Get Mystery Box with random crypto!

Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የሰርጥ አድራሻ: @ayuzehabeshaofficial
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 181.36K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 299

2022-09-29 16:14:52
የድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ የድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ሥርዓተ ቀብር በቅድስተ ሥላሴካቴድራል ተፈፅሟል፡፡
የተወዳጁን የኪነጥበብ ሰው የአስከሬን ስንብት ረፋድ 4 ሠአት በመኖሪያ ቤቱ የተከናወነ ሲሆን በወዳጅነት ፓርክም ከ6፡ 00 ሰዓት ጀምሮ በመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በሙያ አጋሮቹ፣ በአድናቂዎቹና ወዳጅ ዘመዶቹ የአስክሬን ስንብት ተካሂዷል፡፡
ከቀኑ በ 10 ሠአት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ ጓደኞቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት ሥርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል።

ወዳጅ ዘመዶቹ አደናቂዎቹና ቤተሰቦቹ በአርቲስቱ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል።
የድምፃዊ ማዲንጎ በድንገተኛ ህመም መስከረም 17/2015 ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።
ጥቆማ
መረጃ በቪድዮ መስማት ለምትፈልጉ ከስር ባለው ሊንክ ዩቱብ ተከታተሉ





38.4K viewsAyu, edited  13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 15:56:57 ጎብዬ
ጎብዬ ዙሪያ አንድ ሻለቃ ለህወሓት ሲያስተኩስ እርምጃ ተወስዶበታል። የጥምር ጦሩን ግስጋሴ ለመግታትም ቢሞክር አልተሳካም፣ይችን ክፍተት ተጠቅመው የህወሓት ታጣቂዎች የተነጠቁትን የበላጎ ተራራን መልሶ ለመያዝ ትናንት ምሽት ከፍተኛ ትንቅንቅ አድርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ህወሀት ከዞብል ወደ ጎብዬ ማታ ተጨማሪ ሀይል አስገብቶ የነበረ ቢሆንም አብዛኛው በሜካናይዝድ ጦሩ ተመቶበታል።
በዚህ ሰዓት በዱርለበስ በኩል በአሲላንባ ተራራ፣እንዲሁም ባለፈው አመት ምሰውት በሄዱት የከፈተኝ ምሽግ ውስጥ ሆነው ውጊያ እያደረጉ ይገኛሉ።
በሮቢት በኩል የተለወጠ ነገር የለም።
አዩ ዘሀበሻ
መስከረም 19/2015 ዓ.ም
ከቀኑ 9:56
ቀሪውን በዚህ ሊንክ ዩቱብ ተከታተሉ





38.3K viewsAyu, 12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 13:55:41 Watch "አሁናዊ ዋና ዋና ዜናዎች ጎብዬ መቀሌ አዲግራት አዲዐርቃይ መተማ በመቀሌ ከፍተኛ ተቃውሞ አመራሮች ታሰሩ " on YouTube


41.9K viewsAyu, 10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 11:12:02 በመቀሌ ለድሮን ጥቃት ጥቆማ እና መረጃ ሰጥታችኋል በሚል የከተማ እና የዞን አመራሮችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መታሰራቸው ታውቋል። በዚህ የተነሳ የመቀሌ ህዝብ ተረብሿል።
==================
በዝርዝር ወደ ኋላ ላይ በዩቱብ የማጋራችሁ ይሆናል፣መረጃ በቪድዬ መስማት ለምትፈልጉ በዚች ሊንክ ግቡ





18.3K viewsAyu, edited  08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 11:04:58 የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ያደርጋል። የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕተኛው ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ በስብሰባው ላይ ስለድርድሩ ማብራሪያ ይሰጣሉ። ፈረንሳይ በጠራችው በዚህ ስብሰባ ኢትዮጵያም ተጋብዛለች።
zehabesha
ዛሬ በርካታ መረጃዎችን እንለዋወጣለን ጠብቁኝ
መረጃ በቪድዬ መስማት ለምትፈልጉ





