅ ከቴሌ እውቅና ውጪ የስልክ መስመሮችን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ወደ ውጪ ሀገራት በማስደወል ሕገ-ወጥ አገልግሎት ሲሰጡ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጄኔላ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መፍቱህ ከድር ተናግረዋል፡።

በሕገወጥ መንገድ አገልግሎት ይሰጥ የነበረው የስልክ መስመር የመንግስትን ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳና በቴሌ አገልግሎት ላይ ኪሳራ የሚያስከትል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ተጠርጣሪዎች በድብቅ ግለሰቦችን ወደ ውጪ ሀገራት በከፍተኛ ገንዘብ በማስደወል የግል ጥቅማቸውን በሕገ-ወጥ መንገድ ያገኙ እንደነበር የክልሉ ፖሊስ መረጃ አመልክቷል፡፡
በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር የገባ ባለ አንቴና የስልክ ማሽን፣ ብዛት ያላቸው ሲም ካርዶች፣ ሞባይሎች፣ የዋይፋይ ሳጥኖች፣ የተለያዩ ኬብሎች፣ ፍላሾችና አንቴና መያዛቸውም ተጠቅሷል፡፡
#FBC
መረጃ ለማድረስ እንዲሁም ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይፃፉልን
http://t.me/ayulaw