19.2K viewsAyu, edited  08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 21:29:59 በግዳን በኩል የተኩለሽን ምሸግ የተነጠቀው የህወሓት ታጣቂ ምሽጉን መልሶ ለመያዝ ሀይል አደራጅቶ ቢመጣም አልተሳካለትም። በራያ ግንባር በአራዱም፣በቆላ በላጎ በየተራራው ተቆርጦ የቀረው የህወሓት ታጣቂ ስፍር ቁጥር የለውም። አብዛኛው የሬሽን አቅርቦት ተቋርጦበታል። በዚህ የተነሳ ያልደረሰውን ሰብል ጭምር እያወደሙ ይገኛሉ። የሚሆነውን አብረን እናያለን።
አዩ ዘሀበሻ
መስከረም 18/2015 ዓ.ም
Time to rest,good night see you tomorrow. May GOD, peace, love , happiness and unity be upon Ethiopia and her heroic people at large.
=======================
ጥቆማ
በዚህ ዙሪያ ከስፍራው በስልክ ያሰባሰብኩትን ሰፋ ያለ ዘገባ ጠዋት በዩቱብ  የማጋራችሁ ይሆናል ከስር ባለው ሊንክ ግቡ





39.4K viewsAyu, edited  18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 20:56:34
ተጨማሪ ድንጋጌዎች እና የተሻሻሉ መመሪያዎች ይሄን ይመስላል። አንድ ደላላ 2% ይከፍል የነበረው የተሻረ ሲሆን አሁን በተሻሻለው 30% ግብር እና 10% ታክስ እንዲከፍል ያዛል። ቀሪው ከላይ ተያይዟል።
======{{==================
መረጃ በቪድዬ መስማት ለምትፈልጉ


41.1K viewsAyu, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 20:43:29
የአመራ ክልል ንግድ ቢሮ ደላሎች ግብር እንዲከፍሉ መመሪያ ወጣ
በድለላ ስራ የተሰማሩ ነጋዴዎችን ግብር ለማስከፈል የወጣ መመሪያ ቁጥር 19/2014 ዓ.ም።
በዚህም አንድ ደላላ 30% ግብር እና 10% ታክስ ይከፍላል ሲል መመሪያው ያዛል።
ማሳሰቢያ
በመመሪያው ላይ "መመሪያ ቁጥር 19/2014" ተብሎ የተገለፀው መመሪያ ቁጥር 19/2015 ዓ.ም
እንዲሁም መመሪያው የወጣበት ቀን መስከረም / 2015 ዓ.ም ተብሎ እንዲነበብ ለማሳሰብ እወዳለሁ።
======{{==================
መረጃ በቪድዬ መስማት ለምትፈልጉ


40.0K viewsAyu, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 20:01:20 የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ ተደረገ
**
የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታወቀ።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት 6:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ የሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል።

1. ቤንዚን በሊትር - 57 ብር ከ05 ሣንቲም
2. ነጭ ናፍጣ በሊትር - 59 ብር ከ90 ሣንቲም
3. ኬሮሲን በሊትር - 59 ብር ከ90 ሣንቲም ሲሆን

4. በሥራ ላይ የነበረው ዋጋቸው ባለበት የሚቀጥል የነዳጅ ውጤቶች

4.1. የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር - 76 ብር ከ87 ሣንቲም

4.2. ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር - 43 ብር ከ89 ሣንቲም

4.3. ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር - 43 ብር ከ06 ሣንቲም እንዲሆን ተወስኗል።

በሌላ በኩል አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተረዘጋው የታለመ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽክርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በሁለተኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደገረም።

እነዚህ ተሽከሪዎች በሐምሌ ወር በተወሰነላቸው ዋጋ ቤንዚን በብር 41.26 በሊትር እንዲሁም ነጭ ናፍጣን በብር 40.86 በሊትር እየገዙ እንዲቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ከእጥፍ በላይ ያደገ ድጎማ ከመንግሥት እንዲያገኙ የተደረገ ስለሆነ በሚቀጥው ጊዜ ዋጋ እስኪሻሻል ድረስ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አይደረግም ሲል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።
======{{==================
መረጃ በቪድዬ መስማት ለምትፈልጉ


48.4K viewsAyu, edited  17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 19:19:41
አሳዛኝ መረጃ
በአደዓ በርጋ በደረሰ የመኪና አደጋ 15 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ
በምስራቅ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ ዛሬ ከቀኑ 6:30 ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል። ሰዎችን አሳፍሮ ሲሄድ የነበረው መኪና ከተሳቢ ጋር ተጋጭቶ ነው አደጋው የደረሰው፣ 15 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 30 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት እና በ2 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።
መረጃ በቪድዬ መስማት ለምትፈልጉ


40.6K viewsAyu, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